Get Mystery Box with random crypto!

#የተለያዩ በነገው እለት ወደ ስራ የሚገባው የአማራ ባንክ የተሰኘው የንግድ ተቋም በጣም በርካታ | (ABC) Amhara Broadcasting Corporation

#የተለያዩ

በነገው እለት ወደ ስራ የሚገባው የአማራ ባንክ የተሰኘው የንግድ ተቋም በጣም በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደሚጋሩት ከአማራ ህዝብ ወይም ከክልሉ ህዝብ ጋር ግንኙነት እንዳለው አብዝተው ይገለጻሉ።

ነገሩ ግን ወዲህ ነው ተቋሙ የተመሰረተው የክልል ስም ይዞ ነው እንጂ የክልሉ ሀብት ሁኖ አይደለም ይልቁንም የክልሉ ህዝብ ሀብት የሆነው አብቁተ የተሰኘው ተቋም ማሳደግ ሲገባ የግለሰቦች የሀብት ምንጭ የሆነውን የአማራ ባንክ እንደ ህዝብ ባንክ ማስተዋወቅ ተገቢ አይመስለኝም።

ባንኩን የመሰረቱት ደግሞ የመንግስት ተቋማት ሀላፊዎች ናቸው ታዲያ ይህን የንግድ ተቋም ወደፊት በአማራ ክልል የተለየ እንክብካቤ ሊደረግ እና የንግድ ስርዓቱን የሚውክ ህገወጥ ተግባር በሀላፊዎች የፈፀሙ ይሆናል የሚል ስጋት አለ።

አንድ የህዝብ ተቋም የህዝብ ነው ለማለት በተቋሙ የሚገኙ ትርፋች ለህዝብ አገልግሎት የሚሆኑ ትምህርት ቤት የጤና ተቋማት የሚገነባበት እና የህዝብ ተወካዮች የሚመሩት ወይም ተጠሪ የሆነ ነው በዚህ መሰረት የአማራ ባንክ ይህዝብ ሳይሆን የንግድ ተቋም ነው።

https://t.me/JournalistNetsanetGetachew