Get Mystery Box with random crypto!

ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የፊታችን መስከረም 20 ድምፅ ይሰጣል ተባለ ሰኔ 14 ምር | Zena Nebab ✅

ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የፊታችን መስከረም 20 ድምፅ ይሰጣል ተባለ

ሰኔ 14 ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የፊታችን መስከረም 20 ድምፅ እንዲሰጥ መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ቦርዱ ምርጫ ባልተደረገባቸው ምርጫ ክልሎች ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ድምፅ መስጫ ቀኑ መወሰኑን አስታውቋል።
ሁሉም የቦርዱ አመራሮች በተገኙበት የምክክር መድረክ በቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ አማካኝነት ቦርዱ ሲሰራቸው የቆያቸው ስራዎች የተመለከተ ሪፓርት ለፓርቲዎች የቀረበ ሲሆን ቀጣዩን የምርጫ ሂደት ከአካባቢዎቹ አጠቃላይ ሰላምና ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ዝርዝር መረጃ ተሰጥቶ ውይይት ተደርጓል።
በዚህም ምርጫው በመጪው መስከረም 20ቀን 2014 ዓ/ም እንዲካሄድ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ድምፅ አሰጣጡ በሶማሌ፣ በሐረሪ ክልል እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የሚከናወን ሲሆን የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔም በተመሳሳይ ቀን መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ቦርዱ አስታውቋል።

አል ዐይን