Get Mystery Box with random crypto!

ዓዲ ዳዕሮ እና ወለጋ '…ጦርነቱ ቀጥሏል። የኤርትራ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ጥምር ጦር በሰሜነኛ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዓዲ ዳዕሮ እና ወለጋ

"…ጦርነቱ ቀጥሏል። የኤርትራ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ጥምር ጦር በሰሜነኛው የትግራይ ክፍል ከህወሓት ጋር እየተዋጉ ነው። በዚህ መሃል የትግራይ ህዝብ የድሮንና የመድፍ ሰለባ እየሆነ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተለይ ሰሞኑን በመስቀል በዓል በዓዲግራት፣ በመቐለ፣ በሽረ፣ በሽራሮ እና በዓዲ ዳዕሮ ተደጋጋሚ የድሮንና የአውሮፕላን ድብደባ በኤርትራ መንግሥት እና በኢትዮጵያ መንግሥት የተፈጸመ ሲሆን የዓዲ ዳዕሮው ግን ከበድ ያለ እና በጣም ይለያል፣ ይከፋልም ነው የተባለው። አሁን ዓዲዳዕሮ ከተማዋ ወደ ፍርስራሽ ተቀይራለች።

"…ዓዲ ዳዕሮ ማለት ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ የትምህርት ዕድል (scholarship) አግኝቶ ተምሮ በመምጣት ሃገሩን በአራቱም ነገሥታት (በአጼ ቴድሮስ፣ በአጼ ተክለጊዮርጊስ፣ በአጼ ዮሐንስ እና በአጼ ምኒልክ) ያገለገለው የማኅደረ ቃል ተወልደ መድኅን የትውልድ ሃገር ናት። አጼ ቴዎድሮስ ዘመነ ክረምቱን ለማሳለፍ የሚመርጧትና ብዙጊዜም ክረምትን የሚያሳልፉባት ናትም ይባላል። ልዑል ራስ መኰንን የመጨረሻ ዘመን ሕይወታቸውን በምናኔ ያሳለፉበት እና እንደ ቤተ ቂርቆስ አቡነ ኖላዊነ ሔር ገዳማት የሚገኙባትም ናት።

"…እሺ ይሄ እንኳን የጦር ቀጠና ነው ልንል እንችላለን። አለልህ እንጂ ወለጋ ዐማራ የሆነ ሁሉ ህፃን ሽማግሌ ሳይል ተራው ዜጋ የሚታረድበት ምድር። ሰሞኑን ብቻ መቶ የሚሆኑ የመንግሥት እስረኞችን ዐማራ ናችሁ ብለው ቤት እስር ቤቱን ቆልፈው በእሳት አቃጥለው ዐመድ እንዳደረጓቸው ተሰምቷል። መስከረም ሊያልቅ 10 ቀናት እየቀሩት በ20 ቀናት ውስጥ ብቻ 500 ዐማሮች ታርደዋል። ራያም የሬሳ ክምር ነው ያለው ይባላል። በዚያም አለ በዚህ የአቢቹ መንግሥት ትግሬንና ዐማራን ምንም አይነት ተቃውሞ ሳይነሣበት እያጸዳው ነው።

"…እንደተለመደው ነፍስ ይማር እንበል።