Get Mystery Box with random crypto!

'ርዕሰ አንቀጽ' '…አንድን ሰው አንድ ጊዜ በኃይለኛው ልትሸውደው፣ ልታታልለው ትችላለህ። ምን | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…አንድን ሰው አንድ ጊዜ በኃይለኛው ልትሸውደው፣ ልታታልለው ትችላለህ። ምን አስነክቶኝ ነው? በምን አፍዝዞኝ ነው? መተት፣ ድግምት፣ አስማት አስነክቶኝ ነው እንጂ እንዱህማ አድርጎ አይሸውደኝም፣ አያታልለኝም ነበር ብለህ እስክትቆጭ እስክትገረም ድረስ ልትሸወድ ትችላለህ። ይሄ ደግሞ ያለ ነው። ተፈጥሮአዊም ነው። ሳትተኛ ሳያሸልብህ በአደባባይ ከእጅህ ላይ ሰዓትህን፣ ከጣትህ ላይ ቀለበትህን፣ ከአንገትህ ላይ ሀብል ወርቅህን፣ የኪስ ቦርሳህን፣ ሞባይልህን ወስዶብህ ልትደነቅ ትችላለህ። ከመደነቅህ የተነሣ ያደነዘዘህን፣ አፍዞ የሰረቀህን ልትሸልመው ራሱ ሊዳዳህ ትችላለህ። እንደ መጀመሪያው ባይሆንም በድጋሚም ልትታለል ትችላለህ። ክፋቱ ይሄ መታለል መጭበርበር የሁል ጊዜ የዘወትር ሙያህ፣ ተግባርህ ከሆነ ግን አንተ ሃኪም ዘንድ መቅረብ፣ ጠበል ሄደህ መነከር ነው ያለብህ።

"…እንቅፋትም አንድጊዜ ሊመታህ ይችላል፣ ጥፍርን መንግሎ፣ በአናትህ ተክሎ፣ በአፍጢምህ ሊደፋህ፣ ጥርስህን ሊያስለቅምህ ሁላ ይችላል። ሌላም ጊዜ ተዘናግተህ ሊደግምህ ይችላል። እንቅፋቱ ግን ሁል ጊዜ በወጣህ በገባህ ቁጥር የሚያዳፋህ ከሆነ፣ በአፍጢምህም ተክሎ ጥርስህን የሚያስለቅምህ ከሆነ ግን ድንጋይ እንቅፋቱ ምንም ስህተት የለበትም። ራሱ ድንጋዩ ራስህ አንተው ነህ ማለት ነው። ለጠየቀህ ሁሉ ሁል ጊዜ እንቅፋት መትቶኝ ነው እያልክ ገጣባህን የምታሳይ ከሆነ እንቅፋቱ ራስህ ነው ማለት ነው። የምትወቅሰው፣ መታኝ አደናቀፈኝ እንቅፋት ሆነብኝ ብለህ የምትከሰው ግዑዝ ድንጋይ ወይም እንጨት ሆነ እንጂ አፍ እውጥቶ የሚናገር ቢሆን ራሱ እንቅፋቱ ነበር አንቀጽ ጠቅሶ ከስሶ ከርቸሌ ዘብጥያ የሚያስወረወርህ።

"…የሰው ልጅ አልፎ አልፎ፣ በአዳዲስ በእንግዳ ሰዎች ሊታለል ይችላል። በተለይ ሱፍ የለበሰ፣ ጥሩ ቁመና ያለው፣ የተማረ የሚመስል፣ ቆንጅዬ ሴት፣ ደንዳና የቤት እመቤት የምትመስል እነደ ቦርኮው፣ እንደ ደሀው፣ እንደ ጨርቃሙ ሰው ስለማይጠረጠሩ ለማታለል ምቹ አፈር ይሆናሉ። በአዳዲስ ዘዴ፣ ታክቲክ፣ ቴክኒክም ሰው ሊሰረቅ፣ ሊዘረፍ ይችላል። እንጂ ሁሌ ዘወትር መልኩን ግብሩንም በሚያውቁት ሌባ፣ ዘራፊ ሊዘረፍ አይችልም። አንድ ሌባ ሁል ጊዜ የሚሰርቅህ ከሆነ ሌባው ሌባ ሳይሆን መባል ያለበት ግብር፣ ታክስ፣ ቀረጥ ሰብሳቢ ነው መባል ያለበት። ስለትህን፣ አሥራትህን፣ ዘካህን እየሰጠኸው ነው እንጂ ዘረፈ ሰረቀኝ ብለህም ማውራት የለብህም። በተለያየ ታክቲክ የተለያዩ ሌቦች ሊሰርቁን የሚችሉት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። እዚያው አውቶቡስ ውስጥ፣ እዚያው ሰፈር፣ በእዚያው መንገድ ላይ ያው የማውቀው ሌባ ሁሌ የሚሰርቀኝ ከሆነ ግን በቶሎ ሃኪም ሊያየኝ እንጂ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ የለብኝም።

"…መሀይሙ አቢይ አህመድ፣ አጭቤው፣ ቀፍሎ አዳሪው፣ አውርቶ አደሩ አቢይ፣ የበሻሻው አራዳ ስንቴ ነው የሚዘርፍህ? የሚሸውድህ? እርግጥ ነው ሰውየው በመጀመሪያው ወራት አዳሜና ሄዋኔን አደንዝዞ፣ አፍዞ አስገብሯል። የ7 ተኛ ጨው ተማሪ በፌክ ዶክትሬት ፍሮፌሰሩን ሁሉ አፍ አስከፍቷል። አርቲስቱን፣ አክቲቪስቱን ሁሉ እግሩ ስር አሰግዷል። ጋዜጠኞችን ማርኳል። ጳጳስ፣ ፓትርያርክ፣ ቄስና ሼክ፣ ፓስተር ሁላ አልቀረውም ዋቴ ሲሠራው። ወንድ ሴት፣ ህፃናት አዛውንት፣ ወጣት የለም፣ አራዳ፣ ፋራ፣ ብልጥ፣ ሰገጤ የለም። ወዛደሩንም ወታደሩንም ሁሉንም  እኩል ነው ያሟሟቸው። ሿሿ የሠራቸው። ኧረ ይሄ ሰው? የምንል ጥቂቶችንም ሆነ መንጋውን አፈር ከደቼ ያስጋጠን። ኢትዮጵያን፣ እናትን፣ ሚስትን፣ እግዚአብሔርን በአፉ ጠርቶ ነው ምድሩን ሁሉ ሽባ ያደረገው።

"…እሺ አንድ ቀን ተሸወድክ ምንም አይደል። አንድ ወርም ተሸወድክ፣ አንድ ዓመትም ጊዜ ሰጥተህ ተሸወድክ እንበል። ስድስት ዓመት ሙሉ ለመሸወድ መዘጋጀት፣ መፍቀድ ችግሩ የአቢይ፣ የብልጽግናም አይደለም። ችግሩ የራስህ ነው። ወይ ፈርተሃል፣ ቀዝነሃል፣ ተንበጫብጨሃል አልያም ለመታለል፣ ለመጭበርበር ፈቅደሃል። ወይም አንተ ራስህ ከእሱ የባስክ አጭበርባሪ፣ ቀጣፊ፣ ዋሾ፣ ሌባ፣ ዘራፊ፣ ቀማኛ፣ ነፍሰ ገዳይ፣ ሳዲስት፣ ውሸታም አስመሳይ ነህ። ሌባን ሌባ ቢሰርቀው ምን ይደንቀው ነገር ነህ። ለጨካኝ ደግሞ ጨካኝ ነው የሚታዘዝለት፣ ለሌባ ሌባ፣ ለዋሾ ውሸታም። ስለዚህ በአቢይ ምላስና አመራር እየተታለልክ ለመገዛት ፈቃደኛ ከሆንክ እሱ የሚከሰስበት አንዳችም ምክንያት የለም። ራስ ወዳድ ሰው አያሸንፍም።

"…በዘመነ ደርግ የግዳጅ ሰልፍ ነበር። ወያኔ ጫካ ሆና ሕዝቡ በግዳጅ ነው ደርግን ወጥቶ የደገፈው ብላ ዋይዋይ ትል ነበር። ደርግ ወርዶ እሷ ሥልጣን ላይ ስትወጣ በግዳጅ ብቻ አይደለም በአበል ሁላ ታሰልፈው ጀመር። ስዩም መስፍንማ ባድመን ለሻአቢያ አስረክቦ ሲያበቃ በገገማው መጥቶ ባድመ ለእኛ ስለተወሰነ ሕዝቤ ሆይ በጀማ ወጥተህ መስቀል አደባባይ ጨፍር ብሎ የቴሌቭዥን ቀጥታ ሥርጭት ሁላ አዘጋጅቶ እነ እማማ ዘቢደሩንና እነ እማማ ዙቤይዳን አስጨፈራቸው። ገገማ። ይኸው የህወሓት የወያኔ ኢህአዴግ ልጅ አጅሬ ብልጽግናም የሴፍቲኔት ጡረተኞችን እና እስላሞችን በሃይማኖት ሰብኮ ሰልፍ አስወጥቶ ድጋፍ አገኘሁ ብሎ ዓይኑን በጨው ታጥቦ አታሞ ሲያስደልቅ፣ ከበሮ ሲያስመታ እናያለን።

"…የሕዝብ ንቃተ ህሊና ጨምሯል ወይ? መልሱ አዎ ጨምሯል ነው። ተዲያ በነቃው ሰው ልክ ይሄን ከሃዲ ሀገር አፍራሽ ቡድን ሊዋጋው፣ ሊያወርደው፣ ሊቀይረው የቆረጠስ አለ ወይ? አሁንም መልሱ አዎ አለ ነው። ይሄ የቆረጠ የሚባለው ሰው ብዛቱ ሲታይም የተግባር ትግል ከጀመረው በቁጥር ደረጃ ሲታይ ግን በጣም ጥቂት ነው። ነገሩ፣ ሴራውን ያወቀ፣ የተረዳ፣ ነገር ግን ያልቆረጠ፣ ወደ ተግባራዊ ትግል ያልገባ፣ በቤቱ፣ በጓዳው፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ኮመንት ሥር ብቻ ዘራፍ እያለ የሚፎክረው፣ በየመጠጥ ቤቱ የሚፎገላው ግን 95% ቱ ሕዝብ ነው። ይሄ ቀጣፊ አገዛዝ እንዲህ እግር ተወርች የተያዘው፣ መተንፈሻ ያጣው በጣም ጥቂት ነገር ግን ቁርጠኛ በሆኑ ፋኖዎች ነው። ይሄ ይሰመርበት። በጣም ጥቂቶቹ ናቸው መሠረቱን እያናጉ ያሉት። እነዚህን የሚቀላቀል ሰው ሲጨምር ይፈርሳል።

"…ሴራዎቹም ተመሳሳይ ናቸው። በዘመነ ወያኔ ደሴ ላይ ሼኹን ገድሎ እስላሙን ሁሉ አሸባሪ ብሎ የረፈረፈው፣ ዘብጥያም ያስወረወረው አቢይ አሕመድ ነው። አቢይ አህመድ የስለላ ድርጅቱ ሓላፊ በነበረ ጊዜ ነው እስላሞች ፍዳ የበሉት። በሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖች ሲታረዱ በዚያ ሓላፊ የነበረው አቢይ አሕመድ ነው። አቢይ የሃይማኖት ካርድ ስቦ መምጣቱ አዲስ አይደለም። ኦርቶዶክስን እበቀላታለሁ ማለቱን በጆሮው ሰምቶ የነገረን ራሱ ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ ነው። ዐማራንና ትግሬን ዱቄት ሳያደርግ፣ በየተራ ሳያወድማቸው እንደማይተኛ የታወቀ ነው።

"…የነቃው ሰው ይሄው ትናንት ታይቷል። መጀመሪያ ጎንደር ላይ፣ ቀጥሎ ጎጃም ላይ እስላሞችን ገድሎ እንደ ድሮው መስሎት በዚያው በድሮ አራድነት፣ ያውም የፊት  ጥርሳቸው የወለቀ፣ የሸረፈ፣ እነዚያኑ እነ ሙጂብ አሚኖንና እነ አህመዲን ጀበልን ይዞ ነገሩን ማጮሁን ያፈረሰው ራሱ እስላሙ መሆኑን ስታይ የህዝቡ ንቃተ ህሊና መጨመሩ ይታይሃል። የኦሮሞና የስልጤ እስላሞች አራዳ፣ የዐማራ እስላሞችን ዥል አድርጎ እንደ ድሮው ጎንደር ሞጣ ብሎ መምጣቱ ዘንድሮ አላዋጣም። በኦሮሚያ ስለተጨፈጨፈው የዐማራ እስላም ትንፍሽ የማይለው የኦሮሞ እስላም ዛሬ የኦሮሞ መጅሊስ ቦታውን ሲይዝ ለዐማራ እስላም ተቆርቋሪ ሆኖ መቅረብ አስቂኝ ነው። ገገማ ፋርነት ነው።… ከታች ይቀጥላል…