Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ!!! በምድር ካገኘሃቸውና ከምታገኛቸው ስጦታዎች ሁሉ እጂግ በጣም ድንቅ ና ግሩሙ ጊዜ አሁን | ሰዋስው/@zsewasw

ወዳጄ!!!

በምድር ካገኘሃቸውና ከምታገኛቸው ስጦታዎች ሁሉ እጂግ በጣም ድንቅ ና ግሩሙ ጊዜ አሁን ነው።
ትናንት እንዲህ ቢሆን ኑሮ፣አይ ትናንት እንዲህ በአደርግ ጥሩ ነበር።በማለት መጨነቅህን ማቆም አለብህ።ትናንት መኖር የሚችል ማንም የለም፣ትናንት ያለፈ ታሪክ ነው።ስለነገ ማንም የሚያውቅ የለም ምስጢራዊ ነው ስላዛ ያለህ ድንቅ ስጦታ ዛሬ ነው።ነገን ውብ ለማድረግ ዛሬን መጠቀም ግድ ነው።
መጽሐፍ የመዳን ጊዜ ትናንት፣ ነገ፣በኋላ አላለም የመዳን ቀን አሁን ነው።ያለን ድንቅ ስጦታ አሁን ብቻ ነው። በኋላ ምን ሊፈጠር እንደሚችል የሚያውቅ ሰው የለም።እናም ወዳጄ ልክ አንደ አንበሳ መኖር ከፈለክ አሁን ላይ ጀግና ሁን።በኋላ የሚባል ጊዜ የለም።

ድንቅ የአሁን ጊዜ ተመኘሁ።
አክሊል ዘሰዋስው
@zsewasw