Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ!! እጃችን ጫፍ ላይ ያለ መርዝ ወደ ሌላው የሰውነታችን ክፍል እንዳይሄድ ጨክነን እጃችንን | ሰዋስው/@zsewasw

ወዳጄ!!

እጃችን ጫፍ ላይ ያለ መርዝ ወደ ሌላው የሰውነታችን ክፍል እንዳይሄድ ጨክነን እጃችንን እንደምንቆርጠው በህይወታችንም ውስጥ መከራችንን የሚያስረዝሙብንን ኃጢአቶች መራቅ አለብን። አንዳንዴ በዙሪያችን ያሉ ጓደኞቻችን የስኬታችን እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ፣እነሱ ሳያውቁት እኛን ግን ወደኋላ እየጎተቱን ይሆናል። ከእራሳችን ጋር ያለው ኃጢአት፣ከስኬታችን ሊያስቀረን፣ወደ ምንናፈቀው የሕይወት ጎዳና፣የቅድስና መንገድ ሊያስቀረን ከተነሳ እኛም ያን ኃጢአት ቆርጠን መጣል አለብን፣አብርሃም አባታችን የአባቱን የጣዖት ምስል ይሸጥ የነበረ ሰው ነው፣ነገር ግን ወደ ሕይወት መንገድ የሚያደርሰው ስላልነበር ቆርጦ ጥሎ ወደ ሚናፍቀው ዘለዓለማዊ አባቱ ቤት ገባ።
ወዳጄ አንተስ በሕይወትህ ቆርጠህ ልትጥለው የሚገባ ከአባትህ ከእግዚአብሔር የለየህ፣ኃጢአት፣ ወደ ሕይወት ጎዳና እንዳትሄድ ያጠረህ፣አንዳች ልምድ የለም? ታዲያ መቼ ነው የምትቆርጠው?
ነገ፣በኋላ የሚባል ጊዜ የለም አሁን ነው።
ሐዋርያው እንደተናገረ የመዳን ቀን አሁን ነው።

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ ዲን አክሊል ዘሰዋስው
@zeswasw
@zsewasw
@zsewasw