Get Mystery Box with random crypto!

፨ዞዳይኮች ልዩ ሚያረጋቸው ምንድነው? በአስትሮሎጂ የተቀመጡት ሁሉም ኮከቦች የየራሳቸው ምርጥ መለ | ᗴᎢᕼᏆᝪ ᏃᝪᗞᏆᗩᑕ/ዞዳይክ

፨ዞዳይኮች ልዩ ሚያረጋቸው ምንድነው?

በአስትሮሎጂ የተቀመጡት ሁሉም ኮከቦች የየራሳቸው ምርጥ መለያ አላቸው። ልዩ መለያቸው ባላቸው ባህርይ (የእሳት ፣ የንፋስ ፣ የመሬት ወይም የውሃ ባህርይ) ፣ በገዢ ፕላኔታቸው ተፅዕኖ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ይመሰረታል። ሁሉንም ኮከቦች ለየት የሚያደርጋቸው ምርጥ ነገር ምንድን ነው?
☆✧♡✧☆
_
1. Aries (ኤሪስ) ☞ ከፍተኛ ኃይልና ፍጥነት ያላቸው በመሆኑ የሚያከናውኑትን ድርጊት ቶሎ በመላመድ በቅልጥፍናና በከፍተኛ ተነሳሽነት መፈፀም ይችላሉ።
_
2. Taurus (ቶረስ) ☞ እጅግ በጣም እውነተኛ ከሆኑት ቶረሶች በላይ በየትኛው ኮከብ ላይ እውነትን ትፈልጋላችሁ? ለእውነት የሚኖሩ እንዲሁም ታማኝ ናቸው።
_
3. Gemini (ጄሚናይ) ☞ እነዚህ ኮከቦች ሁለገብ ናቸው። ማንኛውንም ነገር በማንኛውም ሁናቴ ውስጥ ሆነው ማከናወን ይችላሉ። በቶሎ ተግባቢ ፣ ጨዋታ አዋቂ እንዲሁም የአዕምሮ ልህቀታቸውም ከፍተኛ ነው።
_
4. Cancer (ካንሰር) ☞ ሰዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መረዳት የሚችሉና ሰዎች ምን እንዳሰቡ ጭምር በልባቸው መረዳት የሚያስችል ኃይል አላቸው። በእናትነት የሚመሰለው ይህ ኮከብ ለሰዎች በማሰብና የሚወዳቸውን ሰው በመንከባከብ ይታወቃል።
_
5. Leo (ሊዮ) ☞ የተፈጥሮ መሪነት የተሰጣቸው ሊዮዎች ከፍተኛ የሆነ የራስ መተማመን ያላቸው ከመሆናቸው በተጨማሪ የተለያየ ሀሳብ ያላቸውን ነገሮች አንድ የማድረግ ከፍተኛ ብቃት አላቸው። በአጠገባቸው ያሉት ሰዎች በጠቅላላ የአሸናፊነት ስሜት እንዲኖራቸው ያደርጋሉ።zz
_
6. Virgo (ቪርጎ) ☞ በእያንዳንዱ ድርጊት ላይ ጥቃቅን የሚባሉ ነገሮች ላይ እንኳን ትኩረታቸው ከፍተኛ ነው። የማቀናጀት ስራ በሚፈልጉ ነገሮች ላይ በጠቅላላ ከነሱ በላይ የሚመጥን አይኖርም።d
_
7. Libra (ሊብራ) ☞ እጅግ በጣም ደስተኛና ሚዛናዊ የሆነ ኑሮን ለመምራት የሚያስችል ስጦታ ተሰቷቸዋል። ይህን የተሰጣቸውንም ስጦታ በዙርያቸው ካሉ ሰዎች ጋር ሆነው ማጣጣምን ይፈልጋሉ።
_
8. Scorpio (ስኮርፒዮ) ☞ ታማኝነት ከምንም ነገር በላይ የነሱ መሰረት ነው። በታማኝነት ምንም ድርድር የማያውቁት ስኮርፒዮዎች ለቃላቸው ታምነው በመኖር የታማኝነት ምሳሌነታቸውን ያሳያሉ። በምትኩም ከሰዎች ታማኝነትን ይፈልጋሉ። ታማኝ ለሆነላቸው ሰው ከነሱ በላይ ምርጥ ጓደኛ አይኖርም።
_
9. Sagittarius (ሳጂታርየስ) ☞ ዓለምን የሚመለከቱበት የራሳቸው ዕይታ ያላቸው ሲሆኑ በልባቸው ያሰቡትን ነገር ለማሳካት ወደ ኋላ የሚጎትታቸው ምንም ነገር የለም። እስኪያሳኩት ድረስ!
_
10. Capricorn (ካፕሪኮርን) ☞ የሥራ ጉዳይ ሲነሳ ቀድሞ የሚነሳው ካፕሪኮርን ሲሆን በስራቸውም ሆነ በዕለት ዕለት ኑሯቸው ግብረገብ ያላቸው ናቸው። ከስህተት ለመማር ምንም የማያመነቱት ካፕሪኮርኖች ሥራና ሥነምግባር ትልቅ ቦታ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ያምናሉ።
_
11. Aquarius (አኳሪየስ) ☞ ለሰዎች የቆመ ኮከብ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ሰዎችን መርዳት በጣም የሚያስደስታቸው አኳሪየሶች ጥሩ ለውጥ የሚያመጡ ሀሳቦችንም በማመንጨት ይታወቃሉ።
_
12. Picses (ፓይሰስ) ☞ ከሰዎች ጋር በጥልቀት መግባባት የሚችሉና ሰዎችን መረዳት የሚፈልጉ ናቸው። ችግሮች ከመከሰታቸው አስቀድመው ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን የመተንበይ አቅም አላቸው። ፓይሰሶች ምርጥ ጓደኛም ሆነ የፍቅር አጋር መሆን የሚችሉ ናቸው።

#TIP ኮከቦቹ ሲታመሙ

ደም እያተፋቸው:"ባክህ ደና ነኝ" ...የሚሉን
ፓይሰስ
ቶረስ
ቪርጎ
ስኮርፒዮ
ካፒ

አንዴ ሲያስነጥሳቸው:"መሞቴ ነው በቃ!!" .. እያሉ ሚቀውጡት
ኤሪስ
ጃሚኒ
ካንሱ
ሊዮ
ሊብራ
ሳጁ
Share
CHANNEL
@zodiac_ethio
@zodiac_ethio

ሼር ኮከብ ቆጣሪ ቦት ▼
◉⇲
@kokeb_koteri_bot ⇲◉
◉⇲
@kokeb_koteri_bot‌‌

መወያያ ግሩፕ
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲
◉⇲
@zodiac_group ◉⇲