Get Mystery Box with random crypto!

'…ዝግጁ ናችሁ…? '…ሁሉም ጋር ደወልኩ። እንደተለመደው አስሬ ለክቼ አንዴ ቆርጬ መጥቻለሁ። አ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ዝግጁ ናችሁ…?

"…ሁሉም ጋር ደወልኩ። እንደተለመደው አስሬ ለክቼ አንዴ ቆርጬ መጥቻለሁ። አካውንቱን መንግሥት ያውቀዋል ብዬም ጠይቄአለሁ። አዎ ሕጋዊ ነን። ለዚህም አይደል ወይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይላክልን ያልነው ብለውኛል ምሬና አቤ። በዚህ ስጋት አይግባችሁ ዘመዴ ብለውኛል።

"…መንግሥት ራሱ ብሬንም እኮ ሰጥቶናል። የፈለገ ችግር ቢኖር ከማልቀስ የሚመጣ ነገር የለም። መፍትሄ እየፈለግን ከመመከት በቀር ሌላ አማራጭ ለጊዜው ጠረጴዛችን ላይ የለም ዘመዴ ነው የሚለው ዋርካው ምሬ ወዳጆ።

"…ከዚያ ወገን የሚሞቱትም ደሞቼ ናቸው። ወገኖቼ ናቸው። እና ምን ላድርግ። የሚመጡት የእኔን ቤተሰብ ሊዘርፉ፣ ሊገድሉ፣ ሊያፈናቅሉ እኮ ነው። የጨነቀ ነገር እኮ ነው። ስለዚህ አማራጩ ራስን መከላከል ነው። ይሄ ደግሞ ተፈጥሮአዊ መብት ነው።

"…ጦርነቱ ሲያልቅ በህይወት ከተረፍኩ እኔ ምርጥ ገበሬ ነኝ። አርሼ እበላለሁ። ነግጄም ማትረፍ አያቅተኝም። ጦርነት ወደን የገባንበት አይደለም። ተገደን እንጂ። አምና ህዝቤ የደረሰበትን ፍዳ ዓለም ሁሉ ያየው ነው። ዘንድሮም ያ እንዲደገም አንፈቅድም። የእኛም ከአምናው ዘንድሮ የተሻለ ዝግጁና ቁመና ላይ ነን።

"…በቃ ለዚህ ፋኖ ኮቾሮ መግዢያ ላኩልን። መልእክቴ ይኸው ነው ብሏችኋል ዋርካው አርበኛ ፋኖ ምሬ ወዳጆ።

"…እናም አሁን #1000 ሰው ዝግጁ ነን ካለ በኋላ እርግጠኛውን የእነ ምሬን የባንክ አካውንት እለጥፍላችኋለሁ። እነ ምሬ ወዳጆም ጦማሯን ስለሚያዩ በዚያውም ሞራልም ይሆናቸው ዘንድ እስቲ ዝግጁነታችሁን ጻፉላቸው።

"…አሃ ወገን… ዝግጁ…?