Get Mystery Box with random crypto!

የሀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና የእግዚአ ብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱ ስ ጌታችን የዘላለም | The words of eternal life

የሀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና የእግዚአ
ብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱ
ስ ጌታችን የዘላለም ህይወት ነው። (ሮሜ
6፥23)
ሀጢአት የሚገባህን የስራህን የመተ
ላለፍህን ውጤት የዘላለምን ሞት ይሰጥ
ሀል ጸጋ ግን ባልተገባህ ነገር ላይ የልጅ
ነትን ስልጣን ይሰጥሀል! በማይገባህ ነገ
ር ላይ ይሾምሀል! ሀጢአት ፍርድን/ቅጣ
ትን ይዛ ትመጣለች ከእግዚአብሄር የሆነ
ው ጸጋ ግን ይቅርታን ምህረትን ይሰጥሀ
ል!

ሀጢአት ህጉንና ትእዛዛቱን አመካኝቶ
ይፈርድብሀል!ጸጋው ግን በክርስቶስ መስ
ዋእትነት አማካኝነት ከኩነኔ ነጻ ያወጣሀል
(ሮሜ8፥1) ሀጢአት ያለህን 9 መልካም ነ
ገር አይቆጥርልህም ይልቁንም በአንዷ ስ
ህተትህ ጽድቅን ያስቀርብሀል! በክርስቶ
ስ ያገኘኸው ጸጋ ግን የጎደለህን ጽድቅ በ
ኢየሱስ ይሞላልሀል! ይልቁንም ጭራሽ የ
ሌለህን ጽድቅ ይቆጥርልሀል!

ሀጢአት ከእግዚአብሄር ጋር ጠላት ያ
ደርግሀል! ጸጋው ግን በልጁ ደም ያስታር
ቅሀል! (ሮሜ5፥11) ሀጢአት በአንድ ሰው
ምክንያት ወደአለም ገባ ጸጋው ደግሞ በ
አንዱ በክርስቶስ ለአለሙ ሁሉ ተትረፈረፈ
(ሮሜ 5፥15) ሀጢአት ቀንበር ይጭናል!
የጌታችን ጸጋ ግን በነጻነት እንድትኖር ፈት
ቶ ይለቅሀል!(ግን ያለሀጢአት እንድትኖር)
(ገላትያ 5፥1)
ጢአት በደልን ይቆጥርብሀል! ጸጋ ግን
በኢየሱስ ደም በምህረት ያልፍሀል!(ግን
በመንፈስ ቅዱስ እየወቀሰህ) ጸጋ ይልቁን
ም ያልደከምክበትን የጌታን ስጦታ ወይ
ም ጸጋውን ያለብስሀል! ሀጢአት ከጌታ ያ
ርቃል ጸጋ ግን ወደኢየሱስ ያቀርባል!(ሮ
ሜ 5፥2)


ሀጢአት ለጨለማው ስልጣን አሳል
ፎ ይሰጥሀል! ጸጋ ግን ወደሚደነቀው ብ
ርሀን ወደ ኢየሱስ ያሻግርሀል! ሀጢአት ነ
ፍስህን ይገድላል! ጸጋ ግን ህይወትን ይሰ
ጥሀል! ሀጢአት የህሊና እረፍት ይነሳሀል!
ጸጋ ግን በክርስቶስ በተሰራልህ ስራ ሰላ
ምን እረፍትን ይሰጥሀል!(ሮሜ 5፥1-2)
ሀጢአት ለሀሰት አሰራር አሳልፎ ይሰጥሀ
ል ጸጋ ግን ወደ ወንጌል እውነት ይጠራሀ
ል(ገላትያ 1፥6)። ሀጢአት በስጋ የመሆን
ህ ውጤት ነው ጸጋ ግን በእግዚአብሄር
መንፈስ ህልውና ውስጥ እንዳለህ የሚ
መሰክር ማስረጃ ነው!!(ገላትያ 5፥17-22
) ሀጢአት ያለርህራሄ መቅጣትን ያውቅበ
ል ጸጋ ግን ከኢየሱስ ፍቅር የተነሳ ለምህረ
ትና ለይቅርታ ይቸኩላል!


@christology_GC
@christology_GC

@astemiren
@astemiren

@zilivingword
@zilivingword

መንፈሳዊ ተከታታይ ትምህርት መማርን
በጣም ስትፈልጉ ለነበራችሁ መልካም ዜ
ና አለኝ በinbox እንድታስተምረኝ ፈልጋ
ለሁ ብቻ በሉኝ የእግዚአብሄርን ቃል እንከ
ፋፈላለን! @wbinu @wbinu