Get Mystery Box with random crypto!

• ቱቢሆነስት ምን ተሻለን…? ፩ኛ፦ ሰውየው 6 ዓመት ሥልጣን ላይ ቆይቶም፣ ከዚህ በኋላም ለመቆ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• ቱቢሆነስት ምን ተሻለን…?

፩ኛ፦ ሰውየው 6 ዓመት ሥልጣን ላይ ቆይቶም፣ ከዚህ በኋላም ለመቆየት እንዳሰበ እየተናገረም በሥልጣን ዘመኑ ሁሉ አንድም ዩኒቨርስቲ እንደማይገነባም አስረግጦ ተናግሯል።

፪ኛ፦ እሺ ዩንቨርስቲ ካልገነባ ምን ሊያደርግ አስቦ ይሆን? ብለን እንዳንጨነቅም መልሱን ራሱ ይነግረናል። በዘመኑ መገንባት እና መሥራት የሚፈልገው ከመዋዕለ ህፃናትን እስከ 7 ተኛ ክፍል ድረስ ብቻ ነው። ይሞታል እንዴ?

፫ኛ፦ መልካም ህፃናት ላይ መሥራት ልክ ነው። እሺ ህፃናት ላይ እየተሠራ ነው ወይ ብለን ስንል ደግሞ የእንግሊዙ የዜና ወኪል የሆነው ቢቢሲ ለዚህ ምላሽ ይዞ ከች ይላል። "በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሁለተኛና የሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ውስጥ 56% ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ፣ 63% አንድም ቃል ማንበብ የማይችሉ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል። (ጄኖሳይድ በሉት)

"…በመጨረሻም ትውልድን በጠመንጃ ጥይት እና በመሃይምነት ሰይፍ በመግደል ደናቁርት የሞሉበት ሀገር በመፍጠር ለላኩት አካላት ለማስረከብ እየሠራ ያለው ሶዬ በጦርነቱ ውስጥ ከተዘጉት ዩኒቨርሲቲዎች ውጪ በሰላም ቀጠና ያሉት ለተማሪ ምግብ ማቅረብ አቅቷቸው ተማሪ ሊበትኑ መሆናቸው ተነግሯል። ተሰምቷልም።

"…በምግብ ምርት ራሷን የቻለችዋ፣ ያቺ የበለጸገችዋ የብልፅግናዎቹ ሀገር ኢትዮጵያ ግን ትርፍ ስንዴ አምርታ፣ ለእርዳታ የመጣውንም ሰርቃ ለውጭ ሀገር ገበያ በሽያጭ ማቅረቧን በበልፄ አንደበት የነገረችን ነገር ተማሪ እንኳ ማብላት ካቃታት ምንድነው የሚሻለን? የተማረ ይግደለን ስንል ቆይተን ያልተማረው እጅ ላይ ጥሎን ይፍጀን።

• ቱቢሆነስት ምን ትላላችሁ…?