Get Mystery Box with random crypto!

የምሽት መርዶ ነው…!! '…ሃይ ባይና የሚያስቆም። ምንድነው ነገሩ? ምን እስክንሆን ነው የምንጠ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የምሽት መርዶ ነው…!!

"…ሃይ ባይና የሚያስቆም። ምንድነው ነገሩ? ምን እስክንሆን ነው የምንጠብቀው የሚል ልብ ያለው፣ ምራቁን የዋጠ፣ ለትውልድ የሚያስብ አንድ ሰው ስለጠፋ እንደተለመደው ትናንት እንደነገርኳችሁ ሸገር አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ምስራቅ ሸዋ በመተሃራ አባድር 2ተኛ ካምፕ ኦነግ ሸኔ ተብሎ ዐማራን ለማጽዳት በዐቢይ ሽመልስ በተፈጠረው አረመኔ ገዳይ የአባ ገዳ ሠራዊት የተገደሉ 12 ወጣቶች ዛሬ ከረፋዱ 5-6 ሰዓት የ11ዱ በሀሮ አዲ ከተማ በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የቀብር ሥርዓታቸው በጅምላ ተፈፅሟል።

"…የተረሸኑት ወጣቶች 12 ሲሆኑ 11 ክርስቲያኖች 1ኛው ወጣት ደግሞ እስላም መሆኑም ተነግሯል። ሟቾቹምን ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

1 ረታ ስምኦን
2 ፍስሀ ደብልቀው
3 አጥናፉ ዮሐንስ
4 ሻምባል መኮንን
5 አብርሃም አዲሴ
6 ተመስገን እንየው
7 ከበደ ደሳለኝ
8 ተሾማ ሴፓ
9 ፈንታሁን
10 አለማየሁ
11 ሰሙ አልተወቀም። ማንጎ መብላት አምሮት ጓደኛው ጋር አግኝተው የገደሉት የመርቲ ነዋሪ ነው። 12ኛው ሙስሊም ወጣት ነው።

ከሞት ተርፈው ናዝሬት ሪፈር ተብለው የሄዱት ደግሞ በመርፌ ካልፈጇቸው ስም ዝርዝራቸውን እነሆ።

1 ፈንታሁን መኮንን
2 ጋሸው መለስ
3 መስረሻ ዐወቀ
4 በላይ በቡሬ
5 ነጋሽ አበራ

አጅሬ የኦሮሚያ ኦህዴድኦነጉ መንግሥት በወያኔ እያሳበበ በሸኔ ስም ያለማቋረጥ 4 ዓመት ሙሉ ዐማራው በጅምላ እየረሸነ ሬሳውን ለአፈሩ ማዳበሪያ ይከምረዋል። ጠያቂ የለም። ሁሉም የመታረጃ ቀኑን ብቻ ከመጠባበቅ በቀር ሌላ ነገር የለም። ኢህአዴግን ግን ምን አደረገ ተብሎ ነበር ተቃውሞው? ረሳሁት።

"…ወዳጄ አዲስ አበባ አላስገቡኝም ብለህ አትማረር እንዲህ በጅምላ መጨፍጨፍም አለና።

•ማነህ ባለ ሳምንት ቀጥል ተረኛው ሟች?

•እንደተለመደው ነፍስ ይማር…! እንበል…!