Get Mystery Box with random crypto!

ከአጋራቸው ውጪ የሚመኙ ኮከቦች በእርግጥ ከፍቅረኛ ውጪ መሄድ እንደየሰው ባህሪና ሁኔታ የሚወሰን | ᗴᎢᕼᏆᝪ ᏃᝪᗞᏆᗩᑕ/ዞዳይክ

ከአጋራቸው ውጪ የሚመኙ ኮከቦች

በእርግጥ ከፍቅረኛ ውጪ መሄድ እንደየሰው ባህሪና ሁኔታ የሚወሰን ነው። በኮከቦች አይን ስንመዝነው ደግሞ በግንኙነት ውስጥ በሚፈጠር ስጋት፣ የሚፈልጉትን ባለማግኘት ወይም ከልብ ባለማመን ሰዎች ከፍቅር አጋሮቻቸው ውጪ ሌሎች ሰውችን ያማትራሉ/Cheat ያደርጋሉ። ለዚህ በጣም ተጋላጭ ናቸው የሚባሉትን ኮከቦች ከ
bestlive.com ጽሁፍ በመዋስ ከዚህ ቀደም በአምስተኝነት የተቀመጡትን ፓይሰሶች ገልጬ ቀሪዎቹን በይደር አቆይቼ ነበር። ተከታዩ እነሆ፦

5. ፓይሰስ
ፓይሲሶች በአጋራቸው ላይ የመደረብ/cheat የማድረግ እድላቸው በአምስተኝነት ያስቀምጣቸዋል። ምንም እንኳን ፓይሲሶች ስሜትን በመረዳት የተካኑና ስሜታቸውም ጥልቅ ቢሆንም በተወሰነ ደረጃ የሙድ መለዋወጥ ይስተዋልባቸዋል። በናንተ ከተበሳጩ በንዴት ጥለዋችሁ ምሽቱን በራሳቸው ለመደበቅ ሊወጡ የሚችሉ ናቸው።

በዚህ ወቅት ደግሞ ምሽቱን ምን ሊፈጠር እንደሚችል እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቸግራል። በርግጥ በዚህ ጽሁፍ ፓይሲሶች ምንም ያህል ቢጎዱ እንኳን ግንኙነቱን ጨርሶ በማቋረጥ ረገድ ግን ገፍተው እንደማይሄዱ አጽንዖት ሊሰጠው እንደሚገባ ይጠቁማል። ቀሪዎቹ ሶስቱን ደግሞ በቀጣይ የማካፍላችሁ ይሆናል።

4. አኳሪየስ
አኳሪየሶች በአካላዊ ሁኔታ ሌላ ሰው ጋር የመሄድ/cheat የማድረግ እድላቸው አናሳ ነው። ነገር ግን በስሜት ረገድ ወደቀደመ ፍቅራቸው ወይም ወደወደዱት በሀሳብ ሊጓዙ ይችላሉ። ይህንን በስሜት መንጎድ ሲሉ ያስቀምጡታል ጸሀፊያኑ፤ ከዚህ አንጻር አኳረያኖች ከአጋራቸው ውጪ ሌላ የመውደድ/ በስሜት በመሄድ ቃኝተው በአራተኝነት እንዲቀመጡ ሆኗል።

3. ሊብራ
ሊብራዎች በመማለል የታወቁ ናቸው አይነት አገላለጽ ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። ለዚህም ነው ብዙዎች ከሊብራዎች ጋር ግንኙነት ለመጀመር በመጀመሪያው ወቅቶች ሲያመነቱ የሚስተዋለው። ብዙ ጊዜ ይህን መሰል የሊብራዎች ስሜት ብዙ ርቆ ባይጓዝም በዚህ ጽሁፍ ግን በሶስተኝነት ተቀምጠዋል።

2. ሊዮ
ሊዮዎች የትኩረቱ ማዕከል እነርሱ እንዲሆኑ ሁልጊዜም ይሻሉ። እንደ ንጉስ ወይም ንግስት ካልወሰዳችኋቸው/treat ካላደረጋችኋቸው) ይህን መሰል ትኩረታችሁን ለማግኘት የማያደርጉት ነገር አይኖርም። በሌላ ሰው ለማስቀናት ከመሞከር ጀምሮ። ከዚህ አንጻር ሁለተኛውን ደረጃ ይዘዋል።

1. ጀሚናይ
ጀሚናዮች በግንኙነት ውስጥ ፍላጎታቸው ሰፋና በርከት ያለ ነው። ይህንን ፍላጎታቸውን ካልሞላችሁና የሚገባቸውን ትኩረት ካልሰጣችኋቸው ይህን ሊያሟላ ወደሚችል/ትችል ሰው ማቅናታቸው ብዙም የሚገርም አይሆንም። ስለዚህም ከአጋራቸው የሚፈልጉትን ካላገኙ ወደሌላ የመሄዳቸው/cheat የማድረጋቸው እድል የሰፋ ነው በሚል በመጀመሪያው ደረጃ ተቀምጠዋል።

Share
CHANNEL
@zodiac_ethio
@zodiac_ethio

ሼር ኮከብ ቆጣሪ ቦት ▼
◉⇲
@kokeb_koteri_bot ⇲◉
◉⇲
@kokeb_koteri_bot‌‌

መወያያ ግሩፕ
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲