Get Mystery Box with random crypto!

liqe liqawnt zelealem tekle

የቴሌግራም ቻናል አርማ ztekle — liqe liqawnt zelealem tekle L
የቴሌግራም ቻናል አርማ ztekle — liqe liqawnt zelealem tekle
የሰርጥ አድራሻ: @ztekle
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 176

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-12 12:05:09 The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 10 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 13:12:52 The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 30 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-14 18:41:50 Watch "ጾመ ነነዌ +++ የትንቢተ ዮናስ ትርጓሜ +++ Ethiopian Orthodox Sibket +++" on YouTube


181 views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 17:30:06 Watch "እስክንድርን ያስደነገጠችው ታላቋ ሕንደኬና ጥበቧ" on YouTube


199 views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-22 03:09:02 Watch "ሰማያዊው በምድራዊው ተጠመቀ" on YouTube


163 views00:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-22 03:08:54
ጥር 10 ታቦተ መድኃኔ ዓለምንና ታቦተ ዮሐንስ መጥምቅን አጅበን ወደ ባሕረ ጥምቀት ጉዞ እያደረግን። እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ። ጌታችን፣ መድኀኒታችን፣ አምላካችን፣ አባታችን፣ ብርሃናችን፣ ፀሐያችን፣ ሕይወታችን፣ እረኛችን፣ የሕይወት እንጀራችን፣ የሕይወት መጠጣችን፣ ንጉሣችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንወድሃለን እናመሰግንሃለን። የዘመናት አስገኝ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለዓመቱ አድርሰን።
ውድ ጓደኞቼ ለዓመቱ በሰላም ያድርሳችሁ። የበዓለ ጥምቀት ፎቷችሁን አጋሩን።
147 views00:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 11:33:21 በመቀጠልም ከ1245-1268 ዓ.ም ለ23 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በዐጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሳሳቢነት ታቦታቱ በባሕረ ጥምቀት ሲውሉ ምእመናን በታላቅ ድምቀት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እንዲውሉ መንፈሳዊ ዐዋጅ አሳወጁ በማለት ገልጸዋል፡፡

በመቀጠል ከ1426-1460 ዓ.ም ለ34 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በታላቁ ንጉሥ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥትም ንጉሡ ከሊቃውንት ጋር በመወያየት የበዐሉን ታሪክ ተከትሎ ታቦታቱ ጥር 10 ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት እንዲወርዱና ጥር 11 እንዲመለሱ መወሰኑን ሊቀ ትጉኃን ኀይለ ጊዮርጊስ ይተነትናሉ።

እንደሚታወቀው ታቦተ ጽዮን በሄደችበት ሁሉ በረከትን ትሰጥ እንደነበር የአቢዳራን ቤት በበረከት እንደሞላች፤ የዮርዳኖስን ባህር እንደከፈለች፣ የኢያሪኮን ቅጽር እንዳፈረሰች፣ የፍልስጤማውያን ጣዖት ዳጎንን ቀጥቅጣ እንዳጠፋች ሀገሪቱ ትባረክ ዘንድ ርኲሳን መናፍስት ይርቁ ዘንድ ምድሪቱ በቃል ኪዳኑ ታቦታት ትቀደስ ዘንድ ታቦታቱ በመጡበት መንገድ እንዳይመለሱ ታላቅ ዐዋጅ አሳውጀው በዐዋጁ መሠረት ዛሬ ድረስ በደመቀ መልኩ በዓሉ እየተከበረ ይገኛል ብለው ታሪካዊ ዳራውን ጽፈዋል፡፡

ከባሕር ማዶ ጸሐፍያን ውስጥ ቼሩሊ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ቁመቱ 14 ወርዱ 8 ክንድ የኾነ ባሕረ ጥምቀት እንደተዘጋጀ ሲጽፍ፤ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐጼ ልብነ ድንግል በተገኙበት እጅግ ታላቅ ድንኳን በባሕረ ጥምቀቱ ዙሪያ እንዴት ተተክሎ እንደተከበረ ፍራንቺስኮ አልቫሬዝ ገልጿል፤ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረውን የበዓለ ጥምቀት አከባበር ደግሞ ፔድሮ ፔየዝ ዘግቦት ነበር።

አሁን ባለንበት ጊዜም ዳዊት በመዝ 44፡16 ላይ “በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ” በማለት እንደተናገረ ከመቼውም በበለጠ እግዚአብሔር የወጣቱን ልብ በረድኤት ጎብኝቶት "አልፋ ወዖ ቤጣ የውጣ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወወልደ ማርያም ሥግው" ተብሎ ሕይወት የሆነው የአምላካችን የኢየሱስ ስም ለተጻፈበት ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ለሚሠዋበት ለቃል ኪዳኑ ታቦታት ክብር አካባቢውን እያስዋበ፣ ታቦታቱ የሚሄዱበትን መንገድ እየጠረገ፤ ታላላቅ ምንጣፎችን ታቦታቱ በሚሄዱበት መንገድ እያነጠፈ ለቃል ኪዳኑ ታቦት እንደ ነቢዩ ዳዊት ከፍተኛ ክብር በመስጠት እግዚአብሔርን እያገለገለ ይገኛል (1ኛ ነገሥት 6፡1-23)፡፡

“የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት” (ኢያ 3፡3)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ]
የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Rodas9
የYoutube Channel:- https://youtube.com/channel/UCFKnpmDyWe3LQ_9Gx3TMnAg
131 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 11:33:07 [እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ጥምቀት ማለት ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውሃ ውስጥ ገብቶ መውጣት” ማለት ነው፡፡

ምስጢረ ጥምቀትን የመሰረተልን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ሲመሠርትም በማዘዝ ብቻ ሳይሆን በሥራ በማሳየት ጭምር ነው (ማቴ 3፡17፤ ማር 1፡9፤ ሉቃ 3፡21፤ ዮሐ 1፡31)፡፡

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እከብር አይል ክቡር የባሕርይ አምላክ ሆኖ ሳለ በዮርዳኖስ ወንዝ በአገልጋዩ (በፍጡሩ) በዮሐንስ የተጠመቀበት ምክንያት፦
1) አንድነቱን ሦስትነቱን ለመግለጽ
2) የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ (ቆላ 2:14)
3) በእርሱ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት ለመቀደስ
4)ለጥምቀታችን ኀይልን ለመስጠት
5) ለአብነት ርሱ ተጠምቆ እናንተም ተጠመቁ ብሎ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በ30 ዘመኑ ጥር 11 ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት፤ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ እንደሚጠመቅና የዮርዳኖስ ወንዝ ጌታን ስታይ እንደምትሸሽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 113፡3-5፦ “ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ፤ ተራሮች እንደ ኮርማዎች፥ ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ፤ አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ ምን ሆናችኋል?” በማለት ከ1000 ዓመት አስቀድሞ ትንቢት የተናገረ ሲሆን፤ ብዙ ምሳሌም አለውና ከትርጓሜ ወንጌል ይመልከቱ፨

ዮሐንስ ወደ ጌታችን መምጣት ሲገባው ጌታችን ወደ ዮሐንስ የሄደበት ምክንያት የመጀመሪያው ትሕትናን ለማስተማር ነው።
ሁለተኛው ለአብነት ለምሳሌ ነው፤ ይኸውም ዮሐንስ ሄዶ አጥምቆት ቢሆን ዛሬ ባለሥልጣናቱ ካህናትን ቤታችን ድረስ መጥታችሁ አጥምቁን ይሏቸው ነበርና ሰማያዊ ንጉሥ እኔ ከሄድኩ እናንተም ሄዳችሁ ቤተ ክርስቲያን ተጠመቁ ለማለት ሄዷል።

ዮሐንስ ግን ወደርሱ በትሕትና የመጣው አምላኩ ክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ሲል ጌታችንም “ጽድቅን ልንፈጽም” ይገባናል ብሎ ትንቢተ ነቢያትን ሊፈጽም እንደመጣ ሲነግረው ዮሐንስ እሺ አለ።

ከዚያም ተያይዘው ወደ ዮርዳኖስ ሲወርዱ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት የዮርዳኖስ ወንዝ ወደ ኋላዋ ሸሽታለች በዚህም ዳዊት በመዝ 77፡16 ላይ፦
“አቤቱ፥ ውሆች አዩህ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውሆችም ጮኹ” ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ።

ጌታችንም ተጠምቆ ከውሃው ከወጣ በኋላ ሰማይ ተከፈተ ይላል። መተርጉሙ ሲያመሰጥረው፦
1) "ከመ ተጠምቀ ሰማያዊ ናሁ ወረደ እምሰማይ ወሀለዎ ከመ ይዕርግ ውስተ ሰማይ" (ሰማያዊው እንደተጠመቀ ከሰማይ እንደወረደ ወደሰማይ እንደሚያርግ ለማስረዳት)

2) "ወዳግም እስመ አናቅጸ ሰማያት ተዐጽዉ በምክንያተ ዕልወተ አዳም ..." (በአዳምና በሰዎች በደል ምክንያት የሰማያት ደጆች ተዘግተው ነበር። ገነትም ተዘግታ በእሳት ጦር ትጠበቅ ነበር። ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ በጥምቀቱ ምክንያት የሰማይ ደጃፎች ተከፈቱ)።

3) "ሣልስ ያጠይቀነ ከመ እለ ይጠመቁ ይትረኃው ሎሙ አናቅጸ ሰማያት ..." (ለሚጠመቁ ሰዎች የሰማያት ደጃፎች እንደሚከፈቱላቸውና ከሞት ከተነሡ በኋላ ወደ ሰማይ እንደሚወጡ ያስረዳል)።

4) ሰማያት ተከፈቱ መባሉ ደጃፍ በተከፈተ ጊዜ በውስጥ ያለው ዐዲስ ነገር እንዲገለጥ በጥምቀትም ዐዲስ ምስጢር ይገለጣልና ነው።

አብ በሰማይ ኹኖ “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ዘቦቱ ሠመርኩ” (በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው) ብሎ ሲመሰክር፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስም በጽንፈ ዮርዳኖስ ቁሞ ታየ፡፡

መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ለምን ወረደ? ቢባል
ርግብ ኀዳጊተ በቀል (በቀልን የምትተው) ናት፤ መንፈስ ቅዱስም ኀዳጌ በቀል፤ ቸር ነኝ ሲል፡፡
ርግብ ልጆቿን ተከባክባ እንድታሳድግ፤ መንፈስ ቅዱስም ለምእመናን ልሕቀት መንፈሳዊ እሰጣለኊ ሲል፡፡
የርግብ ዐይኑ ነጩም ጥቁሩም ያያል አይከፈልበትም፤ መንፈስ ቅዱስም ዕውቀት ሥልጣን አይከፈልብኝም ሲል፡፡
ርግብ በኖኅ ጊዜ የጥፋት ውሃ መጒደሉን የወይራ ቅርንጫፍ ይዛ ብሥራተ ፍሥሐ የምሥራችን እንደገለጸች፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በመውረድ ከርሱ ጋር የሥልጣን አንድነት ባለው በወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በመውረድ የፍዳ ዘመን ማክተሙን ተስፋ መስቀልን አብሥሯል፡፡
ርግብ ክንፏን ቢመቷት፤ ዕንቊላሏን ቢሠብሩባትም ቤቷን ካላፈረሱባት በቀር አትኼድም፤ መንፈስ ቅዱስም ምንም ኀጢአትን ቢሠራም፤ ጨርሰው ካልካዱት በስተቀር አይለይምና፡፡

ይኸውም በምስጢረ ሥላሴ ትምህርት እንደምንረዳው ከሰማይ ኾኖ የመሰከረው ክርስቶስ በቃልነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ያሉበት (ሕልው የኾኑበት) አብ ነው።
ወርዶ በወልድ ራስ የተቀመጠው አብ በልቡናነት ክርስቶስ በቃልነት ሕልው የኾኑበት መንፈስ ቅዱስ ነው። በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ የታየው አብ በልቡናነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ሕልው የኾኑበት አካላዊ ቃል ክርስቶስ ነው፤ እንዲኽ አድርገው የአካል ሦስትነታቸውን የፈቃድ አንድነታቸውን ለማስረዳት አብ በደመና ኾኖ መሰከረ፤ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ታየ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ ታየ።

በዚኽም የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሚገባ ሲታወቅ በተጨማሪም “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ እግዚአብሔር አብ በመመስከሩ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው በኋለኛው ዘመን ከእመቤታችን ያለ አባት በኅቱም ድንግልና የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ብቻ መኾኑ በሚገባ ተረጋግጧል፤ ዕለቱም በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋንያ ሲባል በግእዝ አስተርእዮ በዐማርኛም የመታየት የመገለጥ ጊዜ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን ስለ ነገረ ጥምቀት የሰማችው ከሌላው ዓለም አስቀድማ ጌታችን ባረገ በጥቂት ወራት (በ34 ዓ.ም) በኢትዮጵያው ጀንደረባ አማካይነት ነው (የሐዋ 8፥26-39)፤ ይህም በዐል ከዘጠኙ ዐበይት በዐላት አንደኛው ሲሆን ጌታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ስላመራ ይህንን ለማሰብ ታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ያመራሉ።

በዚህ መልኩ መከበር እንዴት ተጀመረ? የሚለውን ሊቀ ትጉኃን ኃይለ ጊዮርጊስ በጻፉት የነገረ ሃይማኖት መጽሐፍ ላይ የጻፉትን ለአንባብያን ለማካፈል ወደድኩ። ይኸውም ከ515-529 ዓ.ም ለ14 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በአጼ ገብረ መስቀል ዘመን ሲሆን በጊዜው ቅዱስ ያሬድ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ ከዝማሬው በመነሣት ታቦታቱ ጥር 11 ጠዋት ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ አምርተው አመሻሹ ላይ ይመለሱ ነበር ብለዋል፡፡

ከዚያም ከ1157-1197 ዓ.ም ድረስ ለ40 ዓመት ኢትዮጵያን በመራው በታላቱ ጻድቅ ንጉሥ በላሊበላ ዘመን በአንድ አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስትያናት ታቦታቱ ባንድ ላይ እንዲያከብሩ ንጉሥ ላሊበላ ታላቅ መንፈሳዊ ዐዋጅን አሳውጆ በአንድ አካባቢ፣ ወረዳ፣ ያሉ በአንድ ላይ ማክበር ጀመሩ፤ በርሱ ዘመን የነበሩት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በጎንደር፣ በሸዋ፣ በአንኮበር፣ በመርጡለ ማርያም እየሄዱ ባሕረ ጥምቀቱን እንደባረኩ ይጽፋሉ፡፡
109 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 21:09:41
"ፈጣሪ በውስጧ ያኖረባት ፀሐይን በመመልከቻ ስመለከት ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ። የአቡሻህር ተማሪ ሳለሁ ስለ ምሕዋረ ፀሐይ፣ መሳክወ ፀሐይ፣ ምዕዛረ ፀሐይ፣ ሠረገላ ፀሐይ እና ስለ ፀሐይ የተለያዩ አቅማራት የተማርኳቸው ትዝ ይሉኝና በሐሳቤ ወደ ጉባኤ ቤት ትወስደኛለች።
በአቡሻህር፣ በሳይንስ የተተነችውን ጨምሮ በማዛሮት መጽሐፌ ላይ የጻፍኩትን መንፈሳዊ ምሳሌያቷን ሳስብ በእግረ ልቡናዬ ወደ ፀሐይ ክነፍ ይለኛል" (መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
[ጥር 6/ 2014 ዓ.ም. ጎንደር ሰንሰለታማ ተራሮች ባሉበት ፀሐይ፣ ጀንበር፣ ኦርያሬስ፣ ቶማስስን ስመለከት]
101 views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 17:51:07
109 views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ