Get Mystery Box with random crypto!

የካቲት 11 ቀን 2015   ማስታወቂያ   በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015 የትምህርት ዘመን በመ | Abrehot Library

የካቲት 11 ቀን 2015
 
ማስታወቂያ
 
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
 
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015  የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
የካቲት 15 ቀን እና የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ
1ኛ - የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ   ኮፒ፣
2ኛ - ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
3ኛ - ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡
➢ በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡
➢ ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡
➢ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲውን ድረገጽ https://portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን
➢ ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡
➢ ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም https://portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
➢ በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 17 2015 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡
 
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ                                                             ሬጅስትራር