Get Mystery Box with random crypto!

የነቃ ሲመክር ውዶቼ! ተነሱ! ተነሱ! ተነሱ! በጠያቂ አቅም ነው የሚሰራው መልሱ፡፡ ከኮከቦች ር | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የነቃ ሲመክር

ውዶቼ!
ተነሱ! ተነሱ! ተነሱ!
በጠያቂ አቅም ነው የሚሰራው መልሱ፡፡

ከኮከቦች ርቀት፣
ከባህሮች ስፋት፣
ከአውሎ ንፋስ ጉልበት የተጠነሰሰ፤
የመገለጥ ወይን ከልቤ ፈሰሰ።
ከከፍታዎቼ፣ ከአደባባዮቼ ወስዶ ላይመልሰኝ፤
ከነፍሴ ተማክሮ ክንፌ ቀሰቀሰኝ።

ሰረገላው አይቆም፣ ነጂውም አይተኛ፤
ጥያቄም፣ ይቅርታም፣
ፀፀትም፣ ትዝብትም - ይልካል ወደእኛ፤
“ተጓዦቼን ሁሉ ምንድን አስተኛቸው?
እኔ መቆም አላውቅ -
           ወይኔ ረበሽኳቸው!” ይላል።

ዕረፍት የማያውቀው - ፈጣን ሰረገላ፣
መንቃት በማያውቁ- ተጓዦች ሲሞላ፤
የመገለጥ ወይን በአፍጢሙ ተደፋ፤
“ወራጅ አለ!” የሚል ተሳፋሪ ጠፋ።


ውዶቼ!
ተነሱ! ተነሱ! ተነሱ!
ግለጡ፣ ኀስሱ፣
ከጥያቄ ጅረት በጥራት ፍሰሱ፤
ሰፊ ጊዜ ስጡ ክንፍ ከነፍስያ እንዲወሳወሱ።
ጎዳናው፣ ሸለቆው፣
ጋራው፣ ሸንተረሩ - አዲስ ፊት እንዲያዩ፤
“ወራጅ አለ!” በሉ በየአደባባዩ።

ምንጭ -የመንፈስ ከፍታ
ደራሲ-ሩሚ
በረከት በላይነህ እንደተረጎመው!!

@Zephilosophy
@Zephilosophy