Get Mystery Box with random crypto!

አፈ-ቁጥብ እና በተመሳሳይ ወቅት ደግሞ እጅግ አስቂኙ የቡድኑ አባል! ቤንጃሚን ዊሊያም ኋይት። እጅ | ዜና አርሰናል

አፈ-ቁጥብ እና በተመሳሳይ ወቅት ደግሞ እጅግ አስቂኙ የቡድኑ አባል! ቤንጃሚን ዊሊያም ኋይት። እጅግ የተደራጀው የዘንድሮ የተከላካይ መስመራችን አለኝታ ነው!!

የቱ ነው ዋንኛ መጫወቻ ስፍራዉ እስኪባል ድረስ ቤን ኋይት የትኛውም ዓይነት የመከላከል ግዳጅ ይስማማዋል። መሐል፣ ቀኝ ክንፍ፣ ግራ ክንፍ፣ ይባስ ብሎ የተከላካይ አማካይ ስፍራም መክሊቱ ነው።

አንድ ለአንድ የተቃራኒ አጥቂዎችን ሲገጥም አንገት ቀና የሚያደርግ ጥሩ ወረቀት አለው። ከዊሊያም ሳሊባ መመለስ በኃላ ወደ ቀኝ መስመር አዘንብሎ በወጥ ብቃት እያገለገለ ነው!

የሶስቱ አናብስቶች አለቃ ጋሬዝ ሳውዝጌት.. ዴክላን ራይስን ለሽምግልና እስኪሰደው ድረስ የቤን ኋይት የቀኝ መስመር ተከላካይነት ስፍራ አቋም ተገልጦ ታይቷል። የሊጉን ምርጥ የኋላ ደጀን የያዘው የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ አይተኬ አባል ነው።

ካልተወራላቸው ጀግኖች መሐል!!

አሹ

@ZENA_ARSENAL @ZENA_ARSENAL