Get Mystery Box with random crypto!

የምታምኑት ወይም የቅርቤ የምትሉት ሰው ሊክድዋቹህ ሲሉ የሚያሳይዋቸው15 ነጥቦች ክፍል2 4. | ᗴᎢᕼᏆᝪ ᏃᝪᗞᏆᗩᑕ/ዞዳይክ

የምታምኑት ወይም የቅርቤ የምትሉት ሰው ሊክድዋቹህ ሲሉ የሚያሳይዋቸው15 ነጥቦች

ክፍል2


4. ጥሪት መሰብሰብ ፦ ጥሪት መሰብሰብ ሲባል ምን ማለት ነው ? ከላይ እንደነገርናችሁ በገንዘብ፣ በንብረት ፣በስልክ ፖስዎርድ፣በቤት ቁልፍ፣ በደረሰኞችሊሆን ይችላል ወይም በሌላ ለእናንተ ከላይ የጠቀስናላችሁን ይሰጣችሁ የነበረ ሰው ቀስ በቀስ ያንን ማስቀረት ሲጀምር ማስተዋል ጀምሩ ይሄን ስንል ግን አንድ ሰው ገንዘቤን ወይም ሌላ ነገር ስጡኝ ስላለ እየካዳችሁ ነው ማለት ላይሆን ይችላል ግን እየዘረዘርንላችሁ ያለውን 15ቱን ፓኬጆች እያከታተለ ካመጣ የእዛኔ ግን መንቃት እና እየተካሄደ ያለውን ነገር ማጤን ይጠበቅባችኋል ።

5.ስዕል ጠረጋ :- በእናንተ እና በእነሱ አእምሮ ላይ ያለ ስዕል ይኖራል እነዚህን ስዕሎችን ማጥፋት ነው ለምሳሌ ሁሌ አብራችሁ የምትገናኙበት(የምትቀጣጠሩበትን) ቦታ መቀየር እዚህ ቦታ ይቅርብን ሌላ ቦታ እንሂድ ይላሉ ለረጅም ጊዜ አእምሮ ላይ የተሳለ ስዕል ማጥፋት በተጨማሪ ምሳሌዎች ላስረዳችሁ በየቀኑ ሁሌ 8 ሰዓት ላይ የምትገናኙት ከሆነ ወይም ሁሌ ማታ1 ሰዓት ወደ ቤት የሚገብ የነበሩት ሰዎች ማርፈድ አንዳንዴም መቅረት ካመጡ ስዕል ጠረጋ ላይ ናቸው ማለት ነው ። ስለዚህ በፍቅር ሊሆን ይችላል በቢዝነስ ሊሆን ይችላል ወይም በሌላ ነገር ላይ ያለንን ስዕል እየጠረጉ ሊሆን ስለሚችል በአስተውሎት መመልከት ጀምሩ።

6.ውሎ ቅየራ(ጓደኛ ቅየራ)፦ በአብዛኛው ከእናንተ ጋር በፍቅር ሊሆን ይችላል ወይም በቢዝነስ ጉዳያችሁ ሁለትዋችሁንም የሚያውቁዋችሁ ጓደኞቻችሁን መቀየር ማለትም ሌሎች ጓደኞችን መያዝ ያው መሰሎቻቸውን መምረጥ በሉት ለምሳሌ ከእዚህ በፊት የፈታ ጓደኛ ወይም ስለመፍታት ወሬ ሊነሱ የሚችሉ ሰዎች ጋር መሆን ይሄ ማለት አእምሮዋቸውን እያሳመኑ እና እናንተ ላይ ያለውን ስዕል ጠረጋ እና ድልድይ ሰበራ እና ሌሎቹንም ፓኬጆች ማድረግ እንደጀመሩ እወቁ። እዚህ ጋር ግን አንድ ሰው ጓደኛ ስለቀየረ ብቻ እየካዳችሁ ነው ማለት ላይሆን ይችላል ግን ከላይ ያልናችሁን እና ከታች የጠቀስንላችሁን ፓኬጆች ይዞ እየመጣ ከሆነ ግን ማስተዋል ጀምሩ።


7.ወሬ መረጣ(ወሬ ቅየራ):- ብዙ ጊዜ ገንዘብ ተጭበረበሩ፣እንትና እንደዚህ ሆነ ተፋቱ ምናምን የሚሉ ነገሮችን፣ ዜናዎችን ወይም ወሬዎችን መሳብ ሲጀምሩ።


8 ከመንፈሳዊነት መራቅ(መንፈስን መቀየር)፦ ከእዚህ በፊት መዝሙር ወይም መንዙማ አብራችሁ የምትሰሙ ከሆነ ፣ ቤተክርስቲያን ወይም መስኪድ የምትሄዱ ከሆነ በአጭሩ በጋራ የሆነ የምታደርጉት መንፈሳዊ ነገሮችን መተው ማለትም ከእዚህ በፊት የምትወዱትን መዝሙሮች አለመስማት ሲጀምሩ ። እንደውም ከላይ ስዕል ጠረጋ ላልነው ጠረጋ ነው አይደለም የሚለውን ለመለየት እንዲረዳችሁ ሁሌ ከእዚህ በፊት ወዳችሁ የምትሰሙትን መዝሙሮች ስትከፍቱ ቀይሩ ማለት ወይም ትተው መሄድ ከጀመሩ አስተውሉ። ከእዚህ በፊት እንዳልናችሁ ይሄን ብቻ ስላሳየን እየካዳችሁ ነው ማለት ላይሆን እንደሚችል ማወቅ አለባችሁ መሉ ፓኬጆቹን ግን ይዘው ከመጡ ግን ጠርጥሩ ወዳጆቼ።

9.ባህሪ ቅየራ፦ በአንዴ ከሰዋዊ ወደ አውሬአዊ ባህሪ ቅየራ ታያላችሁማለት ነው። አንዳንዴ እናንተን ከተቀራረቡ በኋላ እሱን ብክደው ፈጣሪ ይቅር አይለኝም ብለዉ በማሰብ የሌላቸውን ባህሪ ለእናንተ ሲሉ ባህሪያቸውን ሞዲፋይ ሊያደርጉ ይችላሉ እና ታማኝ ሊሆኑ ይችላሉ ወይም በተፈጥሮው ባህሪያቸው ታማኝ የሆኑ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ :: እናንተ ማስተዋል የሚጠበቅባችሁ ነገር ለእናንተ ብለው ሞዲፋያ ያደረጉትን ባህሪ Unmodified በማድረግ ሲቀይሩ ማየስተዋል። በተፈጥሮ ባህሪያቸው ታማኝ የሆኑ ደግሞ ወደ ተፈጥሮ ያልሆነው modifed ወደሆነ ባህሪ ሲመጡ ማለትም በግዴታ ሊሆን ይችላል ለምሳሌ የሆነ ብር ተበድረዋችሁ በተለያዩ ምክንያቶች መክፈል ሳይችሉ እና ከአቅማቸው በላይ ሲሆን ሰርቼ ሲኖረኝ እከፈለለሁ ብለው ሊክድዋችሁ ይችላል:: ሌላው ሞዲፋይ የተደረገ ባህሪ እንዴት ልናውቅ እንችላለን የሚል ሃሳብ ዉስጣችሁ ሊነሳ ይችላል ይሄን የምታውቁበት አሪፍ ዘዴ ደግሞ ከእናንተ ጋር ሆነው እንትናን እኮ ሸመጠጥኩት ካድኩት ምናምን የሚሉ ነገሮች ካወሩ ለእናንተ ብሎ ታማኝ እንደሆነ (ማለትም ባህሪውን ሞዲፋይ እንዳረገ በእዛ ማወቅ ትችላላችሁ ማለት ነው ::

10 መንደር ማጥቃት፦ በእናንተ ዙሪያ ያሉትን ጓደኞችን ማለትም በፍቅር ዙሪያ ሊሆን ይችላል በቢዝነስ፣ በብር ጉዳይ ወይም በሌሎች አብራችሁ እያላችሁ የሚያውቁዋችሁን ሰዎች ከመሬት ተነስተው እንትናን ጠልቼያታለሁ አትመቸኝም አይመቸኝም ማለት ከጀመሩ መንደራችሁን ማጥቃት እየጀመሩ እና ለመካድ በይበልጥ እየተንደረደሩ እንደሆነ ማስተዋል ይኖርባቸዋል።


አልጨረስንም በቀጣይ ሌሎቹን ደረጃዎች ይዘን እንመጣለን እስከዛ ግን ያላችሁን ሃሳብ አስተያየት ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን
Share
CHANNEL
@zodiac_ethio
@zodiac_ethio

ሼር ኮከብ ቆጣሪ ቦት ▼
◉⇲
@kokeb_koteri_bot ⇲◉
◉⇲
@kokeb_koteri_bot‌‌

መወያያ ግሩፕ
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲