Get Mystery Box with random crypto!

#ክፍል ሁለት እንደ ሳይንሱ ምርምር የዐስራ ሁለቱ የወራት መጋቢዎች የዞዲያክ ምልክቶች በየ | ᗴᎢᕼᏆᝪ ᏃᝪᗞᏆᗩᑕ/ዞዳይክ

#ክፍል ሁለት

እንደ ሳይንሱ ምርምር የዐስራ ሁለቱ የወራት መጋቢዎች የዞዲያክ ምልክቶች በየ 30 ዲግሪ ርቀት ላይ ይገኛሉ። ይህ ማለት ደግሞ እያንዳንዱ የዞዲያክ ምልክት ለአንድ ወር ያህል ይታያል ማለት ነው።

በእያንዳንዱ ወር ውስጥ ፀሐይ በአንድ የዞዲያክ ምልክት ውስጥ ትሆናለች። ለምሳሌ፦ ሐመል (ኤሪስ) የሚታይበት ወር ከመጋቢት12 - ሚያዚያ12 ብንል በነዚህ ወራት የዞዲያክ ምልክቱ(ኮከቡ) ቀን ላይ ፀሐይ በምትወጣበት ወቅት ከጀርባዋ አለ ማለት ነው። በቀን ላይ ደግሞ ከዋክብትን ማየት ስለማንችል ሐመል(ኤሪስን) በዚህ ወር ቀንም ሆነ ማታ ማየት አትችሉም ማለቴ አንችልም።

Note: ኤሪስን በማታ ማየት ምንችለው ኅዳር (November) ነው። ስለዚህ ኤሪሶች በዚህ ጊዜ ወታቹ ሰማይ ላይ ኮከባችሁን ማየት ትችላላቹ። ሌሎቻቹ ደሞ አታኩርፉ የናንተንም ይዤ ቀርባለሁ።

ሌላው ነገር ጨረቃም ሆነች ፕላኔቶች እንቅስቃሴአቸውን የሚያረጉት በ'ዞዲያክ' ክልል ውስጥ ነው። ከዚሁ ጋር ደግሞ የዞዲያክ ምልክቶች ከወቅቶች ጋር ሊዛመዱ ይችላሉ።



...............................................

#Next ስለ አራቱ ሊቃነ ከዋክብት( The Royal Stars) ስለሚባሉት ምንነት እና እነማን ናቸው ሚለውን ይዤላቹ ቀርባለው....
Share
CHANNEL
@zodiac_ethio
@zodiac_ethio

ሼር ኮከብ ቆጣሪ ቦት ▼
◉⇲ @kokeb_koteri_bot ⇲◉
◉⇲ @kokeb_koteri_bot‌‌

መወያያ ግሩፕ
◉⇲ @zodiac_group ◉⇲
◉⇲ @zodiac_group ◉⇲