Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ 2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ | Abrehot Library

ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ 2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሚያዚያ 24 ቀን እና ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡

ምዝገባንና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከwww.aau.edu.et, http://portal.aau.edu.et እና ከዩኒቨርስቲው የማህበራዊ ገጾች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳዉቃል፡፡


በረመዳን በዓል ምክንያት መድረስ የማትችሉ እስከ አርብ ሚያዝያ 28/2014 ዓ.ም ድረስ ወደ በተመደባችሁበት ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡