Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቢሎስ ሽንገላ/የሀጢአት ሽንገላ (ክፍል 1) 'የዲያቢሎስን ሽንገ | The words of eternal life

የዲያቢሎስ ሽንገላ/የሀጢአት ሽንገላ

(ክፍል 1)

"የዲያቢሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እን
ዲቻላችሁ የእግዚአብሄርን እቃ ጦር ሁሉ
ልበሱ" (ኤፌሶን 6፥11)

ሁላችንም እንደምናውቀው ሽንገላ ማ
ለት ምላስና ልብ አንደበትና ውስጥ ለየቅ
ል ሆነው አንደበት መልካምን ነገር ሲናገር
ልብ ተቃራኒውን ሌላ ነገር ወይም ሌላ አ
መለካከት ይይዛል። ሰይጣንም ለፈለገው
እኛን ከዘላለም ሩጫ የማሰናከል እቅዱን
ለማስፈፀም ከሚጠቀምበት መንገድ አን
ዱ ሽንገላ ነው። በአጠቃላይ ሽንገላ ማታ
ለል መሸወድ ነው! እግዚአብሄርም ከሚጸ
የፋቸው ነገሮች አንዱ ነው።

ዲያቢሎስ በዘመናችን እኛን አማኞች
ን በዋነኝነት በአንድ መንገድ እየሸነገለን ይገኛል! ተሳክቶለታልም!! የምድርን ብል
ጭልጭ ዛሬ ታይቶ የሚጠፋ ንዋይን ባለ
ጠግነትን እንድንጎመጅ አይምሮአችንን በ
ዚ ተቆጣጥሮታል! ይሳካልሀል ይሆንልሀ
ትበለጽጋለህ ትጠረምሳለህ ትወልዳለህ ትከብዳለህ የሚለው ስብከት ቤተክርስቲ
ያናችንን ሞልቷል ቢባል ውሸት አይሆንም
እነዚህ የገንዘብ አገልጋዮች በሽንገላ ነፍ
ሳትን ያታልላሉ "ስኬት ብቻ ከጌታ ጋር ሆ
ነህ ውድቀት የሚባል አያጋጥምህም" የ
ሚል የአልጋ በአልጋ ኑሮ ስብከትን በልዩ
ወንጌል መልክ ይሰብካሉ በእውኑ ቃሉ ከ
ዚህ ጋር ይስማማል?? እንደውም መስቀ
ሌን ተሸከሙ ይላል እንጂ ማነው እስኪ
በምቾት ጌታን ያገለገለ ቃሉን እንያ! ይሆን
ልሀል ይሳካልሀል የሚለው ስብከት የጠ
ላት ሽንገላ ነው ጠላት ከቻለ በስጋም በነ
ፍስም ሊጎዳህ አጥብቆ ይሻል ሁኔታዎች
ካልተመቻቹለት ደሞ ለስጋህ መሸንገያ እ
ና መደለያን በማጉረስ ጥቅማ ጥቅም በ
መስጠት ዋነኛ አላማው የሆነውን ዘላለ
ምህን ሊያስጥልህ ያለ የሌለ ሀይሉን መ
ጠቀም ይጀምራል ያን ጊዜ አንተ ነቃ በል
በቃሉ ራስህን አበርታ!

በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት
መባረክህን አጉልቶ ሳይነግርህ ማገልገል
እንደሚገባው መጠን ጌታን ሳያገለግል የ
አንተን ምድራዊ ችግር አስታኮ ሰበብ አር
ጎ የአንተ ዘመን ነው ትበለጽጋለህ በሚል
ህ አገልጋይ ውስጥ ጠላት የሽንገላን አን
ደበት እንዳስቀመጠ ያለጥርጥር እነግር
ሀለሁ!! ፍላጎትህ ስኬትም ከሆነ እንደእግ
ዚአብሄር ፈቃድና አላማ መሆን አለበት ስ
ኬት ሁሉ መልሚያህ አይምሰልህ መጥፊ
ያህም ሊሆን ይችላልና ስኬትን ለማግኘት
ብዙ ደክመህ ሊሆን ይችላል ግን ያለ ጌታ
ፈቃድ ስኬቱ ወደአንተ ቢመጣም የሰመረ
ህይወትን ማጣጣም አትችል ይሆናል።ስ
ለዚህ የእግዚአብሄርን ቀን ጠብቅ እንጂ ስኬት ለማግኘት ብለህ ባልተገባ መንገድ
አትሂድ አንተ ዘላለምህ የተሳካልህ ማን
ም ያልተሳካለት ነገር የተሳካልህ ማንም
ያላየውን ክብር ያየህ ጎረቤት የሰፈር ሰው
ያላየውን ያላመነ ያላየውን ሀይማኖተኛ ሀብታም ያላየውን የዘላለም ህይወት በክ
ርስቶስ ያገኘህ ስለሆንክ ብቻ በጌታ በጣ
ም ደስስስስ ሊልህ ይገባል እርግጥ ነው
ደሀ ከሰው በታች ሆነህ ሊሆን ይችላል ግ
ን ጠላት ደካማ ጎንህን ተጠቅሞ በሽንገላ
አታልሎ ጠልፎ እንዳይጥልህ መጀመሪያ
የቃሉን ጉልበት ታጠቅ!! አንተ በክርስቶስ
በሰማያዊ ስፍራ የተባረክ ዘላለማዊ ህይ
ወት ያለህ ከማንም በላይ ባለጠጋ ነህ!!!
ጠላት ነፍስህን አጥብቆ ሲፈልጋት የስጋ
ኑሮህን አመቻችቶ በትበለጽጋለህ ስብከት
እየሸነገለ አደንዝዞ አፍዝዞ ይጥልሀል!
ጠላት ኢየሱስን በምድራዊ ብልጥግና እ
ንደፈተነው አትዘንጋ!


በኢየሱስ ስም የዲያቢሎስ ሽንገላ እንዳ
ይጠልፈን የአንተን እቃ ጦር ሁሉ መጠቀ
ም መፈለግ እንድንጀምር ማስተዋልንና እ
ውቀትን እንድትሰጠን እጸልያለሁ!!

@ christology_GC

@astemiren

@zilivingword