Get Mystery Box with random crypto!

ቀላዋጭ…!! ኢሬቻ ማለት…  የባዕድ አምልኮ ነው። የእምነቱም ስም… ዋቄፈና ይባላል። ዋቃ እና አ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቀላዋጭ…!!

ኢሬቻ ማለት…  የባዕድ አምልኮ ነው።
የእምነቱም ስም… ዋቄፈና ይባላል።
ዋቃ እና አቴቴ… የእምነቱ አማልክቶች ናቸው።
የእምነቱ ዓይነት… ሁሉን አቀፍና ሁሉን አሳታፊ ባህላዊ/የባእድ አምልኮ ነው።
የአምልኮ ሥርዓቱ የሚፈፀምበት ስፍራ… በውኃ ዳር እና የተመረጠ የአድባር ዛፍ ባለበት ሁሉ ነው።
የእምነቱ አገልጋይ ባለ ሥልጣናትም… አባ ገዳ እና ሃዸ ስንቄ ተብለው ይጠራሉ።

"…ይሄ ደግሞ የኦርቶዶክስ ቄስ ነው። አምላኩ ኢየሱስ ክርስቶስ የብርሃን አምላክ፣ ክርስቶስ የሞተለት፣ የተሰቀለለት፣ የደማለት፣ ከሲኦል ባርነት፣ ከአጋንንት እስራት የፈታው፣ ነፃም ያወጣው። ካህኑ አድርጎ የሾመው። ሰው ነው። ምንአባቱ ሊሠራ ነው ወንዝ ወርዶ ለዋቃ ጉራቻ ምስጋና የሚያቀርበው? በሰው ኃይማኖት ውስጥ ምን ይሠራል። ይሄ የማሰቢያ ብሎኑ የወለቀ፣ የመንግሥት ሃይማኖት ላይ በሌለው ቦታ የሚልከሰከስ፣ የቃሉም፣ የመስቀሉም አሰዳቢ ዘገምተኛ ሰው ነው።

"…የዋቄፈና ካህናቱ አባ ገዳና ሃዸ ሲንቄዎች ናቸው። እሱ ምን ቤት ነው እዚህ የሚያልከሰክሰው? ምንአለበት መስቀሉን ቢያወልቀው? ምንአለበት ቀሚሱን ቢያወልቀው? ምንአለበት ቆቡን ቢያወልቀው? ይሄን ኮተታም ገና ከአጋንንት እስራት ያልተፈታ፣ የእናቱን ጨሌ ወርሶ ሰንዱቁ ውስጥ አስቀምጦ የሚልከሰከስ ሰው እያዩ ነው ሌሎች የሚሰድቡን። አሁን ይሄ ካህን ነው?

"…ይሄ ገተት አይወክለኝም። ካህኔም አይደለም። እነ ሙጂብ አሚኖና አህመዲን ጀበል እንኳ ስለ ኢሬቻ ምንም ላለማለት ድራሽ አባታቸውን ባጠፉበት ሰዓት ገና ለገና የመንግሥት የሥጋ ዘመድ ነኝ፣ የሚያወግዘኝ፣ ክህነቴንም የሚይዝ ወንድ እናቱ የወለደችው ሲኖዶስ የለም ብሎ እንዲህ ሰድቦ ለሰዳቢ የሚሰጠንን የሰው ግማሽ ምን ትሉታላችሁ።

"…ኢሬቻን ለአማኞቹ መተው ነው። የምን መቀላወጥ ነው? ቀላዋጭ።