Get Mystery Box with random crypto!

የወልድያው ፍንዳታ…!! '…ከህወሓት የተተኮሰ ነው የተባለ ከባድ መሣሪያ ከሳምንት በፊት ወልድያ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የወልድያው ፍንዳታ…!!

"…ከህወሓት የተተኮሰ ነው የተባለ ከባድ መሣሪያ ከሳምንት በፊት ወልድያ ተራራው ላይ ባለው ከቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጀርባ ባለ መንደር ላይ ያረፈ ከባድ መሳሪያ ተኩሳለች። ይሄ ከሳምንት በፊት ነው።

"…ቀጠለና ከ3 ቀን በፊትም እንዲሁ በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የመቃብር ቦታ ላይ የወደቀ ከባድ መሳሪያ ተኩሳለች። ሁለት በሉ።

"…ይኸው ዛሬ ደግሞ ለ3 ጊዜ የተኮሰችው ከባድ ጀነራል መድፍ አኢሴማ ሰፈር አካባቢ አደንጉር ማርያም ቤተክርስያንያን ከትምህርት ቤቱ ጀርባ መውደቁ ተነግሯል። ፍንዳታው ከባድ እንደነበር የተነገረ ሲሆን ከገብርኤል ከተራራው በመውረድ ላይ የነበሩት የዐማራ ልዩ ኃይሎች እና የመከላከያ ሰራዊቱ በፍጥነት በቦታው ላይ የደረሱ ሲሆን እስከ አሁን በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ስለደረሰ ጉዳት እስከአሁን የነገረ መረጃ የለም።

"…ከባዱን ፍንዳታ ተከትሎ ወደ ሰማይ የሚግተለተለውን ጢስና አዋራ የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች እያዩ መሆናቸውንና አሁን ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ ከቤቱ ወጥቶ በየደጃፉ ላይ ተቀምጦ አሞራና ወፍ ባለፈ ቁጥር በስጋት መቀመጡ ተነግሯል።

•የእኔ ጥያቄ…?

፩ኛ፦ ህወሓት ያለችው የት ነው? ቆቦ ናት ጎብዬ?

፪ኛ፦ መድፉ 40 ኪሎ ሜትር ይሄዳል ያለኝ ሰው አለ። እንዲያ ከሆነ ህወሓት ጎብዬ ናት ማለት ነው። ከጎብዬ ወልድያ በመሬት 25 ኪሎ ሜትር ነው የሚርቀው። አስተኳሹም ወልድያ ነው ማለት ነው። እንደዚያ ከሆነ ህወሓትም በመቀሌ ቤት ለቤት አስተኳሾች እዚህ ናቸው ብላ እየፈተሸች እንዳለው ሁሉ በወልድያም ጫት መቃም፣ ማስቃም መከልከሉ፣ የተገኘውንም ጫት መቃጠሉ እንዳለ ሆኖ ለምን በወልድያ ባለው አስተኳሽ ላይ ፍተሻ አይደረግም?

፫ኛ፦ ከድሮኗ በስህተት ይሆን እንዴ የተተኮሰው?

"…ለማንኛውም ድራማው እንደቀጠለ ነው።