Get Mystery Box with random crypto!

ገድለውቷል። ዘርፈውታልም። '…ጎጃሞች አንዲህ ነበር መከራ የበዛባቸው። አዲስ አበባ ለመግባት ሚ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ) ነጭ ነጯን

ገድለውቷል። ዘርፈውታልም።

"…ጎጃሞች አንዲህ ነበር መከራ የበዛባቸው። አዲስ አበባ ለመግባት ሚልዮን ብር ክፈሉ ተባሉ። ሾፌሮች ኦሮሚያ ላይ ይገደላሉ። መኪናው ይቃጠላል። ፍትሕ አጡ ጎጃሞች። ወሎዬዎችም ከወለጋ ታርደው ተሰደዱ። ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን እንዳታልፍ ተባለ። ጎንደሮችም እንደዚሁ። መጨረሻ ላይ ሲመራቸው ዛሬ አገዛዙን በእንብርክክ እያስኬዱት ነው።

"…ይሄ ወጣት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሶፎንያስ ዓሥራት ይባላል። የ24 አመት ወጣት ሲሆን ማክሰኞ ለሊት 8 ላፍቶ አካባቢ ሁለት ወንድ እና አንድ ሴት ሆነው ኖሆም ሆቴል አካባቢ የሰፈሩ ስም ላፍቶ ቦሌ ሚካኤል ውሰደን ብለውት ኮንትራት ይዘውት ይሄዳሉ።

"…ናሆም እንደሄደ አልተመለሰም። በማግስቱ እናቱ ስልኩ ላይ ስትደውል አይሠራም። ጓደኛው ጋር ስትደውል ቦሌ ሚካኤል ብሎ እንደወጣና እንዳላገኘው ይነግራታል። የፈለገ ነገር ቢፈጠር ከእናቱ ጋር ይደዋወል የነበር ልጇ ደብዛ መጥፋቱ ያስጨነቃት እናትም ቦሌ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ትጠይቃለች። የተመዘገበ ነገር  ካለ እናሳውቅሻለን ይሏትና ተመልሳ ላፍቶ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ጠየቀች። እነሱም ተመሳሳይ ነገር ነገሯት እና የአቃቂ ቃሊቲን ስልክ ይሰጧታል። እዚያ ስትደውል ስልኩን ለሌላ ሰው ስጪ ብለው ያለውን ነገር ማለትም ወጣቱ መገደሉንና አስክሬኑ ማሰልጠኛ አካባቢ እንደተገኘ እንዲሁም ለምርመራ ጳውሎስ እንደተወሰደ ይነግሯታል።

"…ዛሬ 5 ሰዓት አካባቢ አስክሬን ተቀብለው ወደ መኖርያ ቤቱ ወደ ላፍቶ ኮንደሚኒየም ወሰዱት። ገዳዮቹ እስከአሁን አልተገኙም። ኮድ 2 A 93488 ቪትዝ መኪናውንም ይዘው መሠወራቸውን የሟች ሶፎንያስ የቅርብ ወዳጆች መረጃውን ለየኔታ ቲዩብ አድርሰው ተዘግቧል። ነፍስ ይማር…!

• አዲስ አበቤ በብላሽ መሞት አይባቃም ግን…?