Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመት ለሶስት ጎረቤት አገራት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ኤሌክትሪክ እንደምትሸ | Zena Nebab ✅

ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመት ለሶስት ጎረቤት አገራት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ኤሌክትሪክ እንደምትሸጥ አስታወቀች።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በድረገጹ ባወጣው መግለጫ ተቋሙ በሚቀጥለው ዓመት ከኃይል ኤክስፖርት ከ138 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዷል።
በተቋሙ የማርኬቲንግና ቢዝነሰ ደቨሎፕመንት መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚኒሊክ ጌታሁን እንዳሉት በተያዘው የበጀት ዓመት ለሱዳን፣ ለጅቡቲ እና ኬንያ ከ1 ነጥብ 63 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሠዓት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ 138 ነጥብ 25 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል፡፡
ገቢውን ለመሰብሰብ ለሱዳን 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሠዓት ኤሌክትሪክ በማቅረብ 55 ነጥብ 48 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለጅቡቲ 527 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሠዓት ኤሌክትሪክ በማቅረብ 34 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት መታሰቡንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
እስካሁን የኢነርጂ ኤክስፖርት ወዳልተጀመረበት ኬኒያ ወደ 695 ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብና 48 ነጥብ 65 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ዕቅድ መያዙንም ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ በኩል የኢትዮ- ኬንያ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመጠናቀቁና የኬንያም ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ታሳቢ ተደርጎ ከጥር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት ለማድረግ እቅድ ተይዟል ተብሏል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለኬንያ 695 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ 48 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በኬንያ በኩል እየተገነባ ያለው የኢትዮ- ኬንያ የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ግንባታ ባለመጠናቀቁ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ እንዳልተቻለ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ ከሦስቱ ሀገራት በተጨማሪ በቀጣይ ከሶማሌ ላንድ፣ ከታንዛኒያ እና ደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ለመፍጠር የሁለትዮሽ ግንኙነት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 71 የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ለመገንባት ማቀዷን መግለጿ የሚታወስ ነው።