Get Mystery Box with random crypto!

'ርዕሰ አንቀጽ' '…የዛሬ ርዕሰ አንቀጽ የተጻፈው በራሴ ጉዳይ ዙሪያ ነው። በጀርመን ቆይታዬ እ | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የዛሬ ርዕሰ አንቀጽ የተጻፈው በራሴ ጉዳይ ዙሪያ ነው። በጀርመን ቆይታዬ እስከ አሁን ሁለት ጊዜ ተከስሻለሁ።  ሁለቱንም ክሶች ዐቃቤ ሕግ ሳይደርስ፣ ወደ ፍርድ ቤት ክርክርም ሳይመራ በፌደራል ፖሊስ ምርመራ፣ ቃሌን በሰጠሁ ጊዜ የቆመ ነው። የመጀመሪያው በኢትዮጵያ ጽንፈኛ እስላሞች ውትወታ በሐሰት በእኔ ባልሆነ ነገር ግን በእኔ ስም በፌስቡክ ገጽ ላይ በተጻፈ የአሸበርቲነት ጦማር ነበር።

"…ከምርመራ በኋላ ፖሊስ እንዲህ ብሎኝ ነበር። ከሳሾችህን መክሰስ ትችላለህ። እኔም መለስኩ። አልከሳቸውም። እነሱም እንደ እኔው ስደተኛ ናቸው። ባያውቁ፣ ባይረዱ፣ ባይገባቸው፣ ቢመስላቸው በስሜት፣ በንዴት፣ ለሃይማኖታቸው ቀንተው ያደረጉት ነው። እኔ እንደተንከራተትኩ መንከራተት የለባቸውም። ይልቅ ንገሯቸው። አስተምሯቸው ብዬ ፋይሉን ዘጋሁት።

"…ቆይቶም ባለፈው የገና ሰሞን ድጋሚ ከሰሱኝ። ያኔ እንኳን የከሰሱኝ በኦሮሞ እና በትግሬ ጽንፈኛ አክቲቪስቶች ጫና አዲስ አበባ የሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ በደረሰበት ጫና ምክንያት በተፈጠረ ምክንያት ነበር ከፖሊስ ጋር የተገናኘነው። የተከሰስኩትም ይሄንኑ አራጅ ከሃዲ የአቢይ ጦር "በፌክ ፎቶ ሲከሱት በፍጹም ስንትና ስንት የፈጠጠ ወንጀል እያለው ይሄን ፌክ ፎቶ መጠቀም ነውር ነው በማለቴና ዘመቻውን በማክሸፌ ምክንያት የተበሳጩ ነውረኞች የፈጠሩት ነበር። እሱም ውድቅ ሆኗል።

"…የአሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። ከሳሾቼን አላወቅኳቸውም። ያው አሸበርቲ ስላለኝ መንግሥት ይሁን፣ ግለሰቦች ይሁኑ፣ ማኅበራት ወይም ድርጅቶች አላወቅኩም። የአሁኑን ግን በብዙ ምክንያት ነገርየውን እንዲሁ በዋዛ ማለፍ አልፈለግሁም። አዎ ከሳሾቼን ወይም ከሳሼን ማወቅ እፈልጋለሁ። ከፖሊስ ጣቢያ በዘለለ ፍርድቤት ቀርቤ ከከሳሾቼ ጋር መሟገት እፈልጋለሁ። ለሚደርስብኝ ቁሳዊም ሆነ አዕምሮአዊ ጉዳት በሕግ አግባብ የሚጠየቀውን መጠየቅ እፈልጋለሁ። በዚያ ላይ ካሳሼን በስም በአካል ማወቁ በራሱ ለእኔ የግድ አስፈላጊም ጠቃሚም ነው።

"…በሌሊት ነው በጠዋት ከመኖሪያ ከተማዬ ተነሥቼ የሕግ ባለሙያ ጠበቃዬ ወደሚገኝበት ከተማ ከመንፈሳዊ ወንድሜ ከኢሱ ጋር የሄድኩት። ከእንግዲህ የሚፈልገኝ፣ የሚከሰኝ ሰው በሙሉ ከእኔ ጋር በአካል ግንኙነት አይኖረውም። ለእኔ መጥሪያ መስጠት ቤተሰቤንም ማጨናነቅ አይጠበቅበትም። ይከሰኛል የክስ ወረቀቱ ለጠበቃዬ ይደርሰዋል። ስፈለግ እቀርባለሁ እሟገታለሁም። ይሄንን ጨርሼ አሁን ገና ከጠበቃዬ ቢሮ ወጥቼ የጓደኛዬ የኢሳያስን ልጆች ጠይቄ፣ ለማታው የኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ መርሀ ግብሬ ለመድረስ ባቡር እና አውቶቡስ ይዤ ወደ ራየን ወንዝ ማዶ ጎጆዬ እመለሳለሁ። የሚያበሳጨው ግን እስከአሁን ድረስ ስንትና ስንት ምን የመሳሰሉ ቃሪያ በሚጥሚጣም የሆኑ ጦማሮች እንዳልለቅ ጌዜዬን መበላቴና ስለራሴ ማውራት የማልፈልገውን የግድ ስለራሴ ለማውራት መገደዴ ነው።

"…ቀጥሎ ከእኔ ጓደኞች ከእናንተ ከቤተሰቦቼ ምን ይጠበቃል? ስለሚለው ጉዳይ እሱን ቆይቼ እመለስበታለሁ። እንግዲህ ዛሬ በእኔ ጉዳይ ነው ስናወጋ የምንውለው። በእኔ በኩል ግን እንደ ዜጋ ስለ ሃገሬ፣ እንደ አማኝ ስለሃይማኖቴ ደሀ ተበደለ፣ ፍርድም ተጓደለ ብዬ ለመጮህ የማንም ፈቃድ አያስፈልገኝም። ከመቃብር በቀር ማንም ምንም አያስቆመኝም።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው።