Get Mystery Box with random crypto!

🌙 ዝክረ ረመዳን مجالس شهر رمضان

የቴሌግራም ቻናል አርማ zkre_remedan — 🌙 ዝክረ ረመዳን مجالس شهر رمضان
የቴሌግራም ቻናል አርማ zkre_remedan — 🌙 ዝክረ ረመዳን مجالس شهر رمضان
የሰርጥ አድራሻ: @zkre_remedan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.87K

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-04-12 06:00:13 የሴት ልጅ ኢዕቲካፍ በተመለከተ

በመሰረቱ ሴት ልጅ ልክ እንደ ወንዶች ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች። በነቢዩ ዘመንና ከእሳቸው ህለፈትም በኃላ ሚስቶቻቸው ኢዕቲካፍ እድርገዋልና።

የተወሰኑ ሊቃውንት በመሰረቱ ሴት ልጅ ተገዳ ካልሆነ በስተቀር ከቤት መውጣቱ የተወገዘ ስለሆነ ኢዕቲካፍ ማድረጓም የተጠላ ይሆናል ሲሉ ሌሎች ደግሞ በእድሜ ከፍ ላሉ ሴቶች እንጂ ለወጣትና ታዳጊ ልጃገረዶች ኢዕቲካፍ አይቻልም የሚል አቋም አላቸው:: ከባሏ ጋር ከሆነ ትችላለች ካልሆነ አትችልም ያሉም አሉ።

ይህን ያሉት ወጣትና ታዳጊ ሴቶች በእድሜ ከገፉት ይልቅ ለፈተና ስለሚጋለጡ ወይም ወንዶችን ለፈተና ስለሚያጋልጡ ነው፤ በተለይ ኢዕቲካፍ ከቤት ውጪ ውሎ ማደርን ስለሚያስከትል።

ከዚህም አንጻር ሴት ልጅ ኢዕቲካፍ በማድረጓና ለኢዕቲካፍ ብላ ከቤት በመውጣቷ ምክንያት ከወንድ ጋር የምትቀላቀል ወይም ከወንድ ጋር ተገልላ የምትቀመጥ ከሆነ፣ እራሷ ፈተና ላይ የምትወድቅ፣ ወይም ሌሎችን ፈተና ላይ የምትጥል ከሆነ፣ ወይም ደግሞ ደህንነቷ በአስተማማኝ ሁኔታ የማይጠበቅ ከሆነ ከኢዕቲካፍ ትከለከላለች።

የባል ፈቃድ
ሴት ልጅ ባሏ ወይም ኃላፊዋ ከፈቀደላትና ሌሎች መስፈርቶች ከተሟሉ በኃላ ለደህንነቷ የማያሰጋ የትኛውም መስጂድ ላይ ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች። በባሏ ፈቃድ ኢዕቲካፍ የገባች ሴት ባሏ ኢእቲካፍ እንድታቋርጥ ከፈለገ ይችላል። ያለርሱ ፈቃዱ የምታደርገው ኢዕቲካፍም ትክክለኛ አይሆንም። ወንጀለኛ ከመሆን ጋር ኢዕቲካፉ ትክክል ይሆናል የሚል አቋም ያላቸው ሊቃውንት አሉ። ለሱንናህ ብሎ ግዴታ የሆነን የባል ሐቅን መጠበቅ መተውም አግባብ አይደለም፣ ለተጨማረ ዒባዳህ ብሎ ወንጀለኛ መሆን ብልህነት አይደለምና ሴት ልጅ ያለ ባሏ ፈቃድ ኢዕቲካፍ ልታደርግ አይገባም። ባለትዳር ያልሆነች | ሴትም ብትሆን በስሩ ያለችን አባቷንም (ወላጆቿን) ወይም ወንድሟን ሰታሳውቅና ሳታስፈቅድ ኢዕቲካፍ ልታደርግ አይገባም። ባልና ወላጆችም | በቂ ምክንያት ወይም ስጋት እስከሌላቸው ድረስ፣ የኢዕቲካፉ ቦታ ደህንነቱ  አስተማማኝ እስከሆነ ድረስና ቦታው ላይ እምነት ወይም ስነ-ምግባራቸው እንዲበላሽ የሚያደርግ ነገር መኖሩን እስካላረጋገጡ ድረስ ከመልካም ነገር ሊከለክሉ አይገባም። ባል ፈቅዶ ሚስት ሱንናህ የሆነን ኢዕቲካፍ ከጀመረች ኋላ ሀሳቡን ቀይሮ እንድትወጣ ቢያዛት እሺ የማለት ግዴታ አለባት። |  “በነዝር” (በስለት) ምክንያት ግዴታ የሆነ ኢዕቲካፍን ግን አስፈቅዳው ከጀመረች በኋላ | ሳትጨርስ ባሏ ማስቋረጥ አይችልም።

|ምንጭ፦ አል መጅሙዕ ሊን-ነወዊይ 8/4፣ አል-ኢትሓፍ 29

( ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚይያህ የሚከተለውን ብለዋል፤ "ሐይድ ላይ | ያለች ሴት ልድ አስገዳጅ ለሆኑ ነገሮች መስጂድ መግባት ትችላለች፤ ነገር ግን | ለመስገድና ለኢዕቲካፍ ብላ መግባት አትችልም፤የ “ነዝር” የስለት ኢዕቲካፍ እንኳ | ቢሆን፡፡ ኢዕቲካፍ ላይ ያለች ሴት ሐይዷ ከመጣ ከመስጂድ ወጥታ ግቢው ላይ ድንኳን ተጥሎላት እዛ ላይ ትቆያለች፤ … ሐይድ | ኢዕቲካፏን | አያበላሽም፤ ምክንያቱም እሷ ፈልጋ የምታደርገው ነገር ስላልሆነ፤ | ከመስጂድ ትውጣ የተባለው ለመስጂዱ ክብር ሲባል ነው ... ከመስጂዱ እንጂ ከኢዕቲካፉ አይደለም ምትከለከለው.. :: ይሁንና ከኣወዛጋቢ ነገሮች ለመራቅ ሲባል ሴቶች ሐይድ ላይ ሆነው ኢዕቲካፍ ባያደርጉ ይመረጣል።

|ምንጭ፦ አል-ሙሐላ 5/322፣ ተስሂሉል- ፊቅህ 1/594። 3 መጅሙዕ አል-ፈታዋ 26/210፣ አል-መጅሙዕ ሊን-ነወዊይ 8/44።


http://t.me/sultan_54
221 views03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 05:16:28 የተከበረውን ቁርኣን ሲያነቡ ለሚጨናነቁ ወይም ቶሎ ለሚሰላቹ ሰዎች መፍትሄ
ሸይኽ አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ይላሉ፦


መፍትሄው ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እንዲህ ሲሉ ይጠቁመናል፦
“ቁርኣንንም ባነበብህ ጊዜ እርጉም ከሆነው ሸይጧን በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ በእነዚያ ባመኑትና በጌታቸው ላይ በተመኩት ላይ ስልጣን የለውምና፡፡ ስልጣኑ በእነዚያ እርሱን በሚታዘዙት በእነዚያም  በእርሱ (ምክንያት)  ሽርክ በሚፈፅሙት ላይ ብቻ ነው፡፡” ( አነህል:98)

• ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ቁርኣንን ከማንበባችን በፊት ምን ማድረግ እንዳለብን መራን።

• አላህን የተረገመውን ሸይጣን ከእኛ እንዲያስወግደውና ከእኛ እንዲያርቀው ከአላህ ጥበቃ መሻት እንዳለብን።

· ቁርኣን ስትቀራ "ተደቡር" ማሰላሰል አለብህ፣ በማሰላሰል የምትቀራ ከሆነ፣ ይህ ነው የቀልብ ፍራቻ የሚያጎናጽፍህ እና የተከበረውን ቁርኣን እንድታነብ የሚያበረታታህ።

• እናም የሚያስጨንቅህ ነገር ሁሉ ሱራውን ማጠናቀቅ ወይም ጁዙን ማጠናቀቅ ወይም ይህን የመሰለ ነገር ብቻ አይሁን።

• ይልቁንም አላማህ ስለ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ አያዎች ባነበብከው ነገር ላይ ማስተዋል እና ማሰላሰል ነው።

• መልክተኛው (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) በሌሊት ሶላት ላይ ቁርኣን ያራዝሙ ነበር።  የረሕመት አንቀፅ አያልፉም፣ ቆም ብሎ አላህን ከምህረቱ ቢጠይቁ እንጂ ስለ አዛብ የሚናገር አያ ሲያጋጥማቸው፣ ቆም ብለው አላህን ከቅጣት እንዲጠብቃቸው ቢማፀኑ እንጂ። ይህ ሁሉ የሚያመለክተው መልክተኛው –የአላህ ሰላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና - በማሰላሰል እና ቀልባቸውን ጥደው ያነቡ እነደነበረ ነው።

|ምንጭ፡- አልሙንተቃ ሚን ፈታዋ አሽሸይኽ አልፈውዛን/የፈትዋ ቁጥር:22

http://t.me/sultan_54
203 views02:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 20:01:12 የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

"በረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርቱ ለሊት ጎዶሎ ቀናት ላይ ለይለቱልቀድርን ተጠባበቁ።"

ቡኻሪና ሙስሊም

𝕋𝕖:http://t.me/sultan_54
244 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 17:44:50 ዘካተል ፊጥር በገንዘብ ተተምኖ ማወጣት ያወገዙ ፉቀሃዎች ረሂመሁሙላህ

* ኢማሙ ማሊክ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ብለዋል፡-

{ለአንድ ሰውም የዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ ቢያወጣ ተቀባይነት የለውም፣ ደግሞም የነብዩ ﷺ ትእዛዝ አይደለም።}

አልሙደወነቱል ኩብራ ( 2/385)

══════❁✿❁═════


ኢማሙ አሽሻፊዒይ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦

“ዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ ማውጣት አያብቃቃም።”

❒ አል ኡም (2/72)

══════❁✿❁═════

* ኢማሙ አል ነዋዊ - አላህ ይዘንላቸውና - (ከታዋቂዎቹ ሻፊዒዮች አንዱ):*
*(አብዛኞቹ የፊቅህ ሊቃውንቶች ዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ ገንዘብ እንዲወጣ አልፈቀዱም)*ብለዋል።

❒ ሸርሑ ሙስሊም (7/60)

══════❁✿❁═════

* ኢማም አሕመድ - አላህ ይዘንላቸውና -
*(ዘካተል ፊጥር ዋጋውን ተምኖ በገንዘብ ለችገረኛ አይሰጠውም።”አሉ። በዚህን ግዜ እንዲህ ተባሉ፡- “ሰዎች፦ ዑመር ኢብኑ ዐብዱል ዐዚዝ  ዘካተል ፊጥርን በገንዘብ የሚሰጡ ሰዎችን ይቀበሉ ነበር። ይላሉ።” እሳቸውም፦
“የአላህ መልእክተኛ ﷺ የተናገሩትን ትተው እገሌ እንዲህ አለ ይላሉን?!” በማስከተልም፦
* ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ብለዋል፡- * (የአላህ መልእክተኛ ﷺ  ዘካተል ፊጥር በምግብ፣በእህል ሙስሊሞች ላይ ግዴታ አደረጉባቸው።) ብለዋል። አላህም እንዲህ አለ፡- (አላህን ታዘዙ መልእክተኛውንም ታዘዙ)*
* ሰዎች ግን እገሌ፣ እነእገሌ፣ አሉ፣ ተባለ እያሉ ሱናን ሲነገራቸው የነቢዩን ﷺ ንግግር ይመልሳሉ!!(ይተዋሉ)!!)* *

❒ አልሙግኒ (2/352)

══════❁✿❁═════



ኢማሙ ሻፊዒይ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-

“ከአላህ መልእክተኛ ﷺ የተረጋገጠ ሱና እርሱ ዘንድ የደረሰው ሰው በሙሉ፣ ለየትኛውም የሰው ንግግር  ብሎ (ሱናን) መተው እንደሌለበት ዑለማዎች በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።”

(አርሪሣላህ ገፅ 425)

http://t.me/sultan_54
249 views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 23:57:29
ረመዷን 13

    ከጾመኞች በላጩ

«فأفضلُ الصُوَّامِ، أكثرُهُم ذِكراً لله عزّ وجل في صَوْمِهِم».
“ከጾመኞቹ በላጩ፣ በጾማቸው ወቅት ኃያሉን አላህን አብዝተው የሚያወሱ ናቸው።”

       /ኢማም ኢብኑል ቀይም/
   [ الوابِلُ الصيِّب/ ص 153 ]



http://t.me/sultan_54
185 views20:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 08:49:46 ሙአዚኑ ለሰላተል ፈጅር  አዛን እያለ መብላት ወይም መጠጣት በሸሪዓ ሑክሙ (ፍርዱ) ምንድን ነው?

ፆመኛ ከእውነተኛው ጎህ መቀደድ አንስቶ ፀሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ፆምን ከሚያበላሹ ነገሮች መቆጠብ ግዴታ ነው። ይህ ማለት ጎህ ሲቀድ እንጂ “አዛን” አይደለም። ሀያሉ አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-
"የንጋት ነጭ ክር (ብርሃን) ከጥቁር ክር (ከሌሊት ጨለማ) የተለየ እስኪገለጽላችሁ ድረስ ብሉ ጠጡም።" (አል-በቀራህ 2፡187)
ስለሆነም አንድ ሰው እውነተኛው ጎህ እንደመጣ ሲያውቅ መብላትና መጠጣት ማቆም አለበት, በአፉ ውስጥ ምግብ ካለ መትፋት አለበት; ያንን ካላደረገ ጾሙን አበላሽቷል።

ሆኖም አንድ ሰው ፈጅር  መውጣቱን (ጎህ እንደ ወጣ) እርግጠኛ ካልሆነ እስኪያረጋግጥ ድረስ መብላት መጠጣት ይፈቀድለታል። ጊዜው ከመድረሱ በፊት ሙአዚኑ አዛን እንደሚል ካረጋገጠ ወይም አዛኑን በሰዓቱ ወይም በጊዜው ማለቱን እርግጠኛ ካልሆነ፡ እርግጠኛ እስኪሆን ድረስ መብላት ይችላል። ይሁንንና አዛኑን እንደሰማ ከመብላትና ከመጠጣት ቢታቀብ ተመራጭ ተግባር ነው።

አንዳንድ ሰዎች ቀጣዩን ሐዲስ እንደማስረጃ በማቅረብ አዛን እያለ የሚበሉና የሚጠጡ ሰዎች አሉ።
አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “ከእናንተ አንዳችሁ  ዕቃው(ኩባያው፣ምግቡ) በእጁ ላይ እንዳለ፣አዛን ቢሰማ እስኪጨርስ አያስቀምጠው።” (አህመድ 10251) (አቡ ዳውድ 2350 )አልባኒ በሶሂህ አቢ ዳውድ ሰሂህ ብለውታል።
ይሁንና ይህን ሐዲስ በተመለከተ ዑለማዎች ጎህ ሳይቀድ የሰላት ጥሪ የሚያደርግ ሙአዚንን የሚመለከት ነው ብለው ተርጉመውታል።

ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ)  የፈጅርን አዛን ሰምቶ እየበላና እየጠጣ የቀጠለ ሰው የፆሙ ፍርዱ ምንድን ነው? ተብለው ተጠየቀው ቀጣዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

" ሙእሚን ማድረግ ያለበት ፆምን ከሚያበላሹ፣ ከመብላትና ከመጠጣት ወዘተ ነገሮች መከልከል ይኖርበታል። ግዴታ ፆም ከሆሆነ ለምሳ፦ እንደ ረመዷን እና “ነዝር”ስለትን ለመሙላት የሚፆምህ መውጣቱ ካረጋገጠ ከምግብና ከመጠጥ እንዲሁም ፆምን ከሚያበላሹ ነገሮች መታቀብ አለበት።
ምክንያቱም አላህ በቁርኣኑ (ትርጉሙ ሲተረጉም) እንዲህ ይላል፡-
"የንጋት ነጭ ክር (ብርሃን) ከጥቁር ክር (ከሌሊት ጨለማ) የተለየ እስኪገለጽላችሁ ድረስ ብሉ ጠጡም።" (አል-በቀራህ 2፡187)

የፈጅር ሰላት ጥሪ መሆኑን ካወቀ መብላቱን ማቆም አለበት። ሙአዚኑ ጎህ ሳይቀድ አዛን የሚል መሆኑ ከታወቀ መብላቱን ማቆም የለበትም። ጎህ መውጣቱ እስኪገለጥለት ድረስ መብላትና መጠጣት ይፈቀድለታል።
ሙአዚኑ የሶላትን ጥሪ ከፈጅር በፊትም ሆነ በኋላ እንደሚል ካላወቀ አዛኑን ሲሰማ፤ መብላቱን ቢያቆም የተሻለ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።( ከተጠያቂነት የሚያድነውን ተግባር ፈፅሟል)። ነገር ግን በአዛን ጊዜ ቢጠጣ ወይም ቢበላ ምንም ችግር የለውም። ምክንያቱም ፈጅር እንደወጣ አያውቅምና።

እንደሚታወቀው የኤሌክትሪክ መብራት ባለባቸው ከተሞች ነዋሪዎቹ ፈጅር መውጣቱን ማወቅ ባይችሉም የአዛን ሰአትና ደቂቃን የታተመ የጊዜ ሰሌዳን መከተል እንደሚችሉ ይታወቃል።
ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቃል፡- “የሚጠራጠርህን ነገር ትተህ የማያጠራጥርህ ተግብር።” በሌላ ሀዲሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አጠራጣሪ ጉዳዮችን የራቀ ሰው ሃይማኖቱን  ክብሩን ጠብቋል።” አላህም የብርታት ምንጭ ነው!
(ፈትዋ ረመዳንያ፣ በአሽራፍ አብዱልመቅሱድ የተጠናቀረ፣ ገጽ 201)
ከላይ ለቀረበው ጥያቄ ምላሹ ሲጠቃለል እነሆ ፦ አንድ ሰው እውነተኛው ጎህ እንደመጣ ሲያውቅ መብላትና መጠጣት ማቆም አለበት, እና በአፉ ውስጥ ምግብ ካለ መትፋት አለበት; ያንን ካላደረገ ጾሙን አበላሽቷል።
አቡሁዘይፋ ሱለጧን ኸድር

  ቅዳሜ ረመዷን 03/ 1444 አ/ሂ
ወላሁ አዕለም!

https://t.me/sultan_54
156 views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 13:36:15 የዛሬው ጁምዓ ኹጥባ
المقصود الأعظم من الصيام

ከጾማችን ትልቁ ግብ ምንድ ነው የምናገኘው?

ረመዷን 02/1444 አ/ሂ

ነሲሓ መስጂድ የተደረገ ኹጥባ

https://t.me/sultan_54
233 views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 00:18:36 ረመዷን ሸህሩል ቁርኣን!

የኢማሙ አሽሻፊዒይ ተማሪ የሆኑት ረቢዕ ኢብኑ ሱለይማን እንዲህ ይላሉ፦

ኢማሙ ሻፊዒይ በአንድ ወር ውስጥ ሦስቴ ያኸትሙ ነበር ረመዳን ውስጥ ደግሞ ከሰላት ውጭ ብቻ ስልሳ ግዜ ያኸትሙ ነበር።”
[ሲፈቱ ሰፍዋ(2/255)]

https://telgram.me/zkre_remedan
382 views21:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 10:27:48 አዲስ ሙሓደራ

የጾም ግቦች


 ሐሙስ ሸዕባን 24/1444 አ/ሂ
ከመግሪብ እስከ ዒሻእ


አለም ባንክ ስልጤ ሰፈር ዓሊ መስጂድ የቀረበ



በሱልጧን ኸድር


https://t.me/sultan_54
228 views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 16:01:29 ከአቡ ሙሳ አል-አሽዓሪ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ﷺ  እንዲህ ብለዋል፡-
አላህ የሻዕባን አስራ አምስተኛው ሌሊት (ለየት ያለ  እይታ)አይቶ ሲያበቃ፣ከሙሽሪክ ወይም በሙስሊም ወንድሙ ላይ ጥላቻ (ኩርፊያ) ያለው ሰው ሲቀር፤ ፍጥረቱን ሁሉ ይምራል።”
(ኢብኑ ማጃህ እና ኢማሙ አሕመድ ዘግበውታል።)

ማሳሰቢያ፦ ① ሐዲሱ ከሰነድ አንፃር “ደዒፍ” ቢሆንም በተለያዩ ሰነዶች ተዘግቦ ስለመጣ ወደ “ሐሠን” ደረጃ ይደርሳል። ሐዲሱ ሐሠን ካሉት የዘመናችን ዑለማዎች መካከል ሸይኽ አልባኒ ይገኙበታል

ማሳሰቢያ፦ ②  በዚህ ለሊት ለየት ያለ ዒባዳ መስራት አይፈቀድም። ቢድዓ ነው። ከመልክተኛውም ﷺ ሆነ ከሰሓቦች ለሊቱን ለየት ባለ መልኩ ያሳልፉ እንደነበረ የመጣ አንድም ሰሒህ ማስረጃ የለም።

የአላህ መልክተኛ ﷺ  እንዲህ ብለዋል:–
“በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን የሰራ  ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት አይኖረውም)››
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

وخير الأمور السالفات على الهدى * وشر الأمور المحدثات البدائع


ከነገሮች ሁሉ በላ
ጩ የሰለፎችን መንገድ መከተል ነው። ከጉዳዮቹም በጣም መጥፎዎቹ አዲስ የተፈጠሩ(ቢድዓዎች) ናቸው።

ሙስሊሞች ሁሉ ሱ
ና አጥብቀው እንዲይዙ፣ በእሷም ላይ እንዲጸኑ እና ከርሷ የሚጻረር ነገር ሁሉ እንዲጠነቀቁ፣ አሏህ እንዲረዳን እንለምነዋለን እርሱ በጣም ለጋስ በጣም አዛኝ ነውና።


https://t.me/sultan_54
81 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ