Get Mystery Box with random crypto!

ስሜታችንን በማንደብቅ : ለእወነታው ዓለም የቀረብን : የእግርኳስ ድጋፍን በነጭ ቀይ ማለያ የታደል | ዜና አርሰናል

ስሜታችንን በማንደብቅ : ለእወነታው ዓለም የቀረብን : የእግርኳስ ድጋፍን በነጭ ቀይ ማለያ የታደልን ፣ በነቆራ ሀሜት ያልወደቅን ፣ የስኬትን ቁንጮ የምንፈልግ : የዛሬዋን ብቻ ሳይሆን የነጊቷን ብርሃን በመልካም ምንዛሬ የምንጠብቅ : ለአርሰናል እምነት ራሳችንን አሳልፈን የምንሰጥ የድጋፍ አለቶች ነን።

ስለንቀታቸው አባዜ ምንም ማለት አንፈልግም! ባልተገራ አንደበት ብትሰድቡን ችግራችን አይደለም ፣ ምላሻችን የልብ ቋንቋ የሆነው ፍቅራችን ነው። አሁን ብታደንቁን አንገርምም ቀድመን ከቦታው ተገኝተን ስሜቱን ስለምናውቀው። ታድያ ከእኛ ጋር የደስታ ጊዜን አታሳልፉ አላልንም ወንድምነታችሁ እና እህትነታችሁ ከላይ የመጣ የተፈጥሮ ገፀ በረከት ነውና! ወደ ሜዳው ተሰናድተን የአባቶቻችንን ታሪክ ያቀፈውን መድፍ ተሸክመን ስንገባ አላማችን ለአርሰናል መታገል ነው። ኑ አሁንም የደስታችን ተካፋይ ሁኑ ግን የነቆራ ሀሜታቹ ከማንነት ተግባራችሁ ስለሚበልጥ ያንን ማድረግ ሀጥያት ነው ሚመስላችሁ!

! ውድ የመድፈኛው አቢዮተኞች !

ያለፈውን ጊዜ በመጥፎ አሳልፋችሁ ይህንን ጊዜ በደስታ የልብ ፈገግታችሁን በንፁ አንደበታችሁ የለገሳችሁን ፣ መወደቅ መነሳት ብርቃችን አይደለም ብላችሁ ያጠነከራችሁን ፣ በሰሜን ለንደኑ ቀበጥ ዝማሬ ውስጥ የጥበብ አንድማታን በአንበተ ርቱነት እያስደመጣችሁን ፣ ከድጋፍ እስከ ህይወት መስዋት ለአርሰናል ፍቅር እራሳችሁን አሳልፋችሁ የሰጣችሁ ፣ የምትወዱን  የምንወዳችሁ ፣ የምታፈቅሩን የምናፈቅራችሁ ፣ ኖራችሁ የምታኖሩን ፣ በፍቅራችሁ ያሳወራችሁን ፣ በሜዳ ላይ ሀ ሁ አቦጊዳን እንደ አዲስ እያስተማራችሁን ፣ የስታሚና ጥንካሬያችንን ከፍ ያደረጋችሁ ፣ ከአንደበት እስከ ተግባር ፅድቀት አርሰናልን መርጣችሁ በጥሞና በሜዳ ላይ ተውኔት የተዝናናችሁ ፣ የመድፈኛው ዓለም የውበት ገፅታዎች... !

" North London Forever, Whatever The Weather, These Streets Are Oun Own, And My Heart Will Leave You Never, My Blood With Forever, Run Through The Stone "

Still we die for Assena

( ደረሰ ንጉሴ )

@ZENA_ARSENAL
@ZENA_ARSENAL