Get Mystery Box with random crypto!

የዓዲ ዳዕሮ ውድመት…!! '…የኤርትራ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ጥምር ጦር በሰሜነኛው የትግራይ ክ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዓዲ ዳዕሮ ውድመት…!!

"…የኤርትራ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ጥምር ጦር በሰሜነኛው የትግራይ ክፍል የምትገኘውን የዓዲ ዳዕሮን ከተማ በዚህ በዚህ መልኩ በድሮን በተዋጊ ጀቶች መውደማቸው ተመልክቷል። በተለይ 100% ህዝቡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ እንደሆነ የሚነገርለትና ታላቁን የመስቀል በዓል በሚያከብርበት ዕለት በመኖሪያ ቤቶች ላይ የዘነበው ቦንብ ከተማዋን ወደ ፍርስራሽነት ቀይሯታል። በዓዲግራት፣ በመቐለ፣ በሽረ እና በሽራሮ በተመሳሳይ ልክ እንደ ዓዲ ዳዕሮ በተደጋጋሚ የድሮንና የአውሮፕላን ድብደባ በኤርትራ መንግሥት እና በኢትዮጵያ መንግሥት የተፈጸመ መሆኑም ተዘግቧል። አሁን ዓዲዳዕሮ ከተማዋ እንደሚታየው ወደ ፍርስራሽነት ተቀይራለች።

"…በጦር ቀጠና ውስጥ የሚፈጸም ውድመት የሚጠበቅ ነው። ተፈጥሮአዊም ነው። ነገር ግን እንዲህ እንደሚታየው በንፁሐን ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ተቀባይነት የለውም። ከተጣያቂነትም አያድንም። ዐማራና አፋር ክልል ገብተው ንፁሐንን የገደሉ፣ ሃብትና ንብረት የዋደሙ ህወሓቶችም ሆኑ ወደ ትግራይ ገብተው የትግራይ ህዝቡንም፣ ሃብትና ንብረቱንም የሚያወድሙ ይዘገይ ይሆናል እንጂ ለፍርድ ይቀርባሉ። ኦርቶዶክስና ዐማራ ግን ያለኮሽታ እያፀዱት ነው። ገራሚ ነው።

"…በትግራይ ትግሬው በሰመኔ ወሎ በራያ እና በወለጋ ደግሞ ዐማራው በኦሮሙማው የዐቢይ አህመድ መንግሥት ሴራ እየጸዱ ነው።

"…ያው እንደተለመደው ለዐማራና ለትግሬ ነፍስ ይማር…!! ሌላ ምን ይባላል…?