Get Mystery Box with random crypto!

ለዐማራ ሲኦሏ ኦሮሚያ '…ወንድነት እኮ አይደለም። ጀግንነትም አይደለም። ገና ለገና ከኋላ አቢይ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ለዐማራ ሲኦሏ ኦሮሚያ

"…ወንድነት እኮ አይደለም። ጀግንነትም አይደለም። ገና ለገና ከኋላ አቢይ አሕመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ብርሃኑ ጁላ፣ ይልማ መርዳሳ ወዘተረፈ አሉልን፣ ጠያቂ፣ ተሟጋች፣ ተከራካሪም የለብንም ተብሎ በማሳው ውስጥ ሃገር ለመመገብ ከአፈር ጋር የሚታገል ምስኪን ገበሬ ገድሎ፣ አርዶ ሰልፊ እየተነሡ ፎቶ መልቀቅ የወንድ ሥራም አይደለም።

"…በኦሮሚያ በንፁሐን፣ በምስኪን ዐማሮች ላይ የሚፈጸመው ግፍ የግፍ ፅዋም ሞልቶ ፈሷል። ትናንት እና ዛሬ ኦሮሞ ላፈሰሰው ደም ምስጋና ለዋቀ ጉራቻ ሲያቀርብ ውሏል። ጭፈራው፣ ዳንሱ፣ መጠጡ፣ ስካሩ፣ ዝሙቱ ለጉድ ነበር። የአሸናፊነት ስሜታቸው በንፍጥ መልኩ ራሱ ሞልቶ ሲፈስ ታይቷል። የቢራ ዋጋ፣ የሥጋ በኪሎ 1500 ብር መግባት፣ ውስኪው አያስጨንቃቸውም። ብር በተለየ መልኩ ለኦሮሞ ቀሬና ቄሮ እንዴት እንደፈሰሰ ፈጣሪ ይወቅ። መንግሥቱ ትራንስፖርት በነፃ ሲያቀርብ ከየትኛው በጀት እንደሆነ ግን አልተናገረም። ከሁሉ የሚገርመው የሃበሻ የሃገር ባህል ልብሱ በነፃ ለቀበሌ ጽዳት ሳይቀር መታደሉ ነው። ነገርየው በዋጋ ደረጃ ውድ ይመስለኛል። ከህወሓት ብልጠትን ያልተማረውና ዝርፊያ ብቻ የተማረው ኦሮሙማ ሃገሪቷን በአፍጢሟ ልክ እንደወለጋው ምስኪን ገበሬ ሊደፋት ተቃርቧል።

"…ህጻናት ለደብተር መግዣ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች መለመን ጀምረዋል። ነዳጅ 16% ፐርሰንት ጨምሯል። አምራች ገበሬ እንደምታዩት እየታረደ ነው። ኑሮ ተወዷል። የቤት ኪራይ ዋጋ ንሯል። መከራው፣ ስቃዩ በሁሉም ቤት እየገባ ነው። እንዲህም ሆኖ በኦሮሚያ ንፁሐን መታረዳቸውን ቀጥለዋል።

"…የናፈቀኝ የዚህ ግፍ መጨረሻው ነው። ነፍስ ይማር ምስኪኑ ገበሬ።