Get Mystery Box with random crypto!

'…የአዲስ አበባው በአል በዚህ መልኩ አልቋል። ነገ በቢሾፍቱ በዋናው ቤቱ መከበሩ ይቀጥላል። እዚያ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የአዲስ አበባው በአል በዚህ መልኩ አልቋል። ነገ በቢሾፍቱ በዋናው ቤቱ መከበሩ ይቀጥላል። እዚያም ላይ እነ ቀውሲ በላይንና እሱን መሳይ ኦርቶዶክስን የሚያሰድብ ዘገምተኛ ቄስና መነኩሴ ካየሁ እኔም ልክ አይደለም ብዬ መንበጫበጬን እቀጥላለሁ። እኔ ከኢሬቻ ጉዳይም ጠብም የለኝም። መብቴም አይደለም። የእኔ ዋናው መልእክት ኢሬቻና ኦርቶዶክስ አባ ገዳና ቄስ በምንም አይገናኙም። እሱን ነው የምመሰክረው። እንጂ ለምን እሺ ካለህ ዲያብሎስን ከገሀነም አምጥተህ አታመልከውም። መብትህ ነው። እኔ ምን አገባኝ። ከኦርቶዶክስ ጋር፣ ከመስቀል ጋር አታነካካ፣ አታዳብል፣ ራስህን ቻል ነው እያልኩህ ያለሁት። ራስህን ችለህ ለምን ጣራ ላይ አትደንስም። መብትህ ነው። ስንት እልል የተባለለት ጠንቋይ በነፃነት በሚዘርፍበት ሃገር ላይ አይደለም ኢሬቻ ለምን የኢሬቻ አጎት አያሽቋልጥም። ጉዳዬ አይደለም።

አንዳንድ እወደድ ባዮች ልክ ኢሬቻን እንደነቀፍን፣ ኦሮሞ ለምን አከበረ እንዳልን፣ እንደቀናን አድርገው እሽኮሎሌ ሲሉ አያቸዋለሁ። ማን አታክብሩ አለ? ስታከብሩ አታነካኩን ነው ያልነው። በኢሬቻ ላይ የሚገኝ ኦርቶዶክሳዊ ምዕመንም ቄስም የተወገዘ ነው ያልነው። ለዋቃ ጉራቻና ለኢየሱስ ክርስቶስ መገዛት፣ እግዚአብሔርንና ጠቋርን ማምለክ አይቻልም ነው እኛ። ነገር አታዳቅሉ እንጂ? ሃይ። ፍቼ ጨምበላላ፣ ወዘተረፈ በሚከበርበት ሃገር መንግሥታዊውን ኢሬቻ አታክብሩ ያለ የለም። እንከባበር። እንደ ቀሲስ በላይ ያለ ቅዳሴ ቀድሶ ማቁረብ የማይችል የክብር ቄስ በየጣኦት አምልኮው ወንዝ እየተገኘ አያሰድበን ነው ያልነው። በየወንዙ ደም በተቀባበት እጁ መስቀል አያሳልመን ነው ያልነው። ይሄን ነው የጠየቅነው። ወይ ድራሽ አባቱ ይጥፋ ነው ያልነው። ይሄ ደግሞ መብታችን ነው።

ለማንኛውም እስከ ነገ… ደኅና እደሩ…