Get Mystery Box with random crypto!

'…በነገራችን ሰውየው ሥራ ላይ ነው። የማዲንጎን ነፍስ ይማር። በማዲንጎ ሞት ሽፋን ግን በወለጋ 5 | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በነገራችን ሰውየው ሥራ ላይ ነው። የማዲንጎን ነፍስ ይማር። በማዲንጎ ሞት ሽፋን ግን በወለጋ 500 ዐማራ ያለምንም ተቃውሞ እና ግርግር ጸድቷል። መቶ ያህሉን ዐማሮች የብልፅግና ሹመኞች እስርቤት አስገብተው በር ዘግተው በቁማቸው በእሳት ጠብሰው ገድለዋቸዋል። 3ቱን በጥይት እስር ቤቱ በራፍ ላይ ረሽነው አንደኛውን በሰንደቅ ዓላማ መስቀያ ብረት ላይ አስከሬኑን አንጠልጥለዋል። በወለጋ ዐማራው እምሽክ እየተደረገ ነው። ይሄን ጉዳይ ዋሽንግተን ፖስትም ዘግቦታል።

"…በትግራይ ዓዲ ዳዕሮ ከተማ ወድሟል። ንፁሐንም ተገድለዋል። ከፈረሰው ከተማ ፍርስራሽ ስርም ንፁሐን ህፃናትና እናቶች አስከሬን ተለቅሞ ወጥቷል። በዚህ ሁሉ መሃል ግን አጀንዳ ማስቀየሻ ማዲንጎ አፈወርቅ ሞቷል። ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ እንኳን ለማዲንጎ የሃዘን መግለጫ አውጥተዋል። የብልፅግና ካድሬና ባለ ሥልጣናትም ጥቁር ልብሳቸውን ዠቅ አድርገው ለማዲንጎ የሃዘን እንጉርጉሮ ሲያሰሙ ውለዋል።

"…ዐማራ አዲስ አበባ እንዳይገባ ተደርጓል። ነዳጅ በሊትር 10 ብር አካባቢ ጨምሯል። ለብልፅግና ፓርቲ የከፋ ነገር ከፊቱ እየመጣለት ነው። ሰው ከባዱን ነገር ዘንግቶ ስለ ማዲንጎ ሞት እያወራ፣ እያዘነ፣ እያለቀሰም ነው። ሚዲያዎቹ ሁሉ አቅጣጫ ተቀመጦላቸው እንዲሠሩበት ተደርገዋል። በተለይ የዐማራ ሚድያማ ጉደኛ ነው። ከ500 በላይ ዐማራ በወለጋ ታርዶ እሱ ቀንም ማታም ስለማዲንጎ ሞት ጥቁር ለብሶ ሲዘግብ ይውላል። እስከ 40ው ድረስ ዘገባው የሚቆም አይመስልም። እስከ ሰኞ ድረስ ደግሞ ከእሬቻ ውጪ ሌላ ወሬ በሚዲያው አይኖርም።

"…በዚህ መሃል ግን የትግራይ ከተሞች ከነህዝባቸው መውደማቸው፣ ዐማራና ትግሬም መዋጋቱን፣ በራያ፣ በወለጋ፣ በኦርሚያም ዐማራው መታረዱ፣ ነዳጁም መናሩ፣ ዶላርም መወደዱ፣ ብርም የመግዛት አቅሙ መፈጥፈጡ ይቀጥላል።

•ደኅና እደሩልኝ…!