Get Mystery Box with random crypto!

አሥራ ሁለቱ የወራት መጋቢዎች (የዞዲያክ) ከዋክብት በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊ ስያሜዎች እና ትርጓሜያ | ᗴᎢᕼᏆᝪ ᏃᝪᗞᏆᗩᑕ/ዞዳይክ

አሥራ ሁለቱ የወራት መጋቢዎች (የዞዲያክ) ከዋክብት በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊ ስያሜዎች እና ትርጓሜያቸው በተጨማሪም አስትሮሎጂ ጥንቁልና ነው?

፩ የሚዛን ኮከብ ( Llbera) ሚዛንቃሉ የግእዝ ሲሆን አማርኛዉም እንዳለ ቃሉን ወስዶታል በ0ረብኛም እልሚዛን ይለዋል። ትርጉሙም መድሎት፣ መመዘኛ ማለት ነው፣ ይህ በሚዛን የተሰየመ ኮከብ እንደ አቡሻክር ገለፃ መስከረም መጥቶ 30 ዕለት ከ10 ኬክሮስ የሚመግብ ነው። መልኩን ሚዛን አድርገው ቀዳሞት ኢትዮጵያውያን የማለበት ምክንያት በዚህ ወር በ11 ኛው ቀን መዓልቱና ዕለቱ የሚተካከልበት ወርህ ዕሪና (የመተካከል ወር) ነውና ከግብሩ የተነሣ ቅርፁ ሁሉን አንድ በሚያደርግ በሚያስተካክል በሚዛን ለመሳል ተችሏል ይላል።

፪ የ0ቅርብ ኮኮብ (Scorpio) ወቅራብ ቃሉ የግእዝሲሆን በዕብራይስጥ ወቅራብ፣ በሱርስት ዓቅርባ ፣ በሀረብኛ እልዐቅረብ ይለዋል ትርጉሙም ጊንጥ ማለት ነው በዚህ የተመስለ ይህ ኮኮብ እንደአቡሻህር ገለፆ ጥቅምት ወጥቶ 30 ዕለት ከ40 ኬክሮስ የሚመግብ ነው። በዚህ ጥቅምት ወር እንደ ንብረቱ ተነሥተው ህብረ ኮኮቡን የጊንጥ ኮኮብ ብለውታል።

፫ የቀውስ (የቀውጠ) (sagittarius) ሊቀ አለቃ ደስታ በመዝገበ ቃላታቸው ላይ :- በአማርኛ ቀመጡ የተባለው ይህ ኮከብ በዐረብኛ ቀውሲ እንደሚባል ገልፀው ትርጉሙም ቀስተኛ ማለት እንደሆነ ገልጸዋል። እንደ አቡሻህር ገለጻ መልኩ ቀስተኛ የሆነው በህዳር ወጥቶ 30 ዕለት ከ28 ኬክሮስ ይመግባል።

፬. የገዲ (ጀዲወይም ጀደይ) ኮኮብ(Capricorn) ፦ ታህሳስ መጥቶ 30ዕለት ከ20 ኬክሮስ የሚመግብ ሲሆን መልኩ የፍየል ጠቦት የሚመስልነው የጥንት ኢትዮጵያውያን የፍየል ቅርፅ የሰጡበት ምክንያት ፀሐይ በዚህ ወር የሚታዩትን ህብረተ ከዋክብት የሁለት ኮረብታ ጫፍ ላይ መውጣት ከሚያስደስተው ፍየል ጋር በማገፃፀር ይህ ህብረ ኮኮብ ባዱር ፍየል ቅርፅ አስቀምጠዉ የጊዲ (ጀዲ) ኮከብ capricorn ብለው ጠርተዋል።

፭ የደላዊ ኮከብ(Aquarius) :- ደለው የሚለው የግእዝ ቃል ሲሆን በአማርኛ ደላይ ሲባል ትርጒሙም ከጉድጓድ የዉሃ መቅጃ መጐተቻ ከእንጫት ከብረት የተበጀ ዕቃ ባልዲ ባለማንጠልጠያ ፣ ማህየብ (መቅጃ) ማለት ነው እንደአቡሻህር ገለፃ ይህ ኮኮብጥር መጥቶ 30 ዓለት ከ41 ኬክሮስ የሚመግብ ነው። የአባይ ወንዝ የሚፈሰስበት ጊዜ ነውና በዚህ ወር የሚመግበውን ህብረ ኮከብ የወንዙን መውረድ ለማመልከት የወራጅ ውሃ ከዋክብት ወይም ደለው በማለት የሚፈስ ወሃ መቅጃ የሚሆን የባልዲ ምልክት ሰጥተዋል።

፮ - የሑት ኮከብ ( Pisces ) ልክ እንደ ግእዙ ይህ ኮኮብ በዓረብኛ አልሑት ሲባል ፍቺው ዓሣ ሲሆን የግእዙ መነሻ(ሐመተ) እንደ ሆነ ሊቃውንት ይናገራሉ። ይህ ኮኮብ እንደ አቡሻህር ትንታኔ የካቲት ወጥቶ 30 ዕለት ከ10 ኬክሮስ የሚመግብ ሲሆን መልኩ ዓሣ ነው።

ይቀጥላል ነገ ሁላችሁም እስከዛ ላይክ እና ሼር በማድረግ ጠብቁን ስታነቡ ግን እንድታስተዉሉ የሚገባው እንጊሊዘኛ ስያሜው ለእናንተ እንዲያመች ነው የፃፍነው እንጂ የድሮ ኢትዮጲያውያን አልፃፉትም።
Share
CHANNEL
@zodiac_ethio
@zodiac_ethio

ሼር ኮከብ ቆጣሪ ቦት ▼
◉⇲
@kokeb_koteri_bot ⇲◉
◉⇲
@kokeb_koteri_bot‌‌

መወያያ ግሩፕ
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲