Get Mystery Box with random crypto!

ሽመልስ አብዲሳ > ብሎ የፎከረባቸው አዛውንቱ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ፥ ዛሬም ለ3ተኛ ቀን ረዥም ሰአት | ዘሪሁን ገሠሠ

ሽመልስ አብዲሳ << ሞቼ ነው ቆሜ የሚፈታው? አይደለም መፈታት ዋስትናም አያገኝም! >> ብሎ የፎከረባቸው አዛውንቱ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ፥ ዛሬም ለ3ተኛ ቀን ረዥም ሰአት የፈጀውን የመከላከያ ምስክር ሲያሰሙ ውለዋል!

በዛሬው ችሎት ፦

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር - ረ/ፕ/ር አበባው አያሌው
የትምህርት ሚኒስትር - ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ
የታሪክ ምሁሩ - ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም

በችሎት ቀርበው የምስክርነት ቃል የሰጡ ሲሆን ፣ ከዚህ ቀደም በነበሩት ሁለት ችሎቶች የቀድሞ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፣ ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ፥ ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ ሌሎች በርካቶች ቀርበው የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል!

ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ በአገዛዙ ጥርስ የተነከሰባቸውና የሀሳብ ነፃነት መብታቸውን ተጠቅመው በእውቀትና በሙያ ያገኙትን እውነታ በሚዲያ በማጋራታቸው ብሎም የስርአቱን አስከፊነትና ህገወጥ ተግባራት በይፋ በሀሳብ በመሞገታቸው ፣ በአንባገነኖቹ ይህ እንደወንጀልና አሸባሪነት ተቆጥሮ ፣ በርካታ የክስ ዶሴ ተከፍቶባቸው በወህኒ ቤት እየተሰቃዩ እንደሚገኙ የሚታወስ ነው!

ፍትህ ለጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱና በአንባገነኖች ወህኒ እየማቀቁ ለሚገኙ በቁጥር እጅግ በርካታ ለሆኑት የህሊና እስረኞች!