Get Mystery Box with random crypto!

ለትግራይ አክቲቪስቶች…!! '…ሰሞኑን በዚህ በዳያስጶራ ያሉ የትግራይ ተወላጅ ነን የሚሉ ጉዶች | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ለትግራይ አክቲቪስቶች…!!

"…ሰሞኑን በዚህ በዳያስጶራ ያሉ የትግራይ ተወላጅ ነን የሚሉ ጉዶች ከወትሮው በተለየ መልኩ የሌለ እየቀወጡት የሚመቱትን ከበሮ፣ የሚዘሉትን ዝላይ ባየሁ በተመለከትኩም ጊዜ ይህችን ማስታወሻ ጻፍኩ።  ገና ለገና ቆቦ ገባን ተብሎ እንዲህ የሌለ መፎከርና መዝለል የጤናም አይመስለኝም።

"…የምትዋጋው ከወንድምህ ጋር ነው። የሚፈሰው የሁለታችሁም ደም ነው። እንዲሁ ስትተጋተግ ትናራለህ እንጂ የፈለገ መንግሥታዊ ሸፍጥ ቢኖር፣ የፈለገ ሴራ ቢጎነጎን፣ የምትመጡበት ዐማራ ዘላለሙን እንደማይፋታችሁ ልታውቁ ይገባል። ያውም እየወረራችሁት። ያውም እየዘረፋችሁ እየገደላችሁት በሰላም ረግጠነው እንደ ድሮው እንኖራለን ባትሉ መልካም ነው። የምትወሩት፣ የምትዘርፉት ዐማራ አይፋታችሁም። እንኳን በአደባባይ ዐማራ የሚባል የለም እያላችሁ እየፎከራችሁ፣ ከእርሻው፣ ከቤቱ፣ ከቀዬው፣ ከመንደሩ፣ ከደብሩ አፈናቅላችሁት፣ በገዛ ሃገሩ ተንከራታች፣ ስደተኛ አድርጋችሁት፣ በእናንተው የነፃ አውጪ ተብዬዎች የጥላቻ ፖለቲካ ትርክት ምክንያት ስሙን አስጠፍታችሁት ልታጠፉት አልቻላችሁም።

"…ይሄ የምታዩት የምታዩት የሬሳ ክምር የትግራይ ወንድሞቻችን አስከሬን ነው። ለእናንተ ደግሞ የወንድሞቻችሁ፣ የእህቶቻችሁ፣ የልጆቻችሁ፣ የዘመዶቻችሁ አስከሬን ። ተገደውም ይሁን ወደው ፈቅደው ለሚገቡበት ጦርነት የሚጠብቃቸው እንዲህ መርገፍ ነው። ወደ ዐማራም፣ ወደ አፋርም ምድር በኃይል በገባችሁ ቁጥር የሚጠብቃችሁ እንዲህ ያለ ሞት ነው። ጦርነት አትራፊ አይደለም። ከበሮ ይዞ መጨፈር፣ በለው፣ በለው ማለት አይጠቅማችሁም። ኢትዮጵያ ደግሞ ሁለቱንም ታክማለች። ሁለቱም ልጆቿን ታክማለች። የሞቱትም ወደ አፈሯ መኅፀን ይገባሉ። ታዲያ በዚህም ወገን ሰው አልሞተም። አልቆሰለም ማለት አይደለም። ግን ማሸነፍ አይታሰብም። እልቂት ብቻ እንጂ…!!