Get Mystery Box with random crypto!

#ሰበር የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ የዋግነር አለቃ ፕሪጎዚን ወደ ሩሲያ መመለሳቸውን ተናገሩ | ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

#ሰበር
የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ የዋግነር አለቃ ፕሪጎዚን ወደ ሩሲያ መመለሳቸውን ተናገሩ

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ባለፈው ወር በሩሲያ የተፈጠረዉን ጥቃት ለማስቆም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ማድረጋቸዉ የሚታወስ ሲሆን የሩሲያ ቅጥረኛ ቡድን ዋግነር መሪ ዬቭጄኒ ፕሪጎዚን ቤላሩስ አለመሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ሉካሼንኮ ከቀናት በፊት ፕሪጎዚን በስምምነቱ መሰረት ወደ ቤላሩስ መምጣታቸዉን ተናግረዉ ነበር፡፡

"ፕሪጎዝሂን በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ ናቸዉ በቤላሩስ ግዛት ዉስጥ አይደሉም "ሲሉ ሉካሼንኮ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡በሌላ በኩል የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንደተናገሩት ወደ ዩክሬን የሚላኩ የጦር መሳሪያዎች መዘግየት የመልሶ ማጥቃቱን ሂደት እንዳዘገየዉ ገልጸዋል፡፡ይህዉ መዘግየት ሩሲያ በያዘቻቸዉ የዩክሬን ግዛቶች ፈንጂን ጨምሮ መከላከያዋን እንድታጠናክር አስችሏታል ሲሉ አክለዋል።

የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኢጆር ክላይመንኮ ሩሲያ በምዕራባዊ የዩክሬን ከተማ ሊቪቭ በፈፀመችዉ የሚሳኤል ጥቃት አራት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 32 ሰዎች ቆስለዋል።የሊቪቭ ከንቲባ አንድሪ ሳዶቪይ በጥቃቱ ወደ 60 የሚጠጉ አፓርትመንቶች እና 50 ተሽከርካሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ጥቃቱ ባለፈው አመት ከተጀመረዉ ጦርነት በኃላ በሊቪቭ ከተማከፍተኛ የሲቪል መሠረተ ልማት ዉድመት ማስከተሉን ገልጸዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል