Get Mystery Box with random crypto!

ብስራት ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bisrat_midea — ብስራት ሚዲያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ bisrat_midea — ብስራት ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @bisrat_midea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 307
የሰርጥ መግለጫ

"ሰላም ለኪ ቅድስት ቤተክርስቲያን አምሳለ እየሩሳሌም ሰማያዊት"
ይህ ቻናል የተከፈተው ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን መረጃ የምንለዋወጥበት በዓይነቱ፣ በይዘቱ ለየት ያለ ቻናል በይፋ ከፍቻለሁ።
በዚህ ቻናል👇👇👇
✔ ፎቶዎችን
✔ቪዲዮችን
✔መፅሐፍትዎችን
✔ታሪኮችን ታገኙበታላችሁ።👇👇
Http://Telegram.me/Bisrat_Midea
Http://tiktok/@bisratman20

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-13 20:27:46

ድንግል ሆይ

ድንግል ሆይ የኃጢአታችንን አጽር ቅጽር ታፈርሽልን ዘንድ እንታመንብሻለን፥ ድንግል ሆይ! የዕዳ በደላችንን ደብዳቤ በእጅሽ ትቀጅው ዘንድ እንታመንብሻለን፥ ድንግል ሆይ በንጽሕና ውሀ ሰውነታችንን ታጥቢልን ዘንድ እንታመንብሻለን፥ 
ድንግል ሆይ! በመከራችንንና በጭንቀታችን ጊዜ እንድትደርሽልን ድንግል ሆይ! እንታመንብሻለን፤

ለጠላቶቻችን አሳልፈሽ እንዳትሰጭን በጠላቶቻችንም እጅ እንዳትጥይን ድንግል እንታመንብሻለን፥ የሚጥለንን እንድትጥይው የሚቃረነንንም እንድትቃረኚው ድንግል ሆይ! እንታመንብሻለን፥ የሚበረታታብንን ልምሾ ታደርጊው ዘንድ የሚቃወመንንም ትቃወሚው ዘንድ ድንግል ሆይ! እንታመንብሻለን፥ ስንወጣ ስንግባ እንድትከተይን ስንቀመጥና ስንነሳም እንድትጠብቂን ጠንካራዪቱን አምባ መጠጊያ አንቺን የታመንሽቱን እንታመንብሻለን፥ አንቺን ተጠጋን ነፍሳችንንም በፊትሽ እንጥላለን፤

አንቺን ተጠጋን፥ እራሳችንንም በእጅሽ ሰጠን፥ ከንፈሮቻችንንም ለምስጋናሽ መሣሪያ አደረግን፥ የሚቃረነን ጠላታችን እንዳያገኘን የሰይጣንም ፈረሶች ሠረገላ እንዳይደርሱብን አንቺን ተጠጋን በአንቺም አመንን፥ ከመስጠም በሠራዊትም ከመከበብ ከርኩሳንም መናፍስት ወጥመድ እንድንድን አንቺን ተጠጋን፥ የመላእክተ ጽልመት ፍላፃ እንዳይነድፈን ከአመፀኞችም ጦር እንድንድን ልዩ ከሆነ ሰይፍም እንድንድን አንቺን ተጠጋን፥ የጽድቅንም መንገድ ከሚቃወሙ ሰዎች ወጥመድ እንድንድን አንቺን ተጠጋን፥ አንቺን አመንን፥ እኛን አገልጋዮችሽን አድኝን አሜን።

@Bisrat_Midea
@Keraniyomedhanialemgroup
75 viewsBisrat, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 20:21:29 ዛሬ ምሽት ከ2፣30 ጀምሮ የሚተላለፍ ቃለ መጠይቅ ከብጹዕ አባታችን አቡነ አብርሐም ጋር ማድረጉን EOTC TV ዘግቧል።

ብጹዕ አባታችን ለበርካታ ጥያቄዎቻችን መልስ ይሰጡናልና ኹላችንም እንከታተል።

የቪዲዮ ቅምሻውን በማየት ከምሽቱ 2፣30 ሰዓት ላይ የሚተላለፈውን ስርጭት እንድንከታተል ተጋብዘናል።

#ኢንፈርህ_ሞተ
#ሞትን_አንፈራውም

“እስከ ትበጽህ ለሞት ተበዓስ በእንተ ጽድቅ እስመ እግዚአብሔር አምላክከ ይትበአስ
በእንቲአከ”

“እስክትሞት ለእውነት ታገል። እግዚአብሔር ላንተ ይታገልለሀልና”

           ሲራክ 4 ፡ 2

ምዕመናን መረጃ ይደርሳቸውና ይነቁ ዘንድ ይሄን ሊንክ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ አድርሱ ቀላል የሚመስል ግን ብዙ ጥቅም አለው አድርጉት።

በዚ ግዜ ለዚያልሆንን መቼ ልንታዘዝ ነው። 

#share #share #share 

http://t.me/Bisrat_Midea
68 viewsBisrat, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 17:11:49 ይህም አባት ቴዎድሮስ በገድል የተጠመደ ሆነ መልኩም የሚያምር ነው በሰውነቱም ላይ ከውስጥ ማቅ በመልበስ በላዩ የብረት ልብስ መንቈር ይለብስ ነበር በቅንነቱና በትሕትናው ፍጹም ሆነ። በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ተመርጦ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ። የክርስቶስንም መንጋዎች በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ ሁልጊዜ መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸው ነበር ይልቁንም በሰንበትና በበዓላት ቀን።

የሹመቱም ዘመን ጸጥታና ሰላም ነበረ ቤተ ክርስቲያንም በሰላም ኖረች በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ላይ ዐሥራ አንድ ዓመት ተኩል ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_አብዱልማዎስ_ገዳማዊ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ገዳማዊው ጻድቁ አብዱልማዎስ አረፉ። ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ በበርሃ ሰው ሳያዩ ለ70 ዓመታት በቅድስና ኑረዋል:: በጊዜውም እግዚአብሔር አባ አብዱልማዎስን ወደ አባ ዕብሎይ ልኳቸው ነበር:: ሁለቱ ተገናኝተው አብረው ለ3 ቀናት ሲቆዩ ቅዱስ መልአክ እየተገለጸ አጽናንቷቸዋል:: ከሥውራን ማኅበርም ተቀላቅለው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለዋል::

አባ ዕብሎይ ሲያርፍ አንበሶች እያገዟቸው ቀብረዋቸዋል:: እርሳቸውም "እኔን የሚቀብረኝ ስጠኝ" ብለው ጸልየው ነበርና 3 ገዳማውያን መጥተውላቸዋል:: የካቲት 5 ቀን አባ ዕብሎይን ገንዘው ቀብረው በ3ኛው ቀን አርፈዋል::

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

@Bisrat_Midea
@Keraniyomedhanialemgroup
74 viewsBisrat, edited  14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 17:11:16 #የካቲት_7

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
የእስክንድርያ ሀገር አርባ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት #ቅዱስ_እለእስክንድሮስ አረፈ፣ የእስክንድርያ አርባ አምስተኛ ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት #ቅዱስ_ቴዎድሮስ አረፈ፣ ገዳማዊው ግብጻዊ ጻድቅ አብዱልማዎስ አረፉ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_እለ_እስክንድሮስ_ሊቀ_ዻዻሳት

የካቲት ሰባት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት እለእስክንድሮስ አረፈ፡፡ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ሦስተኛ ነው። ይህም አባት ታሮን በሚባል ገዳም መነኰሰ ትርጓሜውም የአባቶች ገዳም ማለት ነው በጌታችንም ፈቃድ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ እርሱ የተማረ አዋቂ ጻድቅ ሰው ነበረና።

በሹመቱ ወራትም ብዙ መከራ ደረሰበት የግብጽ ንጉሥ ልጁን ሹሞ በመንግሥቱ ላይ አሠለጠነው እርሱም በአስቄጥስ በረሀ ያለውን የመነኰሳቱን ገዳማት አፈረሳቸው። ከክፋቱና ከክህደቱ ብዛት የተነሣ ከምስር በስተሰሜን ወዳለች ገዳም ገብቶ በዚያ አምላክን የወለደች የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን አየና ይች ምንድን ናት አለ እርሷም በሽልማት ሁሉ የተሸለመችና ያጌጠች ናት በልብሶቿም ላይ ያማረ የሐር ልብስ ነበረ ስዎችም የክርስቶስ እናት የሆነች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ሥዕል ናት አሉት እርሱም ተሳድቦ የረከሰ ምራቁን በፊቷ ላይ ተፍቶ ደኅና ከሆንኩ ክርስቲያኖችን ፈጽሜ አጠፋቸዋለሁ አለ ዳግመኛም በክብር ባለቤት በጌታችን ክርስቶስ ላይ የስድብ ቃልን ተናገረ።

ሌሊትም በሆነ ጊዜ የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ታላቅ ራእይን አየ በነጋም ጊዜ ለአባቱ እንዲህ ብሎ ነገረው ዛሬ በዚች ሌሊት ታላቅ መከራና ብዙ ቅጣት ደረሰብኝ ታላቅ ዙፋንንም አየሁ በላዩ የተቀመጠበት ሰው እጅግ የሚያስፈራ የሚያስደነግጥ ነው ፊቱም ከፀሐይ ይበራል የብዙ ብዙ የሆኑ ሠራዊት የጦር መሣሪያ ይዘው በዙሪያው ቁመው ነበር እኔና አንተም እሥረኞች ሁነን በኋላው ቁመን ነበር እኔም በዙፋን ላይ የተቀመጠው ማነው ብዬ ጠየቅሁ ትላንት አንተ የዘበትክበት የክርስቲያን ንጉሥ ክርስቶስ ይህ ነው አሉኝ ከዚህም በኋላ የጦር መሣሪያ ከተሸከሙት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ ጐኔን በጦር ወጋኝ ጦሩንም ከጐኔ ውስጥ አላወጣውም።

አባቱም ሰምቶ ደነገጠ እጅግም አዘነ ያ ልጁም ወዲያውኑ ታመመ አንደበቱም ተዘግቶ በክፉ አሟሟት ሞተ። ዳግመኛም ከአርባ ቀን በኋላ አባቱ ሞተ። በርሱም ፈንታ ሌላ ንጉሥ ተሾመ እርሱም ክርስቲያኖችን እጅግ አሠቃያቸው ይህንንም አባት ሊቀ ጳጳሳት እለእስክንድሮስን አብዝቶ አሠቃየው ከሕዝቡ ሦስት ሺህ የወርቅ ዲናር ለምኖ እስከ ሰጠው ድረስ ጌታችንም ይህን ንጉሥ ፈጥኖ አጠፋው።

ከዚህም በኋላ አሁንም ሌላ ንጉሥ ተሾመ እርሱም ሊቀ ጳጳሳቱን ይዞ እንደ ቀድሞው ሦስት ሺህ የወርቅ ዲናር እንዲሰጠው ፈለገ እርሱም ከወገኖቼ እስከምለምን ታገሠኝ ብሎ ማለደው ንጉሡም ቀጠሮ ሰጠውና ይለምን ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ወጣ።

በተራራ ላይ አንድ ገዳማዊ ሰው ነበር ከእርሱም ጋር ሁለት ደቀ መዛሙርት አሉ በተራራውም በአንድ ቦታ እንዲቆፍሩና እንዲጠርጉ አዘዛቸው ወርቅን የተመላ አምስት ማሰሮ አገኙ አንዱን ሸሽገው አራቱን ወደ ገዳማዊ መምህራቸው አመጡ እርሱም ይረዳበት ዘንድ እንዲስጡት ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ላካቸው። እነርሱ ግን እነዚያን የወርቅ ማሰሮዎች ይዘው ተመልሰው ወደ ዓለም ገቡ የምንኵስና ልብሳቸውንም ጥለው ሚስት አገቡ በዚያም ወርቅ ወንዶችና ሴቶች ባሮችን እንስሳትንም ገዙ።

የዚያችም አገር አስተዳዳሪ ያዛቸው ገንዘብንም ከወዴት እንዳገኙ በመግረፍ መረመራቸው እነርሱም አምስት የወርቅ ማሰሮዎችን እንዳገኙ አመኑ መኰንኑም ለንጉሥ የጭፍራ አለቃ አሳልፎ ሰጣቸው እርሱም ወደ ንጉሥ አቀረባቸውና አምስት የወርቅ ማሰሮ እንዳገኙ አስረዳው ንጉሡም ጭፍሮቹን ልኮ የሊቀ ጳጳሳቱን ቤት በረበረ የአብያተ ክርስቲያናት ከሆነ ከንዋየ ቅድሳት ያገኘውን ሁሉ ወሰደ ሊቀ ጳጳሳቱንም አሠረውና ወርቅን የተመሉ አራቱን ማሰሮዎች ደግሞም ሦስቱን ሽህ የወርቅ ዲናር አምጣልኝ አለው እርሱም ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ገንዘብ ምንም ምን የለኝም አለው ወደ ሕዝቡ ልኮ ሦስቱን ሽህ የወርቅ ዲናር አምጥተውለት እስከ ሰጠው ድረስ አልተወውም ይህንንም ክፉ ንጉሥ ጌታችን አጠፉው።

ከዚህም በኋላ ከእርሱ የከፋ ሌላ ንጉሥ ተሾመ እርሱም የሐሰተኛውንና የርኵሱን ነቢይ ስም በከበረ መስቀል ፈንታ በእጆቻቸው ውስጥ እንዲአትሙ የክርስቲያንን ወገኖች አስገደዳቸው። ይችም ምልክት የመለኮትን ነገር የሚናገር ወንጌላዊ ዮሐንስ የተናገራት ትንቢት ናት ይህም ክፋ ንጉሥ ወደ ሀገሮች ሁሉ ይህን እንዲአደርጉ አዘዛቸው ሊቀ ጳጳሳቱንም እንዲሁ ያደርግ ዘንድ አዘዘው።

ሊቀ ጳጳሳትም ይተወው ዘንድ ብዙ ለመነው አልተቀበለውም ዳግመኛም እስከ ሦስት ቀን ይታገሠው ዘንድ ለመነው ከዚህም በኋላ ደግሞ እንዳይጥለውና ወደዚህ ወደረከሰ ሥራ እንዳያስገባው ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ማለደ ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በጥቂት ደዌ ጐበኘው ወደ ቤቱ እስክንድርያ ይሔድ ዘንድ እንዲአዝዝለት ንጉሡን ለመነው።

ንጉሡም ከለከለው ሰለ እጅ ኀትመት ምክንያት ለመፍጠር ሰለ መሰለው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገለጠለትና ነገ ታርፋለህ አለው እርሱም አርድእቱን እግዚአብሔር ነገ ስለሚጐበኘኝ አርፋለሁና መርከብን አዘጋጁ አላቸው። አንዳለውም በማግሥቱ አረፈ ሥጋውንም በመርከብ ተሸክመው ወስደው ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሥጋ ጋር ቀበሩት።

በዚህም አባት አለእስክንድሮስ ዘመን በግብጽ አገር ለሚኖሩ መለካውያን ስሙ አንስጣስዮስ የሚባል ሊቀ ጳጳሳት ነበራቸው ያዕቆባውያን ምእመናንን ይወዳቸዋል ስለዚህም ወገኖቹ መለካውያን ተጣሉት። እርሱም ነፍሱን ያድን ዘንድ አስቦ ወደዚህ አባት አለእስክንድሮስ መጥቶ ከሥልጣኑ በታች በመሆን የሚታዘዝ ሆነ እለእስክንድሮስም አንስጣስዮስን በእርሱ ፈንታ የሊቀ ጵጵስናውን ሥልጣን ይዞ መንጋውን ይመራ ዘንድ እርሱ ግን ከመነኰሳት እንዳንዱ ሁኖ በገዳም ይኖር ዘንድ እንዲተወው ለመነው።

አባ አንስጣስዮስም አልወደደም እንዲህም አለ ይህን የምሻ ከሆነ አኔ እስከ ዛሬ ሊቀ ጳጳሳት አልነበርኩምን ላንተ ደቀ መዝሙርህ ሁኜ ላገለግልህ ወደድኩ እንጂ አለ። በመካከላቸው ከተደረገው ከብዙ ልመና ከብዙ ምልልስም በኋላ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ አንስጣስዮስ ፈቀደ በአንዲትም ሀገር ላይ ኤጲስቆጶስነትን ሾመው። መንጋውንም እንደሚገባ በጎ አጠባበቅን ጠበቀ፡፡ አባት እለእስክንድሮስም በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር የኖረው ሃያ አራት ዓመት ከስድስት ወር ነው እግዚአብሔርንም አገለገለው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሊቀ_ጳጳሳት_ቴዎድሮስ

በዚህችም ዕለት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት ቴዎድሮስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አምስተኛ ነው። ይህም አባት መርዩጥ በሚባል አገር በአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ የዚያም ገዳም ስም ጠንቡራ ነው። ለአንድ ፍጹም ጻድቅ የሆነ ሽማግሌ ሰው ደቀ መዝሙሩ ሆነ። እርሱም ልጁ ቴዎድሮስ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና እንደሚሾም በመንፈስ ቅዱስ አይቶ ይህንን ለመነኰሳቱ ነገራቸው።
72 viewsBisrat, 14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 17:08:21 በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ለሁለትዮሽ ውይይት ሩሲያ /ሞስኮ/ መግባቱ ተገለፀ ።

በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ከብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ጋር ለመወያየት እና የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክትን ለማድረስና በሁለትዮሽ የአብያተ ክርስቲያናቱ ቀጣይ ግንኙነት ላይ ውይይት ለማድረግ ሞስኮ መግባቱ ነው የተገለፀው።

የልዑካን ቡድኑ አባላት የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጊዜያዊ እና ቋሚ ፕሮጀክቶች መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

@Bisrat_Midea
70 viewsBisrat, 14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 15:17:50 በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋይ ሥላሴ አካሉ የይቅርታ ደብዳቤ በአስገቡ ሰዓት "የተሾሙበትን" አስኬማና አልባሳትም አስረክበዋል።

"እውነትን ተረድተው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስተኛ ናት። ሌሎች በማወቅም ባለማወቅም የሄዳችሁ አሁንም ለመምጣት የተቸገራችሁ ቤተ ክርስቲያን በሯ ክፍት ነው::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

(ማኅበረ ቅዱሳን እንደዘገበው)

@Bisrat_Midea
@Keraniyomedhanialemgroup
92 viewsBisrat, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 15:11:50 #ሰበር_ዜና
፨፨፨፨፨፨፧፨ ፨፨፨፨፨፨
በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋይ ሥላሴ አካሉ በዛሬው ዕለት የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ።

ጥር 14 በሕገ ወጥ መንገድ በመሾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወገዙት መካከል አንደኛው ዛሬ የካቲት 5/2015 ዓ.ም የይቅርታ ደብዳቤ ለማስገባት ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደሚገኙ ሰምተናል።

@Bisrat_Midea
@Keraniyomedhanialemgroup
91 viewsBisrat, 12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 15:09:56 #ሰበር_ዜና

ጥር 14 በሕገ ወጥ መንገድ በመሾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወገዙት መካከል አንደኛው ዛሬ የካቲት 5/2015 ዓ.ም የይቅርታ ደብዳቤ አስገብተዋል

(ማኅበረ ቅዱሳን እንደዘገበው)

@Bisrat_Midea
@Keraniyomedhanialemgroup
89 viewsBisrat, 12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 22:25:44 የክርስቶስ ቤተሰቦች አባቶች እናቶች ወንድሞችና እህቶች እንደምን አመሻችሁ
የብፁዓን አባቶች አካሄድ በጣም ትዕግስትን ፥  ጥበብን መንፈሳዊትን የተሞላ ነው። የተሰጠን መግለጫም በዚያው መጠን ረቂቅ ነዉ። ለኛም  ለምዕመናን ግርታን ፈጥሮብን ይሆናል ግን ምሥጢሩ የረቀቀ ስለሆነና ብዙ ጥያቄ የባስ ከሚያስነሳ በሚል መሰለኝ እጥር ምጥን ያለ መግለጫ ነዉ የውጣው። ከመሸ ዛሬ በ04/06/15 ዓ.ም በማህበረ ቅዱሳን ቀጥታ ሥርጭት ግርታችንን ለመቀነስ በማስብ ይመስለኛል አቡነ ናትናኤል እና አቡነ አብርሀም ከጠ/ሚሩ ጋር የነበረውን ሰፊ ውይይት እንዲሁም ተጨማሪ መልዕክት አስተላልፈዋል እና ተከታተሉት እፎይታን ይሰጣል። ይህን መነሻ በማድረግ መሰለኝ አንድ አገናኝ ልዑክ እንደተቋቋመ ከላይ የጠቀስኳቸው አባቶች ተናግዋል፡:  ዛሬ መግለጫ የሰጡት የተወገዙት ሰዎችም  መግለጫቸው የተቀዛቀዘና የተደጋገመ ነበር።
እግዚአብሔር አምላክ ያሳየንን ሰላም ያለዉ ብርሃን አንድነት የቅ ቤተክርስቲያንን ልዕልና ያስፋልን

@Bisrat_Midea
@Keraniyomedhanialemgroup
111 viewsBisrat, 19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 22:20:25 እብሎይ ግን የቀድሞ ጸሎቱን አላቋረጠም እንዲህም እያለ እኔ ክፉ ባሪያ በየሰባቱ ሰባ ጊዜ በደልኩ ቸር ጌታ ሆይ መሐሪ አባት ሆይ ይቅር በለኝ የማይበድል ባሪያ የማይምር ጌታ የለምና። በዚችም ዕለት እስከ ሌሊቱ እኩሌታ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አደሩ እርሷም እሑድ ናት:: በዚያችም ጊዜ ከፊተኛው የሚበልጥ የሽቱ መዓዛ ሸተተ ገዳማዊውም ወንድሜ ዕብሎይ ና በውኃ ታጠብ ደስ ይበልህም በዚች ሰዓት ከተቀበልከው መከራ ታርፋለህና አለው:: በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለሁለቱም ቍርባኑን አቀበላቸው አባ ዕብሎይም አረፈ መላእክትም ነፍሱን ተሸክመው እስከ አርያም በረሩ።

ያ ገዳማዊም እኔ ሽማግሌ ነኝ ሥጋውን መሸከም አልችል የምቆፍርበትም የሌለኝ ምን አደርጋለሁ ብሎ የሚያስብ ሆነ በዚያንም ጊዜ ሁለት አንበሶች መጥተው ለሥጋው ሰገዱ መቃብሩንም ቆፍረው ሥጋውን እንደ ሰው ተሸክመው ወስደው ቀበሩት ገዳማዊውንም እጅ ነሱት እርሱም ባረካቸውና በሰላም ሔዱ።

ከዚህም በኋላ ያ ገዳማዊ የሚቀብረኝ አገኝ ይሆን ብሎ አሰበ ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ አትዘን ሥጋህን እኔ አስቀብራለሁ ያለ ሦስት ቀንም አልቀረህም ወዳንተም ሦስት ሰዎችን እልካለሁ የበግ ጠባቂው የአባ እብሎይን ገድል ንገራቸው እነርሱም ለሌሎች ይንገሩ ከእግዚአብሔር ምሕረት ተስፋ እንዳይቆርጡ በኃጢአት ለወደቁ አለኝታ ይሆን ዘንድ።

በማግሥቱም ሦስት ሰዎች መጡ እርሱም የበግ ጠባቂውን የአባ ዕብሎይን ተጋድሎ ነገራቸው እነርሱም እጅግ አድንቀው ጻፉት ከገዳማዊውም ዘንድ እስከ ሦስት ቀን ተቀመጡ ከዚህም በኋላ ገዳማዊው ተነሥቶ ጸለየ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ እነዚያ ሁለት አንበሶችም መጡ መቃብርንም ቆፍረው እንደ ሰው ወስደው ቀበሩትና ከእነዚያ ሦስት ሰዎች ጋር ተጓዙ ወደ አስቄጥስ ወደ አባ መቃርስ ገዳም እስከሚአደርሷቸው መርተው ወሰዱአቸው ሰዎቹም የሆነውን ሁሉ ለመነኰሳቱ ነገሩአቸው። እነርሱም እጅግ አደነቁ የበግ አርቢው የአባ ዕብሎይን ገድል ጻፉ ሁል ጊዜም በእሑድ ዕለት የሚያነቡት ሆኑ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አሞኒ

በዚህችም እለት ኢትዮጵያዊ የሆኑ ጻድቃን አቡነ አሞኒ የተወለዱበት በዓልና ለልጃቸው አቡነ ዮሐኒም መታሰቢያቸው ነው፡፡ አባታችን የካቲት5 ቀን አክሱም ውስጥ ሲወለዱ ሰይጣናት የወላጆታቸውን ቤት ከበው በማየታቸው እንደተወለዱ በእጃቸው ቢያመለክቱ በአንድ ጊዜ 60 ሰይጣናት ተሸንፈው እንጢስ በነው ጠፍተዋል። አሞኒ ማለት አሸናፊ ማለት ነው። አባ አሞኒ የራስ ፀጉራቸው ልብስ መጎናጸፊያ ሆኖቸው የኖሩ ታላቅና ቀደምት አባት ናቸው።

በደመና ተጭነው ኢየሩሳሌም ደብረ ዘይት ድረስ በመሄድ ከአባ ዕብሎይ ጋር ተገናኝተው ብዙ ምሥጢርን አውርተዋል። አባ ዮሐኒንያ ሳደጉት አስተምረው ያሳደጓቸው አባ አሞኒ ናቸው፡፡ የእናቱን ጡት ፈጽሞ ጠብቶ የማያውቀውን የመንፈስ ቅዱስ ልጃቸውን አባ ዮሐኒን እሳቸው እያጫወቱት የታዘዘ አሞራ በክንፎቹ እያለበሰው ቶራ (ሰሳ) እያጠባችው ነው ያደገው፡፡

አባ አሞኒ ልጃቸው አባ ዮሐኒ አድጎ 12 ዓመት ሲሆነው ከዚህም በኋላ ዲቁና ሊያሾሙትና አክሱም ጽዮን ወስደው ሊያስባርኩት ቤተ ካህናት ከተባለው ቦታ ይዘውት ሲሄዱ ልዩ ስሙ ሲሂታ ከሚባለው ቦታ ሲደርሱ ከወገባቸው በላይ እራቁታቸውን የሆኑ እንስራ የተሸከሙ ዐሥር ሴቶች አገኙ፡፡ አባ ዮሐኒም አባታቸውን "አባቴ እነዚህ ደረታቸው ላይ ቀንድ ያላቸው ጽጉራቸው የረዘመ ምንድን ናቸው? እንደ እኛ የሆኑ መስህታን የሚባሉት እነዚህ ናቸውን?" አሏቸው፡፡ አባ አሞኒም "አይደሉም ልጄ ዝም ብለህ ሂድ" አሏቸው፡፡ በኋላ ግን ትዝ ሲላቸው "በዱር እንስሳት ያሳደኩት ልጄ ወንድና ሴት ለይቶ ሲያውቅ በዚያው ሊሳሳት አይደልምን?" ብለው በማሰብ ዲቁናና ክህነቱ ይቅርበት ብለው ተመልሰው ወደ በዓታቸው ይዘውት ገቡ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ አበይዶ ወደ አባ አሞኒ መጣና እሳቸውን ከአባ ዮሐኒ ጋር እያገለገሏቸው ተቀመጡ፡፡ ዮሐኒ እየጻፈ አበይዶ የሚጻፍበትን ቆዳ እያዘጋጁ ሦስቱም በአንድነት በተጋድሎ መቀመጥ ጀመሩ፡፡

አባ ዮሐኒ ሃያ ዓመት አባ አሞኒ ደግሞ አርባ ዓመት በሆናቸው ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለአባ አሞኒ ተገለጠላቸውና "አሞኒ ሆይ ከእንግዲህስ እግዚአብሔር ወደኔ ና ብሎሃል" አላቸው። እሳቸውም ልጆቻቸውን አባ ዮሐኒንና አባ አበይዶን ጠርተው "በሉ እንግዲህ እኔ ወደ እግዚአብሔር መሄዴ ነውና ጸልዩልኝ" አሏቸው፡፡ ከማረፋቸውም በፊት አባ ዮሐኒን ለብቻቸው ጠርተው "አንተ አባ ዮሐኒ ካሁን በፊት ሲሂታ ላይ ያየሃቸው ሴቶች ናቸው፣ አዳምንም ከገነት ያስወጡ ናቸው፡፡ ወደፊትም እንደ እነርሱ ያለ የደረሰብህ እንደሆነ ካለህበት ገደል ተወርውረህ ውደቅመ በባሕር ውስጥ ጥለቅ" ብለው ነግረዋቸው ዕለት ኅዳር5 ቀን በሰላም ዐረፉና ወደ ጠራቸው እግዚአብሔር ሄዱ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት እና #መዝገበ_ቅዱሳን)
@Bisrat_Midea
106 viewsBisrat, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ