Get Mystery Box with random crypto!

'…አርበኛ ፋኖ ምሬ ወዳጆን ድውዬ አገኘሁት። በስልክም ብዙ አውራን። ስለ መከላከያው ስለ ዐማራ ል | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አርበኛ ፋኖ ምሬ ወዳጆን ድውዬ አገኘሁት። በስልክም ብዙ አውራን። ስለ መከላከያው ስለ ዐማራ ልዩኃይል እና ስለ ምሥራቅ ዐማራም ፋኖም ተጋድሎ ጀግናው በቃሉ መስክሮልኛል። "…ዘመዴ ከሁሉም እኮ ጥቂት ጥቂት በጥባጭ ሊኖር ይችላል። ነገር ግን ሁላቸውም መከላከያም፣ ልዩኃይሉና ፋኖው በዐማራ ምድር እየተዋደቀ ነው። ደሙንም እያፈሰሰ ነው። ሌላ ሌላውን ትተን በአንድነቱ ላይ እናተኩር። የውስጥም የውጪም ጠላት ማሸነፊያው አንድነት ብቻ ነው። ብሔርብሔረሰቦች ናቸው እየተዋደቁ ያሉት። ከድል በኋላ ስህተት ነው የምንለውን ብናጠራ ይሻለናልም ደግሞም አትጠራጠሩ እናሸንፋለንም ብሎኛል። ንግግሩ ልብያሞቃል።

"…ምሬ ትክክለኛውን ስንቅ የሚያገኙበትን የባንክ አካውንትም በራሱ አንደበት ሰጥቶኛል። እዚህ ርቀት ድረስ የሄድኩት ለዚሁ ነው። ዘመዴ እኛ የምንበላው ባጣን ጊዜ ከመከላከያውና ከልዩ ኃይሉ ተካፍለን ነው የምንበላው። እነሱም እንደዚያው። ወደሞት የምንሄድ እኛ አንድ ነን። በሰጠሁህ የባንክ አካውንት ላክልን። ኮሚቴዎች ከደሴና ከኮምቦልቻ አውጥተው ኮቾሮ ገዝተው ይልኩልናል። አመሰግናለሁ። ብዬው ተለያይተናል።

"…እናንተ ተዘጋጁ። አምስትም አስርም ሳንቲም ለማዋጣት ተዘጋጁ። ስንቅ መግዣ የሚሆን ለማዋጣት ተዘጋጁ። ቆይቼ እለጥፍላችኋለሁ። የምሥራቅ ዐማራ ፋኖን ካገዝን በኋላ ደግሞ ሌሎች እንዲህ በበረሃ ለሚዋደቁም እጅን መዘርጋት ያስፈልጋል።

"…ከዚያ በፊት ግን በውጭ ሃገር ሆነው ህወሓትን በመደገፍ በሎም ለሚሉት እንዴት የትግራይ ልጆች በዐማራ ምድር እየረገፉ እንዳሉ አይተው ወደ ቀልባቸው ይመለሱ ዘንድ ዘግናኝ ፎቶ እለጥፍላቸዋለሁ። አደብ ግዙ። እልቂት እንጂ ድል አይኖርም።

"…እመለሳለሁ። ጠብቁኝ…!!