Get Mystery Box with random crypto!

ዒድ ጁምዓ (ዓርብ) ዕለት ሲውል ሰላተል ዒድ እና የጁመዓ ሰላት ሁኔታ* የሳዉዲ ዓረብያ ቋሚ የፈ | 🌙 ዝክረ ረመዳን مجالس شهر رمضان

ዒድ ጁምዓ (ዓርብ) ዕለት ሲውል ሰላተል ዒድ እና የጁመዓ ሰላት ሁኔታ*

የሳዉዲ ዓረብያ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ በቁጥር  21,160 ባወጣው መግለጫ ተከታዮቹን ሀሳቦች ጠቅሷል።

1) ኢማሙ ሰላተል ጁምዓ እንዲሰገድ የማድረግ ግዴታ አለበት። ጁምዓ ለመስገድ በቂ ሰዉ ካልተገኘ ዙህርን ያሰግዳል።

2) ሰላተል ዒድ የሰገደ ሰው የጁምዓ ሰላትን ባይገኝ ይፈቀድለታል። ዙህርን በወቅቱ ይሰግዳል። ሆኖም ግን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ጁምዓን ቢሰግድ የተሻለ ነው።

3) የዒድን ሰላት ያልሰገደ ግን ይህ ፍቃድ አይመለከተዉም። ጁምዓን የመስገድ ግዴታ አለበት።

4) በዚህ እለት ጁምዓ በሚሰገድባቸዉ መስጂዶች ሲቀር የዙህር አዛን አይደረግም።


https://t.me/zkre_remedan