Get Mystery Box with random crypto!

  የካቲት 12 ቀን 2015 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015 ዓ.ም በማታ መርሃ ግብር ለመጀመሪያ | Abrehot Library

 
የካቲት 12 ቀን 2015
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015 ዓ.ም በማታ መርሃ ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት በዲፕሎማችሁ ወይም ደረጃ 4 ለምታመለክቱ አመልካቾችን ይጋብዛል
 
 
በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
 
1. የዲፕሎማችሁን ወይም ደረጃ 4 ትምህርት ማስረጃ ከCOC ደረጃ 4 ጋር ማቅረብ
2. ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ
 
ማሳሰቢያ፡-
 
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 300 / ሶስት መቶ / በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን መላክ፤
4. ምዝገባዉን ካከናወኑ በኋላ የትምህርት  ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
5. ለመግቢያ ፈተና 600 ብር በኢትዮዺያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000087392067 ከፍላችሁ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ የመፈተኛ ቦታ ይዞ መገኘት ይጠበቅባችኋል
6. በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲዉን የመግቢያ ፈተና ጊዜን፤ በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (www.aau.edu.et) እና (https:\\portal.aau.edu.et) ወደፊት ይገለጻል፡፡
7. የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 
 
    የምዝገባቀን፡   ከየካቲት 13 እስከ የካቲት 17 2015 ዓ.ም 
የምዝገባቦታ ፡    በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
 
  
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር