Get Mystery Box with random crypto!

መከራ ውስጥ ያለ ሕዝብ ተስፋኛ ነው። አንድ ቀን የተጫነበት የመከራ ቀንበር እንደሚሰበር ተስፋ ያደ | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

መከራ ውስጥ ያለ ሕዝብ ተስፋኛ ነው። አንድ ቀን የተጫነበት የመከራ ቀንበር እንደሚሰበር ተስፋ ያደርጋል። በተስፈኝነቱ የተነሳ አማኝ ይሆናል።
'ከመከራ አወጣኻለሁ፥ መብትህን አስከብረዋለሁ' የሚልን ወሽካታ አምኖ ለመከተል አያመነታም።

መከራ ወለድ ተስፈኛነት ተንኮለኞችን አምኖ እንዲከተል ያደርጋል

ህዝባችን በስቃይ የሚልፍ ፥ በመከራ የሚፈተን ፥ ሰቆቃ ደጋግሞ የሚግበኘው ነው።
"አንድ ቀን ከዚህ መከራ አርነት እወጣለሁ" የሚል ተስፋ የመኖር ሃይልን ይሰጣል። ይኽ መልካም ቢሆንም በህዝቡ ተስፈኛነት የሚያተርፉ ነጋዴዎች ተፈጥረዋል። "ካላችሁባት ሰቆቃ ነፃ አወጣችኋለሁ" የሚሉ ጮሌዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው መንበር ላይ ወጥተዋል፥ ሃብትንም አጋብሰዋል።

የድሆች ችጋር ብልጣብልጦችን አበልፅጓል፥ የህሙማን ደዌ የቅንጦት መንገድን የጠረገላቸው አሉ፥ የሚስኪኖችን ረሃብ ታከው ለቁንጣን የተዳረጉ ጥቂት አይደሉም።

ለዚህ ሁሉ የሚዳርገው "አንድ ቀን ያልፍልኛል" የሚል ተስፈኝነት ነው።

የህዝቡ የችጋር ቀንበር ካልሰበረ በቀር መነገጃ መሆን አይቀርም።

እውቀት ወለድ ነፃነት የመጀሪያው የአርነት መንገድ ነው!

ተስፋበዓብ ተሾመ
@Tfanos
@Tfanos