Get Mystery Box with random crypto!

አሥራ ሁለቱ የወራት መጋቢዎች (የዞዲያክ) ከዋክብት በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊ ስያሜዎች እና ትርጓሜያ | ᗴᎢᕼᏆᝪ ᏃᝪᗞᏆᗩᑕ/ዞዳይክ

አሥራ ሁለቱ የወራት መጋቢዎች (የዞዲያክ) ከዋክብት በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊ ስያሜዎች እና ትርጓሜያቸው በተጨማሪም አስትሮሎጂ ጥንቁልና ነው?

ክፍል፪

፯ የሐመል ኮኮብ(ኤሪስ)፦ ሐመል የሚለው ቃል "ሐሚል ሐሚሎት " ከሚባለው የግእዝ ንዑስ አንቀፅ የተገኘ ሲሆን ትርጒሙም" መዕነስ ፣ ማባብ፣ ማፍራት ፣ መሸከም " ማለት ነው በ0ረብኛውም እልሐመል ይለዋል ። በሀገራችን ''በመስከረም ስፍራው ኹሉ ለምለም እንደሚባል መጋቢትም እንደ መስከረም መርኃ ዕሪና ( የመተካከል ወራት ) ነውና ልክ እንደ መስከረም ቅጠቱ ልምላሜው ሳይቀር የፅንስ ጊዜን የሚያሳይ ነውና በመጋቢት መጥቶ 30 ዕለት ከ43 ኬክሮስ የሚመግበውን ኮከብ መልኩ እንስት በጎችን የሚያስረግዝ አውራ በግ አድርገው እንደ ስሙ ምስጢር የማስረገዝ የሚሸከም ምሳሌ አድርገውታል ይላሉ። በተጨማሪም የከበረ ዋጋ ያላቸው የበግና የፍየል ግልገል የሚወለዱበት ነውና ህብረ ኮከቡን የበግ ግልገል ወይም የሁለቱ ግልገሎች ከዋክብት ብለዉ ሠይመወቸዋል ::

፰ የሰውር (ተውር) ኮከብ ( Taurus ) ፦ "ሰውር"ቃሉ የግእዝ ሲሆን "ሶር" ማለት በሌ፣ አውራ ማለት ነው፤ በዐረብኛም "ሰውር " ይባላል፤ ሚያዝያ ወጥቶ ከፀሐይ ጋር 30 ዕለት ከ12 ኬክሮስ የሚመግብ ነው መልኩ እንደ ሥያሜው ሶር ( በሬ) ሆኖ ተስሏል:: በዚህ ወር በሬዎች ተጠምደው የሚያሱበት ነውና የዚህን ወር ህብረ ኮከብ የሰውር (የበሬ ወይም የኮርማ ) ከዋክብት ብለዋቸዋል።

፱ የገውዝ ኮከብ ( Gemini ) ፦ ውስጡ እንደሚበላው መንታነት እንዳለው የገውዝ ፍሬ የዚህ የገውዝ የግእዝ ፍቺውም "ዕጥፍ ፣ ጥንድ፣ መንታ፣ ሁለት "ማለት ነው ፤ ግንቦት መጥቶ ከፀሐይ ጋር 30 ዕለት ከ 30 ኬክሮስ የሚመግብ ኪሆን መላኩን በሥዕል ሲያዩት ጥንድ ባልና ሚስት (ጥንድ) ወይም ወንድና ሴት ይመስላል በዐረብኛም "እልጅውዛ" ይባላል።

፲ የሰርጣን (ሸርጣን) ኮከብ ( Cancer ) ፦ በግእዝ ስርጣን ፣ በዕብራይስጥ ሳርጣን ማለት ጐርምጥ ወይም የጐርምጥ ዓይነት ብዙ፣ እጅ እግር ያለው የባህር ተንቀሳቃሽ ፍጥነት ሲሆን 0ረቦች አቡ መቀስ በሰኔ ወጥቶ በ30 ዕለት ከ26 ኬክሮስ የሚመግብ ነው። በዚህ ወር ፀሐይ በዚህ ወር ፀሐይ በትሮፒክ ዞን የምትደርስበትና በዝግታ እንቅስቃሴ እያፈገፈች ስትሄድ እንድሸርጣን ወይም ጎርምጥ የምትመስል መሆኑን እንቅስቃሴዋን ለማመልከት የዚህ ወር ህብረ ኮኮብን የሸርጣን ቅርፅ ሰጥተዋቸዋል።

፲፩. የአሰድ ኮከብ ( Leo) ፦ ሊቁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በግእዝ መዝገበ ቃላታቸው ላይ "አሰድ"ማለት ትርጉሙ"አንበሳዊ፣አንበስ፣አንበሶ"ማለት እንደሆነ ሲገፅ በ0ረብኛም "እልአሰድ "ይባላል ይህ ኮከብ ከፀሃይ ጋር ሐምሌ ወጥቶ 30 ዕለት ከ10 ኬክሮስ የሚመግብ ሲሆን በአንበሳ አምሳል ይሳላል በዚህ ወር አራዊት ውሃ ለመጠጣት ከዱር ወጥተው በአባይ ዳርቻ የሚታዩበት ወር ነውና የወሩን ህብረ ኮከብ የአሰድ (የአንበሳ) ከዋክብት እንዳላቸው ይፅፋል።

፲፪. የሰንበላ ኮከብ ( Virgo) ፦ ሰንበል ወይም ሰንበልት ማለት በግእዝ ናርዶሳዊ የሆነ ጥሩሽቱ፣ ከዕፀወ ዕጣን አንዱ ነው፣ ዛጉል ወይም የባህር ሽቱ ይባላል በቅዱስ መፅሐፍና በሊቃውንት ድርሰት ይህ የሽቱ ዓይነት በብዛት ተጠቅሶ እናባለ በመሆኑም በዚህ የሽቶ ስም የተጠራው ከ0ሥራ ሁለቱ መናዝል አንድ የሆነው ይህ ኮኮብ ሽቱ ፣ የሸቱ ዛላ ተደርጎ ይሣላል፣ በግእዝ ሰንብላ የተባለው ይህ ኮኮብ በ0ረብኛ እንሰንቡለት ሲባል ከፀሐይ ጋር ነሐሴ ወጥቶ 30 ዕለት ከ42 ኬክሮስ የሚመግብ ነው ። ከዚህ ወር የደረሰውን ትኩስ ነዶ ይሰበስቡ ነበርና ህብረ ኮኮቡን የነዶ የክምር ወይም የእስት ዛላ ቅርፅ ( የመከር ድንግል) ቅርፅ በመስጠት ሠርተዋቸዋል።

ከላይ እንዳየነው በጥንት ዘመን የነበሩ ኢትዮጵያውያን እነዚህ በየወራቱ በሰማይ ላይ የሚታዩትን 12ቱን ህብረተ ከዋክብት በአባይ ዙሪያ የወሩን የአየር ንብረት ሁኔታ ለመጠቆም ሥዕላቸውን በመሃል ከዋክብትን ሲጠቀሙ ፣ የጥንት ግሪኮች ግን በፕላኔቶች ላይ እንዳደረጉት እነዚህ 12ቱን ህብረተ ከዋክብትን እስከ ማምላክና ለጣዖቶቻቸው እስከ መስጠት ደርሰዋል በዚህም ም\ክ ብዙ ሰዎች አስትሮሎጂ ጥንቁልና ነው የሚሉት ነገር ግን ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን በታሪኳ ለዘመን ቀመር፣ ሥራ ፍጥረትን ለመርዳት፣ ለምርምር ከመጠቀም ውጪ ፀሐይን፣ ጨረቃን ፣ ከዋክብትን አምልካ እንደማታወቅ ግልፅ ያለ ታሪኳና የዘመን አቆጣጠር ሥያሜዋ ሁሉ ያስረዳል።

አበቃን በሌሎች ወሳኝ ነገሮች እንመለሳለን እስከዛ ይሄን ፖስት Like እና ሼር በማድረግ ብዙዎች ጋር እንዲደርስ አድርጉ ::
Share
CHANNEL
@zodiac_ethio
@zodiac_ethio

ሼር ኮከብ ቆጣሪ ቦት ▼
◉⇲
@kokeb_koteri_bot ⇲◉
◉⇲
@kokeb_koteri_bot‌‌

መወያያ ግሩፕ
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲