Get Mystery Box with random crypto!

-የህያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል- ደካማ ጎን ሲጠፋብህ ጠንካራ ጎንህን እን | The words of eternal life

-የህያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል-


ደካማ ጎን ሲጠፋብህ ጠንካራ ጎንህን እን
ደ ደካማ ጎን በመቁጠር ጠላትህ ሊፈትን
ህ ቀዳዳ መፈለግ ይጀምራል ያንጊዜ በእ
ምነትና በተስፋ የማይሻገሩት የለምና ጉዞ
ህን ወደፊት በጽናት ተጓዝ!ጸሎትህን ጠላ
ት ባወጣው አዋጅ አትሻር! ዳንኤል ጠንካ
ራ ጎኑ መጸለይ ነበርና ለንጉሱ ዳርዮስ ከአ
ንተ ከንጉሱ በቀር ለ30 ቀን ለአምላኩ ማ
ንም ልመና እንዳያቀርብ ብለህ የማይለወ
ጥ የማይሻር ህግ አውጣ አሉት ህጉንም የሻረ በአንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል ተስ
ማሙ። ባሉት መሰረት ንጉሱ ህጉን አወ
ጣላቸው ዳንኤልም ይሄን በሰማ ጊዜ መ ጸለዩን አላቆመም ቀድሞም እንደሚያደር
ገው እንደወትሮው ጭራሽ መስኮቱን ከፍ
ቶ ይፀልይ ጀመረ። ጠላት ጦሩን በአንተ
ላይ ቢያሰልፍም ከአንተ ጋር ያለው ከሁ
ሉም ይበልጣልና ጠላትህ ከአምላክህ ጋ
ር እንዳትነጋገር ጸሎት እንድታቆም ቢፈት
ንህም ከታማኙ ጌታ ጋር የጀመርከውን ግ
ንኙነት አታቋርጥ! ውድቀት በጠላት የፈተ
ና ብዛት ሳይሆን በእግዚአብሄር ካለመተ
ማመን የሚመጣ ነው። በፈጣሪህ ላይ አ
ለመተማመን የውድቀት ውድቀት ነው!!

ጠላቶቹ በበረቱበት ጊዜ እሱም በአም
ላኩ ብርታትን ጨመረ እንጂ እጅ አልሰጠ
ም! መሳፍንቱ ሊጥሉት ባሰቡት ነገር እሱ
ጸንቶ ተገኘ! ምንም እንዳልተፈጠረ ያለስጋ
ት ሁሌም የሚያደርገውን ያደርጋል። በህ
ጉም መሰረት ንጉሱ የምታመልከው አም
ላክ ያድንህ ብሎ ወደአንበሶች ጉድጓድ
ጣለው። ንጉሱም በነጋታው ወደጉድጓዱ
ቀርቦ (ዳን.6፥20) ላይ የህያው አምላ
ክ ባርያ ዳንኤል ሆይ ሁልጊዜ የምታመል
ከው አምላክህ ከአንበሶች ያድንህ ዘንድ
ችሎአልን? አለው እሱም አምላኩ መላእ
ክቱን ልኮ የአንበሶቹን አፍ እንደዘጋ ነገረ
ው።

ንጉሱ ራሱ የዳንኤል አምላክ የዋዛ እንዳልሆነ ይገምታል ማለትም ምን አልባ
ት ከአንበሶች መንጋጋ ሊያስጥለው እንደ
ሚችል ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በከፊል ያ
ምናል ለዛም ነው አንበሶቹ ዳንኤልን በል
ተው ይጨርሳሉ በሚባልበት ጊዜ በነጋታ
ው መጥቶ አምላኩ እንዳዳነው የጠየቀ
ው "የህያው አምላክ ባሪያ" ብሎ ጠር
ቶታል። ስለዚህ የዳንኤልን አምላክ በህያ
ውነቱ አዳኝነቱ በጥቂቱም ቢሆን ይታመና
ል። (ቁ.23 ላይ በአምላኩ ታምኖ ነበርና
አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም ይላል) ንጉ
ሱም በመንግስቱ ግዛት ለሚኖሩት ህዝቦ
ች ሁሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ለዳንኤል አም
ላክ እንዲገዙና እንዲንቀጠቀጡ እሱ ህያ
ው አምላክ ግዛቱም እስከመጨረሻ የሚ
ኖር ነው ያድናል ይታደግማል ድንቅን ያደ
ርጋል ብሎ መሰከረ።በመጀመሪያ እምነቱ
ከአንበሶች አዳነው በዚ የተነሳ ንጉሱ የእ
ግዚአብሄር ሀይል ተገለጠለት እምነቱ በ
2 ነገሮች ውጤት አመጣ አንድም መዳን
ሌላው ደሞ የእግዚአብሄር ማዳን ለሰዎ ች ሁሉ መታወቅ ቻለ የተሰራው ስራ በአ
ለም ተመሰከረ። እምነት ራሳችንን ብቻ ሳይሆን
የሚያድነው የጸና እምነት ካለን አምላክ ለ
እኛ በሚሰራው ነገር ውስጥ ማዳኑን ለሰ
ዎች ሁሉ ይገልጣል! አምላክነቱን ዘላለማ
ዊነቱን በእኛ በኩል ለህዝብ ሁሉ ይገልጣ
ል።

ዳንኤል የአምላኩን ህግ ከማክበር ውጪ
ሌላ ምንም ደካማ ጎን አልተገኘበትም! በ
ኢየሱስ ስም እንደ ዳንኤል ስህተት ተፈል
ጎ የማይገኝብን አምላካችንን የምንፈራ በ
ጸሎት የተጋን ታማኝ አገልጋዮች ያድርገን



@zilivingword


@astemiren

@christology_GC