Get Mystery Box with random crypto!

ሜትለንድ-ናይልስ ወደ ሳውዝሃምፕተን ሊያቀና ነው የአርሰናል የቀኝ መስመር ተመላላሽ የሆነው ኤንስ | ዜና አርሰናል

ሜትለንድ-ናይልስ ወደ ሳውዝሃምፕተን ሊያቀና ነው

የአርሰናል የቀኝ መስመር ተመላላሽ የሆነው ኤንስሊ ሜትለንድ-ናይልስ ይህንን የውድድር አመት በውሰት በሳውዝሃምፕተን ለማሳለፍ እንደተዘጋጀ የፋብሪዚዮ ሮማኖ መረጃ ያመላክታል።

የ25 አመቱ ወጣት ከአርሰናል ጋር እስከ 2024 ድረስ የሚያቆየውን ኮንትራት እንደሚፈርም የሚጠበቅ ሲሆን ሳውዝሃምፕተን ደግሞ የውሰት ውሉ ላይ የመግዛት አማራጭ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል።

ሜትለንድ-ናይልስ የባለፈውን የውድድር አመት ግማሹን በሮማ እንዳሳለፈ የሚታወቅ ሲሆን በዚያን ጊዜም በሁሉም ውድድሮች 12 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሎ ነበር።

ጥር ላይ ወደ ሮማ ከማቅናቱ በፊት በዚያ የውድድር አመት ለአርሰናል 11 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሎ ነበር። ነገር ግን በያዝነው የውድድር አመት በአርሰናል የጨዋታ ስብስብ ውስጥ እንኳን መካተት አልቻለም።

@ZENA_ARSENAL @ZENA_ARSENAL