Get Mystery Box with random crypto!

የምታምኑት ወይም የቅርቤ የምትሉት ሰው ሊክድዋቹህ ሲሉ የሚያሳይዋቸው15 ነጥቦች ክፍል3(የመጨረሻ | ᗴᎢᕼᏆᝪ ᏃᝪᗞᏆᗩᑕ/ዞዳይክ

የምታምኑት ወይም የቅርቤ የምትሉት ሰው ሊክድዋቹህ ሲሉ የሚያሳይዋቸው15 ነጥቦች

ክፍል3(የመጨረሻ ክፍል)

11. አስመሳይ አፍቃሪነት ፦አስመሳይ ሳቅና አስመሳይ ፍቅር ፣አስመሳይ አብሮ መሆን ለምሳሌ አዳም ገነት እያለ የተከለከለውን በለስ ሲበላ እና ከፈጣሪ መሸሽ ሲጀምር እግዚአብሔርም አዳምን ለምን ሸሸከኝ ሲለው አንተ የሰጠከኝ ሴት አሳስታኝ ነዉ እሷም ደግሞ በሌላ ማሳበብ ማለትም እኔ እወድዳለሁ እግዚአብሔር ግን ሄዋን ናት ያሳሳተኝ የማለት አስመሳይነት ባህሪ ያሳያሉ ወደ እኛ ስናመጣው እኔ እወድክ ነበረ እወድሽ ነበረ እኔ ታማኝ ነኝ ምናምን የሚሉ ከንቱ ዲስኩሮች እና ወሬዎች ሲያወሩ አስተውሉ ። በአጭሩ የወላዋይነት (የሚዋዥቅ) ባህሪ ፣ብልጭ ድርግም የሆነ ባህሪ ሲያሳዩ ውሸትና እውነት ሲደባለቅ ይሆ ሰውዬ ብሬን ሊክደኝ ነው ብላችሁ ሰውየውን አጥኑት እና ይሄን ስታጤኑ የምትወዱት እና ልታጡት የማትፈልጉት ሰው ከሆነ እሱ ከመካዱ በፊት ይሄን ብር ትቼልሀለሁ ማለት ጥሩ ነው እንደ Tip ይሄን ነገር ውሰዱ በቻላችሁት ሁኔታ ለሰው ብር አታበድሩ የምትወዱት ሰው ከሆነ ለምሳሌ 10,000 ብር ቢጠይቃቹ 1000 በነፃ ልስጥክ ሌላው ከሌላ ሰው ፈልግ ብላችሁ መስጠት ወይም አለማበደር በብር ዙሪያ የሚመጡ መካድን ልታስቀሩ ትችላላችሁ ።

12. ከፍተኛ ግጭት ፦ ለመካድ ወደ መጨረሻው አካባቢ ሲደርሱ የሚያሳዩት ባህሪ ነው በትንሽ ነገር መጋጨት መነጫነጭ ጥሉን ማክረር ይሄ ደግሞ ለቀጣዩ ደረጃ ግብዓት ይሆናቸዋል።

13. ጥልን ማራዘም ፦ ከላይ ባልናቹ መሰረት ኩርፊያን ማራዘም እና ሌሎችም እዚህ ላይ ማስተዋል ያለባችሁ ይሄ ሰው በብር ሊሆን ይችላል ወይም በፍቅር እና በቃል ኪዳኑ ሊክድ ሲያስብ የሚያደርገው ነገር ስንጠቃ ፣ የነገር ጉንጎና ፣ አቃቂር ማውጣት እና ያንን አምጥተው ከዚህ በፊት እንደዚህ ተናግረኸኛል እንደዚህ ብለኸኛል አድርገኸኛል እያሉ ጥል ማምጣት ሁላ ለጓደኞቻችሁ እንዲ ብለከኛል አድርገኸኛል እያሉ ጥል ማምጣት ሁላ ለጓደኞቹሁ እንዲ ብለከዋል የእናንተንም ለጓደኞቻቹሁ እየነገሩ ጥሉን መለጠጥ ሲጀምሩ ክህደት ሊፈፅም እንደሆነ መረዳት ይኖርባቸዋል እና ቆም ብላቹ አስቡ

14. እገዳ(Blocking)፦አብዛኛውን ነገር ብሎክ ወደ ማድረግ ይገባል ከዚህ በፊት እንደነገርናችሁ እናንተ ጋር ያሉትን መረጃዎች ፣ምስሎች ፣ዶክሜንቶች ፣ቁልፎች እናንተን የሚያገናኛችሁን ድልድዮች (Network) ስላፀዳ እናንተን ቢከዳ ምንም እንዳይጎዳ ስላደረገ እና አእምሮው ላይ ሁሉን ነገር ስለጨረሰ በቀጣይ የሚደረገው እናንተን Block ወደ ማድረግ ነው Facebook ላይ ሊሆን ይችላል ስልክ ስትደውሉ ሊሆን ይችላል ብሎ ሲያደርጉ ማለትም በአጭሩ እናንተ እና እነሱ መሃከል ትልቅ ግርግዳ ያቆማሉ ይሄ ሲሆን ሰውዬው እየካዳቹ እንደሆነ ማወቅ ይጠበቅባችዋል ።


15. በቃል ማፅናት፦ መጀመሪያ ላይ ስትገናኙ በቃል እንደተሰማማችሁት ሁሉ መጨረሻ ላይ በቃል ክህደቱን ያፀናዋል ማለት ነው :: ይሄም ማለት ገንዘብ ሰምታችሁኛል ለእኔ ከእኔ ጋር የፍቅር ግንኙነት የላቸውም በማለት በቃል ያፀኑታል ማለት ነው። ይሄ ሁሉ ሂደት ከመፈጠሩ በፊት ግን እናንተ ራሳችሁ የራሳችሁ የምትሉትን ሰዉ ከክህደት ማዳን ይኖርባችዋል ማለትም የሰው ልጅ የመጨረሻው ሃይሉ የቃል ሃይል አለው ማለትም መናፍስቶች መንፈስ ነው ያላቸው እንጂ የቃል ሃይል የላቸውም የሰው ልጅ ግን የቃል ሃይል አለው ይሄም የመጨረሻውን ነገር በቃል ሃይል ማፅናት ይችላል ማለት ነው። ይሄም ሲክዳችሁ አልሰጠከኝም አላውቅም በማለት ቢቃል ያፀናሉ ማለት ነው። የቃል ሃይል ስንል ምን ያክል ትልቅ ነገር እንደሆነ እናሳያችሁ በመፅሃፍ ቅዱስ እኛ እየሱስ ክርስቶስን ጌታችን እንደሆነ በልባችን አምነን ከዛ በአፍችን ስን ነገር ይላል እዚህ ላይ ስናይ የቃል ሃይል እንዳለ እንረዳለን ስለዚህ ክርስትና ማለት በልብ ያሰብከውን በአፍ መናገር ነው እስልምናም ማለት በልብ ያሰብከውን በአፍ መናገር ነው ሴጣንንም የሚያምኑ ሰዎች ሴጣንንም ሲያምኑ እንደዛው ነው ለምሳሌ አንታይክራይስት፣ኢሉሚናቲ ፣ፍሪማሰኖች እና ሌሎችም ሊሆኑ ይችላሉ በጠቅላላ የሚያደርጉት ከልባችሁ እግዚአብሔርን ከውስጣችሁ ካስወጣችሁ በኋላ በቃል እንድትናገሩ እና ቃለመሃላ እንድትፈፅሙ ያደርጉዋችዋል ያው በራሳቸው መፀሃፎች ላይ ይሄን በል ይባላል ወይም እግዚአብሔርን ካድ ይሉታል ያንን አስብለው በቃል እንዲፀና ያስደርጋሉ ማለት ነው ።እና ምን ለማለት ነው ይሄ ሁሉ ሂደቶች አልፎ በቃል እንዳያፀናው እናንተ ራሳችሁ ማድረግ ትችላላችሁ ማለትም ክህደት የሚመጣው በራሱ ብቻ የሚያመጣው አይደለም መናፍስቶችም ለእዚህ ያግዛሉ ዋናው ክህደትም የሚያመጣው ይሄ ነው የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር እና ከእርኩሳን በመናፍስት መሃል ብሎ የእምነት ሃይል ማለት የእግዚአብሔር ሃይል ሲሆን የክህደት ሃይል ደግሞ የእርኩስ መናፍስት ሃይል ስለሆነ ቅድም ባልናችሁተ

ደረጃዎች መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ሃይል ጋር ነበር ከዛ ወደ እርኩሳን መናፍስት መምረጥ ማለት ነው እና እንዳትካዱ እና ክህደት እንዳይፈፀምባችሁ ከፈለጋችሁ ይሄ ዘመን በእውቀት እና በማስተዋል ለማለፍ ይሄ ነገር ያስፈልጋቸዋል ብለን ስላሰብን አካፍለናችዋል። እዚህ ላይ ግን እንደማጠቃላይ አንድ ማሳስቢያ ይኖራል እሱምን አስረዳችዋለሁ አንድ ምግብ ለምሳሌ ድንች ቅቅልን ብንወስድ ለመቀቀል ስንል የምንመስዳቸው Step ይኖራሉ እና እነዛ ሁሉ Step ከተከሰተ ነው እንጂ ድንች ቅቅል የሚባለው እንጂ አንዱን step ብቻ ማለትም ከገበያ ድንች መግዛት፣ ውሃ መጣድ ወይም ሌሎቹን Step አንዱን ብቻ ስላረጋችሁ ድንች ቅቅል ልትሰሩ ነው ማለት እንዳልሆነው ሁሉ ከላይ ከዘረዘርንላችሁ step አንዱ ወይም ሁለቱን ስላያችሁም እየተካዳችሁ ነው ማለት ላይሆን ስለሚችል ነገሮችን ከላይ በነገርናችሁ አኳያ አንፃር ማጤን ይኖርባችዋል ብለን የአሁኑን ፖስት በእዚህ እናበቃለን በእዚህ ፅሁፍ ምንተሰማችሁ ከእዚህ በፊት የተካዳችሁ ካላችሁም ከፃፍነው ነገሮች እና ካጋጠማችሁ ነገር ጋር በማገናኘት የተሰማችሁን በኮሜንት አካፍሉን
Share
CHANNEL
@zodiac_ethio
@zodiac_ethio

ሼር ኮከብ ቆጣሪ ቦት ▼
◉⇲
@kokeb_koteri_bot ⇲◉
◉⇲
@kokeb_koteri_bot‌‌

መወያያ ግሩፕ
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲