Get Mystery Box with random crypto!

የምታምኑት ወይም የቅርቤ የምትሉት ሰው ሊክድዋቹህ ሲሉ የሚያሳይዋቸው15 ነጥቦች ክፍል1 ሳይኮ | ᗴᎢᕼᏆᝪ ᏃᝪᗞᏆᗩᑕ/ዞዳይክ

የምታምኑት ወይም የቅርቤ የምትሉት ሰው ሊክድዋቹህ ሲሉ የሚያሳይዋቸው15 ነጥቦች

ክፍል1


ሳይኮሎጂስቶች ከሚናገርዋቸው ምክሮች በመነሳት የምትወዱት ሰው ሊክድዎት ወይም ከመካዳቸው በፊት ከተቻለ በቶሎ ለማስቆም ካልተቻለ ደግሞ ራስን ከመጎዳት ለማዳን ይረዳል ብለን ነው ያዘጋጀነው ስለዚህ በአፅእኖት አንቡት። እዚህ ጋር ግን ማወቅ ያለባችሁ ነገር አንድ ወይም ሁለት ነገር ከዘረዘርነው ላይ ስላያችሁ የምትቀርቡት ሰው ሊክዳችሁ ነው ማለት ላይሆን ይችላል ይልቁንም የዘረዘርናቸውን ፓኬጆች እያከታተለ ይዞ ከመጣ ይሄኔ አስተውሉ ከታች ስታነቡ። ክህደት ስንል ልታውቁት የሚገባው ነገር አንድ ሰዉ ሊክዳችሁ ሲያስብ መጀመሪያ አእምሮ ላይ ነው የሚሰራው ማለትም በሂደት በልምምድ ነው። ክህደት ስንል በፍቅር ፣ በገንዘብ፣ በቃልወይም በሌሎች ነገሮች ሊከሰት ይችላል:: ሌላው ብዙ ሰዎች ሰው አላምንም ከዚህ በፊት የተጎዳሁት ይበቃል ሲሉ ሰምታችሁ ሊሆን ይችላል ያግን መፍትሄ አይደለም :: ከላይ የተነገውን መሠረት በማድረግ የቅርብየምትሉት ወዳጅ ፣ ጓደኛ ወይም ሌላ ከእናንተ ጋር ግንኙነት ያለው ሰዉ ወደ ክህደት ሲገቡ እንዴት ማወቅ ይቻላል የሚለውን 15ነጥቦች ከእዚህ በመቀጠል እናቀርባለን በትኩረት ተከታተሉን።

1. የፈሲታ ተቆጣታ :- ይሄ ማለት ምንም ነገር በሌለበት ያለምንም ምክንያት ሲጠረጥሩዋቸው ማለት ነው። ለምሳሌ፦ በጣም የምትወዱት ፣ የምትቀርቡት ወይም የምታከብሩት ሰዉ ከመሬት ተነስቶ በእዚህ ጉዳይ አላምናችሁም አጠረጥራችዋለሁ ካለ የመጀመሪያ ምልክት እያሳያችሁ ሊሆን ስለሚችል ነገሮችን በአስተውሎት ማየት ጀምሩ:: የመጀመሪያውን ሃሳብ ለመጠቅላል ያክል አንድ ሰው አጠረጥራችዋለሁ ሲል እናንተን እየጠረጠራችሁ ሳይሆን ራሱን ( እምሮውን ) እያሳመን መሆኑን እወቁ ም/ ክ እናንተማ ንፁህ ናችሁ ስለዛ ነው ።


2 የኩነኔ ስሜት ማጋባት፦ አንድ ሰዉ ብር ተበድሮ ለመካድ ሲያስብ መቼ ሰጠከኝ ብሎ ለመካድ ሲያስብ ያንን ከማለቱ በፊት በራሳችሁ ላይ ይሄንን ስሜት ማለትም ኩነኔው እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል ያው ከላይ በገንዘብ ጠቀስን እንጂ በሌሎችም ጉዳይ ሊሆን ይችላል :: እንዴት የኩነኔ ስሜት ሊፈጥርብን ይችላል የሚለውን በምሳሌ እንይ ፡- ሁሌ የሆነ ቦታ ስትቁጣጠሩ በጊዜ መጥቶ የሚያወቅ ሰው ሊሆን ይችላል ወይም በጊዜው የሚገኝ ሰውም ሊሆን ይችላል ብቻ ግን ሊክዳችሁ ያሰበ ሰሞን ከቀጠሮው ሰዓት ቀደም ብሎ በመገኘት ደውሎ ምንሆናችው ነው እየጠበቅኳችሁ እንዴት እንዲህ ታደርጋላችሁ ይላል ከዛም አልፎ ትንሽ ሰዓት ስታሳልፉ በዚህ ም/ክ በማድረግ የሌላ ጊዜ ቀጠሮዋችሁ ላይ ሊሆን ይችላል ወይም የእዛኑ ጊዜ ይቀራሉ ወይም ከቀጠሮው ቦታ በጌዜ ይዳሉ ከዛ በእናንተ በውስጣችው ማርፈድ አልነበረብኝም ማለት ነው የሚል የኩነኔ ስሜት እንዲሰማችሁ ያደርጋል ግን ማሰብ ያለባችሁ እናንተ አሁንም ንፁህ መሆናችሁን ነው ሰው ራሱ ሊክዳችሁ ሲያስቡ የሚያሳዩት ምልክት እንደሆነ ተረዱ ከላይ ሃሳቡ እንዲገባችሁ የመረጥነው ምሳሌ ጠቀስን እንጂ በሌላም ነገር ሊሆን ይችላል ሃሳቡን ብቻ እናንተ እንድታውቁ የሚገባው ነገር ሰው ሊክድዋችሁ ሲያስብ በሁለተኛ ደረጃ የሚያሳያችሁ ባህሪ ራሳችሁን ምንም በሌለበት ሁኔታ እንድትኮንኑ ለማድረግ ይጥራሉ ማለት ነው ።በአጭሩ በማንኛውም ነገር እና በእያንዳንዱ ነገር የኩነኔ ስሜት እንዲሰማችሁ ማድረግ ያደርጋሉ።



3ድልድይ ሰበራ፦ ድልድይ ሰበራ ማለት ደግሞ እናንተን ከእዛኛው ሰው ያስተሳሰራችሁን ነገር መስበር ነው ለምሳሌ ፦ በጋብቻ ውስጥ ልጆች ፣ ገንዘብ፣ ፍቅር ወይም ሌሎች የተሳሰራችሁበትን ጉዳይ ቀስ በቀስ ወደማናጋት እና ያስተሳሰራችሁን ነገሮች ( ድልድዮች ) መደ መስበር ይሄዳሉ ይሄ ሂደት ደግሞ በቀጥታ ወደ 4ተኛው ደረጃ ይወስዳችል ::


ይቀጥላል ቀጣዩ ነጥቦች በክፍል ሁለት ይዘን እንመጣለን እስከዛ ግን ምን ሃሳብ አላችሁ ኮሜንት ላይ ፃፉልን::
Share
CHANNEL
@zodiac_ethio
@zodiac_ethio

ሼር ኮከብ ቆጣሪ ቦት ▼
◉⇲
@kokeb_koteri_bot ⇲◉
◉⇲
@kokeb_koteri_bot‌‌

መወያያ ግሩፕ
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲