Get Mystery Box with random crypto!

'…ወለጋ ሄጄ ነው ያረፈድኩት። በኦሮሞ ሚዲያዎች ጭምር ከፍተኛ ቅስቀሳ እየተደረገበት እና በዝግ እ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ወለጋ ሄጄ ነው ያረፈድኩት። በኦሮሞ ሚዲያዎች ጭምር ከፍተኛ ቅስቀሳ እየተደረገበት እና በዝግ እየተፈጸመ ስላለው ዘግናኝ የዐማራን ዘር የማጽዳት ተግባር እንዴት እየተከናወነ እንደሆነ ከተጎጂዎች ስሰማ አርፍጄ ነው የተመለስኩት። የታረዱትን ስምዝርዝር በከፊል ተረክቤአለሁ። እሱን መርዶውን ቆይቼ አቀብላችኋለሁ። ጠብቁኝ።

"…ዘመዴ የዛሬውስ ባጣም አሰፈሪ ነው። ዓለምም እያወቀው ስለሆነ የምን ቁጥቁጥ ነው በአስቸኳይ ባለ በሌለ ኃይላችሁ ዐማሮቹን አጽዷቸው ተብሎ ስለተነገራቸው በ5 አቅጣጫዎች ግልብጥ ብለው እየመጡብን ነው። እንጃ ዛሬስ የመጨረሻችን ቀናችን ይመስለናል። ቪድዮዎቹና ፎቶዎቹ ሰሞኑን ይደርሱሃል። ዐማራ እንኳን አይደርስልንም ሌሎቹ ግን ኦሮሞዎቹ እንዴት እንደፈጁን ለዓለም አሳይልን። ግለጥልንም ብለውኛል። እሺ ብያቸዋለሁ። የሚዘገንን የታረዱ የዐማራ ህጻናት ቪድዮም ደርሶኛል። እንዴት እንደማቀርብላችሁ ስለከበደኝ ለመጀመሪያ ጊዜ አቅም አጣሁ። ኧረ በስመ ሥላሴ። ምን አይነት ጭካኔ ነው?

"…ለኢሬቻው ግብር፣ ለዋቀ ጉራቸው ኦሮሞው በወለጋ የዐማራን ዘር እያጠፋው ነው። እውነቱ ሃቁ ይሄው ነው። ይመዝገብ። ብአዴን ህወሓት ሠርታ ከሰጠችው ክልል ውጪ ስላሉት ዐማሮች አይመለከተኝም ብሏል። ዐማራ መድኅን አጥቷል።

"… በትግራ ዓዲ ዳዕሮም በአውሮጵላን የታገዘ ንፁሐን ላይ ፍጅት መፈፀሙን እየተመለከትኩ ነው። እሱንም እመለስበታለሁ። የራያው የዐማራ እልቂትም እንደቀጠለ ነው።

"…ማዲንጎ አፈወርቅን አስወግዶ አጀንዳ ለማስቀየስ ነፍሰ በላው ዐቢይ አሕመድ የሠራው ሴራም ብዙም አልሠራለትም። ህዝቡ ገብቶታል። የማዲንጎ ሞት እንደፈለግነው አልተጯጯኸልንም ብለው ይልቅ ሌላ ታዋቂ ሰው እንዳይገነድሱ ጎበዝ በጊዜ ግቡ። ጸልዩም። ምክሬ ነው። ትኩረት ለወለጋ።

"…ቆይቼ የሟቾችን ዝርዝር ይዤ እመለሳለሁ።