Get Mystery Box with random crypto!

ኑሮና ጣዕም ሙያዬን ታውቃለህ፣ ማጀቴን ታያለህ፤ “እንጀራሽ እንክርዳድ፣ገበታሽ ጣዕም አልባ!” ለ | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

ኑሮና ጣዕም

ሙያዬን ታውቃለህ፣ ማጀቴን ታያለህ፤
“እንጀራሽ እንክርዳድ፣ገበታሽ ጣዕም አልባ!”
ለምን ትለኛለህ?

በል ዝም ብለህ ብላ!!
ቸርቻሪ መንግስታት፣
ሰነፍ ገበሬዎች፣
በዝባዥ ነጋዴዎች፣ በበዙባት ዓለም፤
ጠንካራ ጥርስ እንጂ ቀማሽ ምላስ የለም!

በረከት በላይነህ
@Zephilosophy