Get Mystery Box with random crypto!

ለሁሉም አይቀርም ስልህ… '…በትግራዩ ጦርነት ወቅት ጁንታውን ትቶ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ትም | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ለሁሉም አይቀርም ስልህ…

"…በትግራዩ ጦርነት ወቅት ጁንታውን ትቶ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ትምህርት ቤት ፋብሪካዎችን፣ በዐማራ ክልል ገዳማትና የገበያ ማዕከላትን ሠርገኞችና ሙሽሮችን፣ ለቀስተኞችን፣ ትምህርት ቤቶችን በኤምሬትስ፣ በቱርክና በኢራቅ የድሮን ቦንብ ሲቀጠቅጥ የከረመው ጀነራል ይልማ መርዳሳ አሁን በተራው የጋራው ኀዘን በእርሱም ቤት ገብቷል።

"…ጀነራል ይልማ መርዳሳ ሰሞኑን በትውልድ ሀገሩ በሪፐብሊካን ጋርድ እና በመከላከያ ኮማንዶ ያስጠብቃቸው የነበሩት ቤተሰቦቹን እና ዘመድ አዝማዶቹን በራሳቸው በኦነግ ሸኔ በቤተሰብ ጦር የገዛ ወንድሙንና አጎቱን ተገድለውበት በብስጭት ላይ መሆኑም ተሰምቷል። ከተገደሉት በተጨማሪ በርከት ያሉ ቤተሰቦቹም ታግተው መወሰዳቸውና ለማስለቀቂያ እስከ 20 ሚልዮን ብር እንደተጠየቀባቸውም ተነግሯል። ለኢንጅነር ታከለ ኡማ አባት ለኦቦ ኡማ በንቲ እስከ 10 ሚልዮን ብር ድረስ ከፍለው ያስለቀቁት ኦህዴዶች ለጀነራሉ አባት ምን አስበው ይሆን የሚሉም አሉ።

"…ይሄ ሁሉ የሚሆነው እዚያው አዲስ አበባ አፍንጫ ስር በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በጀነራል ይልማ መርዳሳ የትውልድ ስፍራ በሆነችው አመያ ወረዳ ጉሶ ቀበሌ ነው። እስከ አሁን በመላ ኢትዮጵያውያን ግብርና ቀረጥ የጀነራሉ ቤተሰቦች በሁለት ሬጅመንት ሪፓብሊካን ጋርድ በከፍተኛ ጥበቃ ይጠበቁ የነበሩ ሲሆን ሠራዊቱ ሲመታ የጀነራሉ ቤተሰቦችም ተገድለው ታግተዋልም። የበሻሻው በጃል መሮ ሠራዊት ስር ነው። የአዳነች አበቤ አርሲና የሺመልስ አብዲሳም ምዕራብ ሸዋ ሁሉ በጃል መሮ ስር ነው። አዲስ አበባ ዙሪያም ሸኔን አምጥተው አስፍረውታል።

• የጀነራሉም የበቀል ምላሽ እየተጠበቀ ነው የሚሉ መተርጉማንም አሉ።