Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በ2023 በከፍተኛ ሁኔታ እየፈራረሱ ካሉ 12 የአለም ደካማ ሀገራት (fragile Stat | ዘሪሁን ገሠሠ

ኢትዮጵያ በ2023 በከፍተኛ ሁኔታ እየፈራረሱ ካሉ 12 የአለም ደካማ ሀገራት (fragile States) ተርታ ተመድባለች!

በየአመቱ ደካማ/የወደቀ (failed/fragile) መንግስት ያላቸውን ሀገራት መዝኖ በደረጃ የሚያስቀምጠው Fund for peace /FFP/ የተሰኘው አለምአቀፍ ተቋም እኤአ በ2023 አጠቃላይ የአለም ሀገራትን በተለያዩ መመዘኛዎች መዝኖ ደረጃቸውን አስቀምጧል ። በዚህም መሠረት እጅግ በጣም ከፍተኛ እና በጣም ከፍተኛ የወደቀና ደካማ መንግስት ካላቸው ሀገራት ተርታ ኢትዮጵያ ተካታለች።

እጅግ በጣም አስከፊ የመፍረስ አደጋ ውስጥ ከተካተቱት 12ቱ ሀገራት መካከል ወደ7 የሚሆኑት የአፍሪካ ሀገራት ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሱዳንና ሶማሊያ የምስራቅ ሀፍሪካ ሀገራቶች ናቸው።

ለግዛት መፈራረስ/ State Fragility ዋና ዋና ምክንያቶች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል፦ የአስተዳደር ድክመት/Weak governance ፤ የአስተዳደር አቅም ውስንነት (limited administrative capacity) ፤ ስር የሰደዱ ሰብአዊ ቀውሶች (chronic humanitarian crises) የማያቋርጡ ማኅበራዊ ውጥረቶች ( persistent social tensions) እና ብዙ ጊዜ ሁከት ወይም የትጥቅ ግጭት እና የእርስ በርስ ጦርነት (violence or the legacy of armed conflict and civil war) ከብዙ በጥቂቱ የሚገለፁ ናቸው።

የግዛት መፈራረስ/ State Fragility ምን ማለት ነው?

እንደ Fund for peace /FFP/ አገላለጽ ደካማ የሆኑና በመፈራረስ ላይ ያሉ ሀገራት በርካታ መገለጫ ባህሪያት ያሏቸውና በተለያዩ መንገዶች ሊገለፁ የሚችሉ ቢሆንም በጣም ከተለመዱት እየፈራረሱ ያሉ ሀገራት መገለጫ ባህሪያት መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ።

-የግዛቱን አካላዊ ቁጥጥር ማጣት ወይም በሕጋዊው የኃይል አጠቃቀም ላይ ያለው ጠቅላይነት / The loss of physical control of its territory or a monopoly on the legitimate use of force

-የጋራ ውሳኔዎችን ለመወሰን የህጋዊ ስልጣን መሸርሸር/ The erosion of legitimate authority to make collective decisions

-መሠረታዊ የህዝብ አገልግሎቶችን ለማቅረብ አለመቻል/ An inability to provide reasonable public services

-እንደ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሙሉ አባል ከሌሎች ሀገራት ጋር ጤናማና የተሳካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማድረግ አለመቻል/ The inability to interact with other states as a full member of the international community. ከብዙ በጥቂቱ የቀረቡ ማሳያዎች መሆናቸውን ይገልፃል።

Fund for peace /FFP/ የሀገራቱን ደረጃ ለመለየት በመመዘኛነት ከተጠቀማቸው 12 መለኪያ መስፈርቶች መካከል ፦ መጠነ ሰፊ የሙስና ወንጀልና የወንጀል ባህሪ ፤ የዜጎችን ሁለንተናዊ ድጋፍ ማጣትና ግብር መሰብሰብ አለመቻል ፣ የዜጎች ያለፍላጎትና በአስገዳጅ የጥቃት ሁኔታ መፈናቀል ፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት፣ በቡድን ላይ የተመሰረተ ኢ-ፍትሀዊነት ፣ ተቋማዊ ስደት/መፈናቀል ወይም መድልዎ ፣ ከባድ የስነ-ሕዝብ ጫናዎች ፣ አእምሯዊ ፍልሰት (brain drain) እና በተለያዩ ግዛቶች በተለያዩ ጊዜያት የሚፈፀሙ አሰቃቂና በጭካኔ የተሞሉ ወንጀሎችና ግጭቶች መበራከት የመሳሰሉት ይገኙበታል።

Fund for peace /FFP/ የልየታ ነጥብ መሠረት ከ100 ነጥብ በላይ ያገኙና እጅግ በጣም ከፍተኛና በጣም ከፍተኛ በሚል ደረጃ የተቀመጡት 12ቱ ሀገራት ፦ ሶማሊያ ፣ የመን ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ሶሪያ ፣ አፍጋኒስታን ፣ ሱዳን ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ፣ ቻድ ፣ ሀይቲ ፣ ኢትዮጵያ እና ማይናማር ናቸው።