Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ትረካ እና አጫጭር ጽሑፎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ zeneser — መንፈሳዊ ትረካ እና አጫጭር ጽሑፎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ zeneser — መንፈሳዊ ትረካ እና አጫጭር ጽሑፎች
የሰርጥ አድራሻ: @zeneser
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.83K
የሰርጥ መግለጫ

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምሕሮን የጠበቁ
#መንፈሳዊ ጽሑፎች
#የአባቶች እና የእናቶች ንግግሮች እና ምክሮች
#የበገና መዝሙር
#ግጥም
#ትረካ
#ጥበባዊ ስራዎች
#የቅዱሳን ታሪክ በትረካ
ለሐሳብ አስተያየትዎ
@zeboanerges

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-21 15:58:21
https://www.facebook.com/100002638015444/posts/4775375352560351/?app=fbl
7.8K viewsHana Mariam Dagnew, 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 20:42:04 ++ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ++

ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ፊት በዚያች ምሽት በጭንቀት ቆመዋል፡፡ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሠጠኛል ብሎ ነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህ ተጨንቀዋል፡፡ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? እያሉ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ተራ በተራ ጠየቁት፡፡

የቀሩት ሊሸጠው ተስማምቶ የመጣው ይሁዳና ወንጌላዊው ዮሐንስ ናቸው፡፡ ይሁዳ እኔ እሆንን ማለቱ ልቡ እያወቀ ስለነበር ከዐሥሩ ጋር አብረን አንቆጥረውም፡፡ ዮሐንስ ደግሞ ለጌታ ካለው የፍቅር ጥልቀት የተነሣ እኔ እሸጠው ይሆን? የሚል ሥጋት ስላልነበረበት ‘’ጌታ ሆይ አሳልፎ የሚሠጥህ ማነው?’’ አለ እንጂ እኔ እሆንን አላለም፡፡ የሐዋርያቱ የጭንቀት ጥያቄ በማግሥቱ መልስ አግኝቷል፡፡ ሆኖም ይህንን ትሕትና የተሞላ ጥያቄያቸውን ለእኛ ሳይበጅ አይቀርም፡፡

በዙሪያችን ለተደረጉ ፣ ለሚደረጉ ክፉ ነገሮች ሁሉ ምክንያቱ ምንድር ነው? ጥፋቱ የማን ነው? መነሻው ምንድርን ነው? ብንባል ሁላችንም ጣት የምንቀስርበት ሰው አናጣም፡፡
አዳም ዕጸ በለስን ለመብላቱ ‘’ም ክን ያቴ ሔዋን ናት ‘’ አለ
ሔዋን ‘’ዕባብ አሳተኝ ‘ አለች
ዕባብም ጠያቂ ቢያገኝ ሰይጣን ማለቱ አይቀርም ነበር፡፡
አንዳቸውም ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ማለት አልቻሉም፡፡ እንደ ዳዊት ‘’እኔ መተላለፌን አውቃለሁ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊትህ ነው’’ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ለሚሆኑ ነገሮች ሁሉ የምንከስሰው ሰው አናጣም:: መፍትሔው ግን ራስን ማየት ነው:: "እስመ አዕይንቲሁ ለጠቢብ ዲበ ርእሱ" (የጠቢብ ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው) እንዲል

ቅዱሳን በምንም ነገር ራሳቸውን ይወቅሱ ነበር:: በገድላቸው ብዛት በሚጸልዩበት ሥፍራ ዶፍ ዝናብ እየወረደ ሳለ እርሳቸውን እንዳይነካቸው በቆሙበት ሥፍራ እንዳይዘንም ያደረገላቸው ዳግማዊው ኤልያስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያሉትን እናስታውስ:: በቆሙበት ሥፍራ ዝናም እንዳልዘነመ ሲያዩ "ይህችን መሬት በኃጢአቴ ዝናም አስከለከልኳት" ነበር ያሉት:: ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ይህም አይደል?

የሙሴ ወንድም አሮን በእስራኤል ግፊት ጣኦት ሠራ፡፡ ከወርቅ አቅልጦ ጥጃ አምላክ አድርጎ ሠራላቸው፡፡ ከሠራ በኋላም መሥዋዕት ለጣኦቱ አቀረበ፡፡
ሙሴ መጥቶ ሲቆጣ ሲያይ ግን አሮን ፈራና በሕዝቡ አሳበበ የራሱን ድርሻ በተመለከተ ግን እንዲህ አለ
‘ወርቅ ሰጡኝ በእሳት ላይ ጣልሁት ይህ ጥጃ ወጣ’ {ዘጸ 32፡24}
ራሱ ከእጃቸው ተቀብሎ በመቅረጫ ቀርጾ የሠራውን ጣኦት ‘ስጥለው ጥጃ ሆነ’ አለ፡፡ ራሱ ሕዝቡን ‘ስድ ለቅቋቸው’ የነበረ በመሆኑ ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ብሎ ራሱን ሊከስስ ይጠበቅበት ነበር፡፡

በትምህርት ቤት ሕይወታችን የማይረሱ ቀናት ግሬድ የሚለጠፉባቸው ቀናት ናቸው፡፡ ከብዙ የመታወቂያ ቁጥር መካከል ውጤቱን ያየ ተማሪ በዚያ የትምህርት ዓይነት A እንዳገኘ ሲያውቅ ለጓደኞቹ ‘’A አገኘሁ እኮ’’ ይላል፡፡ በተቃራኒው ‘F’ ያገኘ ከሆነ ‘’F ሠጠኝ’’ ይላል እንጂ ‘F አገኘሁ’ አይልም፡፡ A ከሆነ ያገኘው ተማሪው ነው ፤ F ከሆነ ግን በድክመቴ አገኘሁ ከማለት ይልቅ ጥፋቱ የመምህሩ ይሆናል፡፡ ነገሩን አልኩ እንጂ ሀገር ሰላም ብሎ የቆመ በር ጋር ስንጋጭም ‘በሩ መታኝ’ እንጂ መታሁት አንልም፡፡
እናም በሕይወታችን ለሆኑትና ለሚሆኑት ነገሮች ‘ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ትልቅ ጸሎት ነው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 20 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ
7.6K viewsHana Mariam Dagnew, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 18:55:31 እንዴት ናችሁ ወዳጆቼ
እንኳን ለታላቁ ዐቢይ ጾም አደረሳችሁ!
ሀላችንንም መፈረም ያለብን 'petition' ነው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችን የሚደርሰውን ግፍ
ለማስቆም ይህችን ቀላል ነገር እናድርጋት!

"እኔም ሞዐ ተዋሕዶ ነኝ"

https://moaorthodox.com/home/
12.3K viewsHana Mariam Dagnew, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-07 12:33:55 ለዳዊት ማን ነገረው?

መዝሙረ ዳዊት የመጨረሻው እንዲህ ሚል የሚገርም ንግግር አለ።

እንዲህ ይላል " መኑ ነገሮ ለእግዚእየ "

ለጌታየ ማን ነገረው? ማለት ነው።

የጌታስ የጌታ ነው ሁሉን የሚያውቅ ነውና

ነጋሪ አይፈልግም

አበው ምን ይላሉ ለዳዊት ማን ነገረው

ይህንን ሁሉ የልባችንን ልመና ለዳዊት

ማን ነገረው ደስ ሲለን

“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7

እያልን::

ስንፈራ:

መዝሙር 27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

² ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።

³ ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።

እያልን እንድንዘምር ለደስታችን

ለሐዘናችንም የልባችንን ለዳዊት ማን

ነገረው?

ስንበድል
“በፍጹም ልቤ ወደ ፊትህ ተማለልሁ፤ እንደ ቃልህ ማረኝ።”
— መዝሙር 119፥58

እያልን እንድንዘምር ለዳዊት ማን ነገረው?

ለቅዱስ ለልበ አምላክ ዳዊት ማን ነገረው?

መዝሙር 51
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።
² ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤
³ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።

እያልን ስለበደላችን እንድንጸልይ ማን ነገረው?

ለቅዱስ ዳዊት ማን ነገረው?

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
14.1K viewsHana Mariam Dagnew, edited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 08:21:01 ስንክሳር ዘወርኀ የካቲት
9.6K viewsHana Mariam Dagnew, 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 23:00:35 "ምንትኑ ያፈርሐኒ፣
ወትግርምተ መኑ ያደነግጸኒ፣
እንዘ ሰማዕት ጊዮርጊስ ሀሎከኒ፣"
9.1K viewsHana Mariam Dagnew, 20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 13:59:38 ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ

#በሐና ማርያም

@zeneser

ጥር 17፦

ዛሬ ደጉ ሐዋርያ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ የተጠራበት ዓመታዊ በዓሉ ነው።
9.6K viewsHana Mariam Dagnew, edited  10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 13:59:38 ጥር 17፦

ዛሬ ደጉ ሐዋርያ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ የተጠራበት ዓመታዊ በዓሉ ነው።
8.9K viewsHana Mariam Dagnew, edited  10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-22 10:35:32
የተመረጠች ድንግል እና ሰማዕት ቅድስት #ምኅራኤል ከተወዳጅ ወንድሟ #አባሖር ጋር

"" ሃብቷ : በረከቷ በዕለተ ዕረፍቷ ይድረሰን !! ""
ጥር14
ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn
8.9K viewsHana Mariam Dagnew, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ